ለዛሬ ደግሞ የምንመለከተው ሌላው የ‹‹ላ ኢላሀ ኢለሏህ››ን እምነት ከሚያፈርሱት ውስጥ አንዱ የሆነውን የኩፍር ተግባር ነው፡፡ በ‹‹ኩፍር›› እና በ‹‹ሺርክ›› መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ፡ ቅድሚያ የ‹‹ኩፍር››ን ምንነትና ትርጉሙን በመጠኑ እንየው፡-
Author: Admin
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -18
የሰው አይን በመፍራት፣ ወይም ሊመጣ ከሚችል በሽታ ሰበብ ሆኖ ይከላከላል በማለት በአንገትና በእጅ ላይ የሚታሰሩና የሚንጠለጠሉ ነገሮች ከትንሹ ሺርክ ይመደባሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች ሰበብ ከመሆን አልፈው በራሳቸው ኃይል አደጋን ይከላከላሉ፣ የተከሰተን አደጋ ደግሞ ያነሳሉ ብሎ ማመን ደግሞ ትልቁ ሺርክ ውስጥ ይከታል፡፡ አላህ ልጆችን ከሰው አይን ለመከላከል፡ በአንገት ላይ የሚንጠለጠል ሒርዝን ወይም በእጅ የሚጠለቅን ቀለበትና አምባር ሰበብ አላደረገም፡፡ ይህ የሰዎች የተሳሳተ አመለካከት ነው፡፡ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን ነቢያችን (ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ሐሰንና ሑሰይንን (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ፡- “አዒዙኩማ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ፣ ሚን-ኩልሊ ሸይጧኒን-ወሃምማህ፣ ወሚን-ኩልሊ ዐይኒን-ላምማህ” በማለት ከአላህ ዘንድ ጥበቃን ይለምኑላቸው ነበር፡፡ ከዛም፡- “አባታችሁ (ነቢ ኢብራሂም ዐለይሂ-ሰላም) ኢስማዒልንና ኢስሐቅን በዚህ ዱዓእ ይጠብቃቸው ነበር” ይሏቸዋል፡፡ (ቡኻሪይ 3371፣ ኢብኑ ማጀህ 3525፣ አቡ ዳዉድ 4737)፡፡ ትርጉሙም፡- (ሙሉ በሆነው በአላህ ቃል፡ ከሰይጣናትና ከገዳይ መርዛማዎች ሁሉ፡ እንዲሁም ከክፉ አይኖች እጠብቃችኋለሁ) ማለት ነው፡፡ እኛም እሳቸውን በመከተል ይህን አስተማማኝ ዱዓእ ማድረግ እያለብን፡ ሰበብ ያልሆነ ነገር ላይ መንጠልጠል አግባብ አይደለም፡፡ ይልቁኑ ሺርክ ላይ የሚከት ስራ እንደሆነ በሌላ ሐዲሥ ተገልጾአል፡-
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -17
‹‹አት-ተጠዩር››፡- በገድ ማመን ማለት፡- በምናየው ወይም በምንሰማው ነገር ላይ ተመርኩዘን፡ በቃ ሊቀናኝ ነው ወይም ሊከፋኝ ነው የሚል አስተሳሰብና ድምዳሜ ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- አሜሪካኖች 13 ቁጥርን አይወዱትም፡፡ ከመቶ አመታት በፊት የተከሰተ ክስተትን በማንሳት ዛሬም በቀኑ ላይ መጥፎ ጥርጣሬ አላቸው፡፡ ፎቆቻቸውን ስትቆጥሩ 12 ይልና 14 ነው ቀጣዩ፡፡ 13ትን ይዘሉታል፡፡ 13 ቁጥር ያለበት ቤት እንኳ ገዢ የለውም፡፡ ወደ ሆቴል ስትሄዱ 13 ቁጥር ሆቴል የለም፡፡ እስኪ ቆም ብላችሁ አስቡ፡፡ ቁጥር እና ቀን ሰውን ምን ማድረግ ይችላሉ? ይሄ ሁሉ በገድ የማመን ውጤት ነው፡፡
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -16
ሌላው ትንሹ ሺርክ ውስጥ ከሚካተቱት ጉዳዮች አንዱ የ‹ማጣመር› ጉዳይ ነው፡፡ ማጣመር ማለት፡- ለአንድ ሰው፡ አንተን መልካም ነገር ለማግኘትህም ሆነ መጥፎ ነገርን ካንተ ለመከላከል ሰበብ በሆነው ነገር ላይ የአንተ አጸፋዊ ምላሽ፡- ‹‹አላህና አንተ ባትረዱኝ ኖሮ፣ አላህና አንተ ባትደርሱልኝ ኖሮ›› ማለትህ ነው፡፡ ይህ አባባል የሺርክ ቋንቋ ነው፡፡ የአላህን ሰጪነትና ከክፋት ተከላካይነት ከፍጡሩ ሰበብ መሆን ጋር ተያይዞ በ‹‹እና›› ሊገለጽ አይገባም፡፡ ማለት እንኳ ካለብህ፡- ‹‹አላህ ባይረዳኛ ከዛም አንተ ሰበብ ባትሆነኝ፣ አላህ ባይደርስልኝ ከዛም አንተ ባታግዘኝ ኖሮ›› ነው ማለት ያለብህ፡፡
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -15
ባለፉት ተከታታይ ቀናት ስለ ትልቁ ሺርክ ስድስት ነጥቦችን አንስተን ተመልክተናል፡፡ አሁን ደግሞ አላህ ፈቃዱ ከሆነ ስለ ትንሹ ሺርክ የተወሰኑ ነጥቦችን እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-
ትንሹ ሺርክ የሚባለው፡- ተግባሩ (ስራው) ሺርክ ሆኖ፡ ነገር ግን ግለሰቡን (ሰሪውን) ከኢስላም አጥር የማያስወጣው፡ ሆኖም ለከፋ ኃጢአት የሚዳርገው፡ ከዚህ ተግባሩም ሳይቶብት ከሞተ፡ በአኼራ የኃጢአቱን ያህል የሚያስቀጣው ማለት ነው፡፡ ትንሹ ሺርክ ውስጥ ከሚመደቡ የኃጢአት ስራዎች መካከል፡-
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -14
የአላህን ትእዛዝ በሚቃረን መልኩ ፍጡራንን መታዘዝ፡ እነሱን ማምለክ ማለት ስለሆነ ‹‹ሺርክ›› ነው፡፡ ይህም ማለት፡- አላህ የፈቀደውን ነገር እርም ነው ሲሉን፣ እሱ የከለከለውን ነገር የተፈቀደ ነው ሲሉን፡ አሚን ብለን ተስማምተን ከተቀበልን ተገዛናቸው ማለት ነው፡፡ አንድን ነገር ሐራምም ይሁን ሐላል ማለት የአላህ መብት ብቻ ነው፡፡ ህግን ማውጣትና መደንገግ ከአላህ የጌትነት መገለጫዎቹ አንዱ ነው፡፡ ስለሆነም ከአላህ ዲን ተቃራኒ የሆነን ነገር፡ ፍጡርን መታዘዝ የለም፡፡ ጌታ አላህ በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይላል፡-
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” ክፍል -13
ለአላህ ያለንን ፍቅር ለፍጡር አሳልፎ መስጠት የ‹‹ሺርክ›› ተግባር መሆኑን ለመረዳት፡ ቅድሚያ አላህን መውደድ ዒባዳህ መሆኑን እንመልከት፡፡
አላህን መውደድ በልብ ከሚፈጸሙ ታላላቅ የዒባዳህ ክፍሎች የሚመደብ ነው፡፡ ደግሞስ እንዴት አይወደድ? እኛ በዚህ ዓለም ላይ የምንፈልጋቸውንም ሆነ የምንወዳቸውን ነገራት ማነው አሟልቶ የለገሰን? ከራሳችን ብንጀምር፡- ከባዶነት ወደ ሕያውነት በማምጣት በምድር ላይ ፈጠረን፣ ለመኖር እንዲያስችለንም ከበላያችን ዝናብን በማዝነብ፡ ምድር ደግሞ ተቀብላ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን እንድታበቅል፡ ያበቀለችውን ደግሞ ለኛም ለእንሰሳትም ሲሳይ አደረገልን፡፡ (ሱረቱ ዐበሰ 24-32)፡፡
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -12
ተወኩል ማለት ቀጥታ ትርጉሙ፡- መመካት፣መጠጋት ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት፡- በዱንያም ሆነ በዲን ጉዳይ ላይ የሚጠቅመንን ነገር ለማግኝትና የሚጎዳንን ነገር ለማራቅ፣ ደካማነታችንን በመግለጽ ነገሩን ሊያሳካልን ወደሚችል ኃይል (አላህ) ልባችንን ማዞርና: በርሱ ላይ ተስፋ በማድረግ መመካትና፡ እሱም በሚረዳንና በሚወስንልን ነገር ወዶ መቀበል ማለት ነው፡፡
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -11
“አላህን መፍራት” የኢባዳዎች ሁሉ ቁንጮና ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡ የአኼራ ስንቅም ነው፡- “…ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው…” (ሱረቱል በቀራህ 197)፡፡ ከልብሶች ሁሉ ያማረ ልብስ፡ አላህን የመፍራት ልብስ ነው፡- “የአደም ልጆች ሆይ! ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፤ አላህን የመፍራትም ልብስ፣ ይህ የተሻለ ነው፤ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው፤ ይገሠጹ ዘንድ (አወረደላቸው)” (ሱረቱል አዕራፍ 26)፡፡ ውጫዊው ልብስ ገላችን እንዳይታይ ነውራችን እንዳይገለጽ እንደሚሸፍነው ሁሉ፡ ውስጣዊው ልብስ “ተቅዋ” ደግሞ ቀልባችንን በምቀኝነትና መሰል በሽታዎች እንዳንለከፍና እንዳንዋረድ ይሸፍነናል፡፡ “ተቅዋ” ታላቅ የዒባዳ ዘርፍ በመሆኑ ከአላህ ውጪ ላለ አካል ተላልፎ ሊሰጥ አይገባም፡፡ አላህ እንዲህ ይለናል፡- “…ሰዎችንም አትፍሩ፤ ፍሩኝም፤ በአንቀጾቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ፤ አላህም ባወረደው ነገር ያልፈረደ ሰው እነዚያ ከሐዲዎች እነርሱ ናቸው” (ሱረቱል ማኢዳህ 44)። “…አትፍሩዋቸውም፤ ፍሩኝም…” (ሱረቱል በቀራህ150)፡፡ “ይሃችሁ፣ ሰይጣን ብቻ ነዉ፣ ወዳጆቹን (ብዙ እንደሆኑ በመግለጽ) ያስፈራራችኋል፤ አትፍሩዋቸውም፤ ምእምናንም እንደሆናችሁ ፍሩኝ” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 175)፡፡ “…ዛሬ እነዚያ የካዱት ከሐይማኖታችሁ ተስፋ ቆረጡ፤ ስለዚህ አትፍሩዋቸው፤ ፍሩኝም…” (ሱረቱል ማኢዳህ 3)፡፡
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -10
“አድ-ዱዓእ” (ተማጽኖ)፡- ከአላህ ውጭ ያለ አካልን በሩቁ መማጸን (የሞቱ አካላትን) ወይም በቅርቡ ያሉ (በህይወት ያሉትን) አካላት በማይችሉት ነገር ላይ መማጸን ‹‹ሺርክ›› ነው፡፡ ይህ ተግባር ‹ሺርክ› መሆኑን በደንብ ለመረዳት ቅድሚያ ‹‹ዱዓእ›› የዒባዳ አካል መሆኑን እንመልከት፡-











