ከአዒሻህ (ረ.ዐ) እንደተተረከው፡ እርሷ እንዲህ ብላለች:- ‟ሙሐመድ (ﷺ) ጌታውን አይቷል ብሎ ያወራልህ ማንኛውም ሰው በእርግጥ ዋሽቷል፣ እርሱም ዓይኖች አያገኙትም ይል ነበርና።”
(📚Sahih al-Bukhari,7380: Book 97, Hadith 10)
Category: ሐዲስ
አንዱና ብቸኛው “አል ዋሒዱል አሐድ”
“አል-ዋሒድ” የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ አንድና ብቸኛ ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ በህልውናው (በዛቱ) የማይከፋፈል አንድ ጌታ በመሆኑ “አል-ዋሒድ” ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ዩኒቨርሱን (አጽናፈ ዓለሙን) ሲፈጥር ያለ አጋርና ያለ አማካሪ ብቻውን ያዘጋጀ በመሆኑ “አል-ዋሒድ” ይባላል፡፡ ጌታ አላህ በባሕሪያቱና በስሞቹ አምሳያና ሞክሼ የሌለው ብቸኛ አምላክ በመሆኑ “አል-ዋሒድ” ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ብቻውን የሚመለክና የሚሰገድለት እውነተኛ አምላክ በመሆኑ “አል-ዋሒድ” ተብሎ የሚጠራ ነው፡፡
ነብዩ ሙሐመድ “ﷺ” እና ራስን የማጥፋት ትርክቶች
በተለያዩ የእምነት ክፍል ውስጥ የሚገኙ እስልምናን የሚተቹ አካላት ይህንን አርዕስት በሰፊው ሲያራግቡት እናስተውላለን። ለጥያቄያቸው መሠረት የሆኑት በሰሒሕ አል ቡኻሪ ጥራዝ ውስጥ የሚገኙት የሀዲስ ዘገባዎች ሲሆኑ እነዚህን ዘገባዎች በማቅረብ ነብዩ (ሰዐወ) ራሳቸውን ሊያጠፉ ሙከራ ያደርጉ እንደነበር አድርገው ድምዳሜ ሊያስቀምጡ ይሞክራሉ።




