የኢየሱስን መለኮታዊነት አስመልክቶ በክርስቲያን ወገኖቻችን በኩል ለማስረጃነት ከሚያገለግሉ ጥቅሶች መካከል ከላይ የተጠቀሰው ዋነኛው ነው። በተለይም ለዘመናት “እየሱስ እኔ አምላክ ነኝ ካለ እንደዛ ያለበትን ቦታ አሳዩን” ለሚለው የሙስሊሞች ጥያቄ ያገለግላል በሚል ከሚቀርቡ “ማስረጃዎች” ይጠቀሳል። በዚህ ጽሁፍ ይህንን አንቀጽ በተመለከተ “እውን የኢየሱስን መለኮታዊነት ይገልፃልን?” በሚል መነሻ የተወሰኑ ሐሳቦችን በማስፈር ሙግቶቻችንን በማስረጃ ልንፈትሸው እንሞክራለን።
Category: ዒሳ (ኢየሱስ) عليه السلام
አል-መሲሕ
አምላካችን አላህ ታላቁን መልዕክተኛ ነቢዩ ኢየሱስን “መሲሕ” በሚለው የማዕረግ ስሙ ወደ 9 ጊዜ በተደጋጋሚ ይጠቅሰዋል። በሱረቱል አሊ-ዒምራን አንቀጽ 45 ላይ መላእክት የብስራትን ዜና ለማሪያም ይዘው ሲመጡ የሚወለደው ልጅ ስሙ “መሲሕ” ተብሎ እንደሚጠራ አስቀድመው ተናግረዋል። እስኪ ይህ የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ማዕረግ በኢስላም የስሙ ትርጓሜ ምንድነው ? አላህ ለዒሣ ለምን ይህንን ለቀብ “title” ሰጠው? የሚለውን ነጥብ እንመልከት:-
ኢየሱስ عليه السلام አለመሰቀሉን ለመግለጽ 600 አመት መቆየት ለምን አስፈለገ?
‘’አላህ ለምን 600 አመት ድርስ ጠብቆ ሙሐመድን ( ሰዓወ) ነብይ አድርጎ ላከው ? ለምን ቀደም ብሎ እየሱስ (ዐሰ) እንዳልተሰቀለ ለምን ቀደም ብሎ አልነገረንም ? በዚህም ምክንያት እኛ ክርስቲያኖች አላህ ለክርስትና እምነት መፈጠርና ሁሉንም ሰዎች ሆነ ብሎ በማሳሳት ተጠያቂ ነዉ እንላለን። ምክንያቱም እሱ ባያመሳስልባቸዉ ሰዎቹ ኢሳ ተሰቀለ ብለዉ አያምኑም ነበር! ክርስትናም አይኖርም ነበር ። ነገር ግን በዚያን ግዜ የነበሩ ሰዎች ዒሳ እንደተሰቀለ እና እንደሞተ ሊያምኑ የሚችሉበት በቂ ምክንያት አላቸው። ይህንን ነገር ሲያምኑ ወዲያውኑ ለምንድ ነው ነብይ ወዲያውኑ ያላከላቸዉ ለምን 600 አመታትን ለማስተማር ወሰደበት ? ‘’
“ከርሱ በሆነ መንፈስ” ምን ማለት ነው?
ባለፈው ‹‹ከርሱ በሆነው ቃል›› የሚለውን አንስተን፡ በዚህ ዙሪያ የሚነሱ ብዥታዎችን በአላህ ፈቃድ ለማጥራት የተወሰነ ሙከራ ተደርጓል፡፡ ዛሬም የአላህ ፈቃዱ ከሆነ ‹‹ከርሱ የሆነ መንፈስ›› በሚለው ላይ መጠነኛ ቆይታ እናደርጋለን ኢንሻአላህ፡፡
“ከርሱ በሆነው ቃል” ምን ማለት ነው?
መርየም ያለ ትዳር-አጋር ሰው የመውለዷ ነገር አስገርሟት፡ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በጠየቀች ጊዜ የተሰጣት ምላሽ፡- ‹‹ነገሩ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል›› የሚል ነበር፡፡ ይህ ማለት አላህ አንድን ነገር ከሻው (ከፈለገው) ለመፍጠር የሚከለክለው ነገር የለም! ያለ ምንም ሰበብም (እናትና አባትም ሳይኖሩ) መፍጠር ይችላል ነው፡፡ ከዛም አንቀጹ ይቀጥልና፡- ‹‹አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ሁን ይለዋል ወድያዉኑም ይሆናል፥ አላት›› በማለት፡ ከሷ የሚገኘውም ፍጥረት (ዒሳ) “ሁን” በሚለው የአላህ መለኮታዊ ቃል አማካኝነት መሆኑን አበሰራት፡፡ ስለዚህም ዒሳ (ዐለይሂ-ሰለም) ‹‹ሁን›› የሚለው የአላህ መለኮታዊ ቃል ውጤት እንጂ እርሱ ራሱ ‹ሁን› የሚለው ቃል አይደለም፡፡
የመርየም ልጅ ዒሳ ስሙ ቁርዓን ውስጥ ከ25 ጊዜ በላይ መጠራቱ የተለየ ያደርገዋል?
በዚህና መሰል የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾች መሠረት፡- ጌታ አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከቀደምት የነቢያትና የሕዝቦቻቸው ታሪክ ውስጥ፡ ለእምነታችን ጠቃሚና አርአያ የሚሆነውን በሳቸው በኩል እንደሚተርክልን መግለጹን እንመለከታለን፡፡ አያይዞም ይህ የነቢያት ዜና ‹‹በጣም መልካም ዜና›› (አሕሰኑል-ቀሶስ) መኾኑን ይገልጽልናል፡፡ ምክንያቱም በነቢያት ሥም የተጻፉ፣ የአምላክ ቃል በሚል ሽፋን የሰው ድርሰት የኾኑ የሀሰት መጽሐፍቶች አሉና!፡፡ ቅዱስ ቁርኣን ግን ቃሉም ሆነ መልእክቱ የአላህ እንጂ፡ የመላእክት ወይም የነቢያት ወይንም የጸሐፍት አይደለምና፡ በውስጡ ያሉት ታሪኮች ሁሉ ፍጹም እውነት ናቸው፡፡ ሌሎች ‹መለኮታዊ› መጽሐፍት የተባሉት በጠቅላላ በሱ ይመዘናሉ እንጂ፡ እሱ በማንም መጽሐፍት አይመዘንም፡፡
እውን የመርየም ልጅ ዒሳ ሊፈርድ ይመጣልን?
ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “ነፍሴ በእጁ በኾነችው ይሁንብኝ! በናንተ ላይ የመርየም ልጅ ፍትሐዊ ዳኛ ኾኖ ሊወርድ ይቃረባል፡፡ መስቀልንም ይሰባብራል፡፡ አሳማዎችንም ይገድላል፡፡ ግብርንም ይተዋል፡፡ ገንዘብንም የሚቀበለው ሰው እስኪጠፋ ድረስ ይበራከታል፡፡ ለአላህ የሚደረግ አንድ ሱጁድ ዱንያና በውስጧ ከያዘችው ኹሉ የበለጠና የተሻለ ይኾናል” ከዚያም አቡ ሁረይራህ፡ ‹‹ከፈለጋችሁ ይህን አንቀጽ አንብቡ›› አለ፡፡ ‹‹ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በእርሱ (በዒሳ) በእርግጥ የሚያምን እንጅ (አንድም) የለም፡፡ በትንሣኤም ቀን በነሱ ላይ መስካሪ ይኾናል፡፡››፡፡ (ቡኻሪይ 3448፣ ሙስሊም 406፣ አሕመድ 7471፣ ቲርሚዚይ 2398)፡፡
የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ አይደለም!
ሰሞኑን የመርየምን ልጅ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) በተመለከተ፡ ተከታታይ ትምሕርቶችን እየዳሰስን ነው፡፡ በተለይ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከነቢይነትና ከሰብአዊ ፍጥረት ክልል አውጥቶ እሱን አምላካዊ ማንነት ለማላበስ የሚደረገውን ከንቱ ሙከራ ምላሽ እየሰጠንበት ነው፡፡ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከነቢያት ኹሉ በላይ ከፍ ለማድረግ ያግዙናል የሚሏቸውን አንዳንድ ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾችንም በማንሳት የአንቀጹን ትክክለኛ መልእክት እና የነሱን የተሳሳተ ግንዛቤ እየተመለከትን ነው፡፡ ዛሬም አላህ ፈቃዱ ከኾነ የምንመለከተው የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ እንዳልነበረ፣ እንዳልኾነና ፈጽሞም ሊኾን እንደማይቸል የሚያስረዱትን ቀጥታና ግልጽ የኾኑ የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾችን በመጠቀም ነው፡፡ መልካም ንባብ፡-
የዒሳ በሕይወት መቆየት ምን ያሳየናል?
ዛሬ የምናስተናግደው ጥያቄ ደግሞ ይህ ነው፡፡ እሱም፡- የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ሳይሞትና ሳይገደል አላህ ወደራሱ ካነሳው (ከወሰደው)፣ እስካሁንም በሕይወት ካለ፡ በርግጥም እሱ ምድራዊ ቆይታቸውን ፈጽመው፡ ወደ መቃብር ዓለም ገብተው ስጋቸውና አጥንታቸው በስብሶ ከቀረው ነቢያት ይበልጣል ማለት ነው! የሚለውን ነው፡፡ ይህ አመለካከት ግን ፍጹም ስህተት መኾኑን ቀጥሎ ባሉት ምክንያቶች ይብራራል፡-










