ስራ መስራት አትወድም?በማለዳ ተነስተህ መጣርና መድከሙ አስመርሮሀል? እንግዲያውስ ለአንተ እግዚአብሔር መፍትሄ አለው፦
“የዕለት ጒርስ ለማግኘት በመጣር፣ ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤ እርሱ ለሚወዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።”
— መዝሙር 127፥2 (አዲሱ መ.ት)
እንደ መጽሀፍ ቅዱስ መሠረት ለምድራዊ ኑሮ መድከምህ “ከንቱ” ነው። እግዚአብሔር ቢወድህ ኑሮ እንቅልፍ ጥሎ ያስተኛህ ነበር።
If it is said that it will be a response
“እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ያለ ድካም አስተኝቶ ሲሳይ ይሰጣቸዋል ለማለት ነው” የሚል መልስ እንኳን ከተሰጠ የሚከተሉት እንቆቅሎሾች መብራራት አለባቸው፦
1/ መጽሀፍ ቅዱስ እራሱ መተኛትን ነቅፎ ስራን ደግሞ አበረታቶ ከገለጻቸው ሌሎች ምንባቦች ጋር መልዕክቱ ይጣረሳል። ለአብነት መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦
“ሰብሉን በበጋ የሚሰበስብ ጠቢብ ልጅ ነው፤ በመከር ጊዜ የሚተኛ ግን ውርደት ይከተለዋል።”
— ምሳሌ 10፥5 (አዲሱ መ.ት)
በተመሳሳይ
“ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤ ትጉ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ።”
— ምሳሌ 10፥4 (አዲሱ መ.ት)
2/ ለኑሮ መድከምና ንጹህ የልፋትን ዋጋ መመገብ በዚህ ደረጃ ከእግዚአብሔር ውዴታ ጋር በተቃርኖ የሚቀርብ ነው?ከንቱ ተደርጎ በፈጣሪ የሚናናቅስ ነው?
2/ እግዚአብሔርስ ቢሆን (በዘፍጥረት 3፥19) የሰው ልጅ በላቡ እንዲበላ ትዕዛዝ ማውረዱን ረስቶት ነው?ሰው በደነገገው መመሪያ መሠረት የሚያደርገውን ድካም እንደ ከንቱ የሚያየው?
ያቆየን!


