ብቻ የጌታ አላህ ትእዛዝ፣ የነቢያት ሱንና እና የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሕይወት ፈለግ ነው፡፡ አላህ ትዳር የሌላቸውን ሰዎች እንድናጋባቸው ትእዛዝን ሰጥቷል፡፡ ለጊዜው ችግረኞች ቢኾኑ ከሱ በኾነ ቸርነት እንደሚያብቃቃቸውም ቃልን ገብቶላቸዋል፡፡ ቀደምት ነቢያትንም በትዳር እንዲጣመሩ በማድረግ የነቢያት ሱንና መኾኑንንም አበክሮ ነግሮናል፡፡
Author: አቡ ሐይደር
‹‹ሴቶቻችሁ ለናንተ እርሻ ናቸው!››
የአንቀጹን ትክክለኛ መልእክት ለመረዳት አንቀጹ የወረደበትን ምክንያት ማወቁና መገንዘቡ መልካም ነው፡፡ አንቀጹ የወረደበት ምክንያት የአይሁዶችን የተሳሳተ ግልብ ግንዛቤ ለማስተካከልና፡ ሶሓቦችም (ረዲየላሁ ዐንሁም) በነሱ ስንኩል አስተሳሰብ አብረው እንዳይጠፉ ለማስተማር ነው፡፡ ጉዳዩም፡- አይሁዶች ሴቶቻቸው (ሚስቶቻው) የወር አበባ በመጣባቸው ወቅት፡ አብረዋቸው አይመገቡም፣ አብረው አይተኙም ነበር፡፡ ይህ በወር አበባ ወቅት ሴትን የማግለል ጉዳይ ዛሬም በኦሪት ዘሌዋውያን 15፡19-22 ላይ በግልጽ ሰፍሯል፡፡ ይህን ጉዳይ ሶሓቦች ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲያቀርቡት፡ እንዲህ የሚለው የአላህ ቃልም ምላሽ ሆኖ ወረደ፡-
ቁርኣን የአላህ እንጂ የጂብሪል ቃል አይደለም!!
ከነዚህ ሁለት የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾች በመነሳት አንዳንድ ክርስቲያን ወገኖች ቁርኣን የጂብሪል (ዐለይሂ ሰላም) ቃል እንጂ የአላህ አይደለም ይሉናል፡፡ እኛም ለቀረቡት የቅዱስ ቁርኣን ጥቅሶች ምላሻችንን ከመስጠታችን በፊት አንድ ጥያቄ እናቅርብላቸው፡፡ እሱም፡- ባቀረባችሁት ሁለት የቁርኣን ጥቅሶች መሰረት፡ ቅዱስ ቁርኣን የጂብሪል ቃል ነው ብላችሁ ስትሞግቱን፡ እናንተ የጂብሪል ቃል መሆኑን አምናችሁ ተቀብላችሁ ነውን? ወይስ እንዲሁ ሳታምኑበት ለሙግት ብቻ?
አንዱና ብቸኛው “አል ዋሒዱል አሐድ”
“አል-ዋሒድ” የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ አንድና ብቸኛ ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ በህልውናው (በዛቱ) የማይከፋፈል አንድ ጌታ በመሆኑ “አል-ዋሒድ” ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ዩኒቨርሱን (አጽናፈ ዓለሙን) ሲፈጥር ያለ አጋርና ያለ አማካሪ ብቻውን ያዘጋጀ በመሆኑ “አል-ዋሒድ” ይባላል፡፡ ጌታ አላህ በባሕሪያቱና በስሞቹ አምሳያና ሞክሼ የሌለው ብቸኛ አምላክ በመሆኑ “አል-ዋሒድ” ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ብቻውን የሚመለክና የሚሰገድለት እውነተኛ አምላክ በመሆኑ “አል-ዋሒድ” ተብሎ የሚጠራ ነው፡፡





