ከአመታት በፊት ጋዜጠኛ አብዱረሒም ቢቢኤን ሬዲዮ ላይ በሚሰራበት ወቅት አንድ ማንነቱ ከማይታወቅ ሰው ሚስጥራዊ ቪዲዮ ተላከለት። የዚህ ቪዲዮ ¹ ይዘት አስደንጋጭ ነበርና ይፋ ከማድረጉ በፊት የተወሰነ ቀን አሰበበት፥ ለሚቀርባቸውም ሰዎች አጋርቶት ተማከረበት። በስተመጨረሻም ይፋ አደረገው። ይፋ ከተደረገ በኃላ ብዙውን ሰው አስደነገጠ፣ መነጋገርያም ሆነ። ቪዲዮውን ለማስታወስ ያክል አንድ የሙስሊም አለባበስ የለበሰ ሰው የሆነ መጋዘን ውስጥ ለወንጌላውያን የሰጡትን ተልዕኮ እንዴት እየፈጸመ እንዳለ በዝርዝር የሚተነትንበት ነው።
Category: የክርስትያን ሚሽነሪዎች እንቅስቃሴ
የወንጌላውያን ወጥመዶች -3
የወንጌላውያን ወጥመዶች -3
የወንጌላውያን ወጥመዶች -2
የወንጌላውያን ወጥመዶች -2(የምስክርነት ቴክኒክ)..❝.. አቡ ሀይደር አንተ ክርክር ምን ያደርግልሀል? እግዚአብሄር እውነቱን ገልፆልሀል አይደል?..❞..ወንጌላውያን ሙስሊሞችን መሳብ እንችላለን ብለው ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱ የምስክርነት መንገድ ነው። የዚህ መንገድ ዋነኛ ሚና እስልምናን ክደናል የሚሉ የሆኑ ግለሰቦችን በምሳሌነት በማሳየት “ኑ እናንተም” የሚሉበት መንገድ ነው። በዚህ መንገድ ተርታው ሙስሊም ላይ ብዥታን በመልቀቅ ከእስልምና ለማፍለስ ይሞክራሉ። በዚህ መንገዳቸው ውስጥ ግን…
ሙስሊሞችን ማጥመድ (1)
የወንጌላውያን ወጥመድ -1…❝የፖለቲካ መሪዎችን ወይንም በማኅበረሰቡ ላይ ተጽእኖ የሚፈጥሩ አካላት ላይ ትኩረት ማድረግ❞..በሳውዘርላንድ ባፕቲስት ቲኦሎጂካል ሴሚናሪ ውስጥ የሚስዮን እና የወንጌል ስርጭት ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆነው ጆን ማርክ ሙስሊሞችን በወንጌል ስለመድረስ በጥልቀት ለመጻፍ ሞክሯል። እንደ ጆን ማርክ እሳቤ መሠረት ሚስዮናውያን ተርታው ህዝብ ላይ ትኩረት ከሚያደርጉ ይልቅ መሪዎችና የማኅበረሰቡ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ጋ ትኩረት ቢያደርጉ መልካም እንደሆነ ቅድሚያ…
ሙስሊሙን ማክፈር – የዘመናዊው አለም የሚሽነሪ እንቅስቃሴ
ወቅቱ በ1930 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠርር ነበር፤ የግብፁ አል-አዝሀር ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንግዳ ነገር ተሰማ። በሳሙኤል ዚውመር የተመራው የሚሽነሪ ቡድን ያለምንም ፍርሀት ቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ዘልቆ በመግባት የተለያዩ ፓምፍሌቶችንና ብሮሹሮቹን በተነ።በተግባሩ የአዝሀር ዑለሞች ተቆጡ፤ “ፈጽሞ አይደረግም” በሚል ሀሳብ ያንቀላፉት ሳይቀር ባለማመን ሰመመን ውስጥ ሁነው ድንጋጤ አላወሳቸው። የሁሉም ጥያቄ ግን “እነዚህ አካላት በዚህ ደረጃ እንዴት ደፈሩ?” “በርግጥ የዚህ ተግባር መንስኤ የነሱ ድፍረት ነው ወይንስ የኛ ድክመት?” የሚሉት ነበሩ






