ሥላሴያውያን በ4ኛው ክፍለዘመን የቁስጥንጥንያ ጉባኤ ላይ በአብላጫው ድምፅ ከአምላክ ጋር እኩል ይሆን ዘንድ የተወሰነውን መንፈስ ቅዱስ ባይብላዊ መሠረት ለማስያዝ በርካታ ጥቅሶችን አዛብተው ሲያቀርቡ ይስተዋላሉ። መንፈስ ቅዱስ በትኛውም የብሉይም ሆነ የሐዲስ ኪዳን መፅሐፍ ላይ እራሱን የቻለ ኑባሬያዊ መለኮት መሆኑን አይናገርም። ይህን ስንል አብዛኛውን ጊዜ ሚሽነሪዎች የሚከተለውን ጥቅስ ለመንፈስ ቅዱስ ፈጣሪነት ለመጠቀም ይሞክራሉ። እስኪ እንፈትሸው:-
Category: መጽሀፍ ቅዱስ
አፅናኙ ማነው? የአፅናኙ ወሬ ትርክትና የክርስቲያኖች መሟገቻ
በመጽሀፍ ቅዱስ የተነገረለትና የሚመጣው የተባለውን “አፅናኝ” በተመለከተ ከሙስሊሞች ለሚነሱ መከራከሪያዎች ክርስቲያኖች የሚያቀርቧቸው መልሶች ሁሌም በቀዳዳ የተሞሉ ናቸው። ይህ አጽናኝ ተብሎ የተተነበየለት አካል ነብዩ ሙሐመድ “ﷺ” እንዳልሆኑ ለማስረዳት የሚያደርጉት ክርክር ክፍተቶቻቸውን እና ደካማነታቸውን የሚያጋልጥ ነው። ይህንን አጀንዳ በተመለከተ “አፅናኙ ማነው?” በሚል ርእስ ከአመታት በፊት በድምፅ የሰጠሁትን ትምህርት ብትከታተሉት አሁን ለሚወራው መከራከሪያ እንደ መግቢያ ሙሉ ምስል ያስጨብጣችኃል
የማቴዎስ ወንጌል
የማቴዎስ ወንጌል በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ ከተመሳሳዮቹ ወንጌላት {Synoptic Gospels} አንዱ ሲሆን በአቀማመጡ ረድፍ የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያ መግቢያ ላይ ተሰድሯል።
የሉቃስ ወንጌል
«ሉቃስ ማለት የጳውሎስ ተማሪ ጋደኛው የነበረና የሕክምና ሙያ ጭምር የነበረው ሰው ነበር። ጳውሎስም ኾነ ሉቃስ ኢየሱስን አያውቁትም በዘመናቸውም አልተገናኙም። ይሁንና የዚህ የጳውሎስ ጓደኛ የሆነው ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈበትን ዘመን ምሁራን እንደሚያስቀምጡት ከ80-90 AD እንደተዘጋጀ ይናገራሉ። እስከ 110 AD ያደረሱትም አልጠፉም። ይህ የመጀመሪያው ቅጂ {manuscript} ጽሑፍ ደብዛው ጠፍቷል ምኑም የለም። ዛሬ ላይ የዚህ ወንጌል ቀዳማይ ጽሑፍ {Manuscript} አለ የሚባለው በ 250 AD ላይ የተዘጋጀ ፓፒረስ 75 {Papyrus 75} ነው።
የማርቆስ ወንጌል
የማርቆስ ወንጌል «ከአራቱ ወንጌላት መካከል የመጀመሪያውና በቀዳሚነት እንደተጻፈ የሚታመነው የማርቆስ ወንጌል ነው። ይህ ወንጌል ከ66- 70-4) AD ባሉት ጊዜያት እንደተጻፈ ይገመታል። ምሁራን አራቱም ወንጌላት ጸሐፊያቸው በእርግጠኝነት አይታወቅም ይላሉ። አክለውም ጸሐፊዎቹ የኢየሱስ ሐዋሪያት ወይም የዘመኑ የአይን- ምስክሮችም አይደሉም ይልቁንስ ዛሬ ላይ ያለው ስያሜያቸው በ2ኛው ክፍለ ዘመን ላይ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አባቶች የተሰየሙ ባዶ ስያሜዎች ናቸው ይላሉ።…
የተረሳው መንፈስ ቅዱስ
እንደ ክርስቲያኖች እምነት መሠረት ከሥላሴ አካላት ውስጥ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ እንደ አብና ወልድ እኩል መለኮታዊ ስልጣን ያለው አምላክ ነው ብለው ያምናሉ። እንዳለመታደል ሀኖ ግን መንፈስ ቅዱስ የሚገባውን ያክል ቦታ አልተሰጠውም። አንዳንዴም እንዴውም ሌሎች አካላት ሁሉ ተጠቅሰው እሱ ሲረሳ እንታዘባለን። እንዴው መንፈስ ቅዱስ አምላክ የተባለው ሁሉ “አምላክ ሁለት ነው” እንዳይባል ተብሎ ብቻ የኃለኛው ጉባኤ የጨመረው ይመስላል። ይህንን ጥርጣሬ እስኪያረጋግጥልን ድረስ መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ልብም ሆነ በመጽሀፍ ቅዱስ ከአብና ወልድ ጋር እንኳን እኩል የማይታወስ ባይተዋር ተደርጓል። ማቴዎስ በወንጌሉ እንዲህ ማለቱ ተፅፏል፦
ከመጽሀፍ ቅዱስ አስገራሚ ይዘቶች መካከል
ከመጽሀፍ ቅዱስ አስገራሚ ይዘቶች መካከል








