ነብዩ “ﷺ” የልጅ ልጃቸውን ብልት ስመዋል በሚል በግልቡ ለሚቀርበው ክስ የተሰጠ ማብራሪያ መግቢያ የኢንተርኔት አለም የክርስቲያን አቃቤዎች የገቡበት የምዕመን መሸሽ አጣብቂኝ በነብዩ ሙሐመድ “ﷺ” ስብእና ላይ ጥላሸት ይቀባልናል ብለው ያሰቡትን ማንኛውም ትርክት ከማምጣት ወደ ኃላ እንዳይሉ አድርጓቸዋል። በዚህ ረገድ ከሚጠቀሱ ትርክቶች ውስጥ ነብዩ “ﷺ” የልጅ ልጃቸውን ብልት ስመዋል በሚል የሚነሳው አንደኛው ነው። ዘገባው ሙሉ ለሙሉ…
Author: የሕያ ኢብኑ ኑህ
ለዕለት ጉርስ መጣር ከንቱ ነው!
ስራ መስራት አትወድም?በማለዳ ተነስተህ መጣርና መድከሙ አስመርሮሀል? እንግዲያውስ ለአንተ እግዚአብሔር መፍትሄ አለው፦ “የዕለት ጒርስ ለማግኘት በመጣር፣ ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤ እርሱ ለሚወዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።”— መዝሙር 127፥2 (አዲሱ መ.ት) እንደ መጽሀፍ ቅዱስ መሠረት ለምድራዊ ኑሮ መድከምህ “ከንቱ” ነው። እግዚአብሔር ቢወድህ ኑሮ እንቅልፍ ጥሎ ያስተኛህ ነበር። If it is said that it will be a…
እውን ቁርአን እርስ በርሱ ይጋጫልን? | ቀዳሚ ቃል
ቁርአን ከአምላካችን አላህ (سبحانه وتعالى ) የተሰጠን መለኮታዊ መፅሀፍ በመሆኑ በውስጡ ምንም አይነት የእርስበርስ ግጭት እንደሌለበት እኛ ሙስሊሞች እናምናለን። አንድ “መለኮታዊ” የተሰኘ መፅሀፍ ውስጡ ከእርስ በርስ መጣረስ የፀዳ ሊሆን እንደሚገባ ሁሉም ሰው ይጠብቃል። የእርስ በርስ ግጭት ስንል ከሀሳብ ግጭት ጀምሮ የቁጥር፣ የጊዜ፣ የቦታ ወዘተ ግጭቶችን ያካትታል። መነሻ ላይ የተናገረውን መድረሻ ላይ በተቃራኒ ቃል የሚያፈርስ መፅሀፍ አይደለም የአምላክ ቃል ሊሆን ይቅርና የአስተዋሽ ደራሲ ውጤትም ሊሆን አይችልም።
የኢየሱስ “መለኮታዊነትና” የዮሐንስ ወንጌል “ማስረጃ”
የኢየሱስን መለኮታዊነት አስመልክቶ በክርስቲያን ወገኖቻችን በኩል ለማስረጃነት ከሚያገለግሉ ጥቅሶች መካከል ከላይ የተጠቀሰው ዋነኛው ነው። በተለይም ለዘመናት “እየሱስ እኔ አምላክ ነኝ ካለ እንደዛ ያለበትን ቦታ አሳዩን” ለሚለው የሙስሊሞች ጥያቄ ያገለግላል በሚል ከሚቀርቡ “ማስረጃዎች” ይጠቀሳል። በዚህ ጽሁፍ ይህንን አንቀጽ በተመለከተ “እውን የኢየሱስን መለኮታዊነት ይገልፃልን?” በሚል መነሻ የተወሰኑ ሐሳቦችን በማስፈር ሙግቶቻችንን በማስረጃ ልንፈትሸው እንሞክራለን።
አደምን በአምሳያው ፈጥሮታል?
ይህንን ሀዲስ አስመልክቶ አንዳንድ ክርስቲያኖች የዘፍጥረቱን አንቀፅ በማሰብ “አደም በአላህ አምሳያ” ተፈጠረ ማለቱ እኛ የአምላክ ምስልንና ቅርፅን ይዘን መገኘታችንን ያሳያል ሲሉ ሊያቀርቡ ይሞክራሉ፡፡
የወንጌላውያን ወጥመዶች – 4
ከአመታት በፊት ጋዜጠኛ አብዱረሒም ቢቢኤን ሬዲዮ ላይ በሚሰራበት ወቅት አንድ ማንነቱ ከማይታወቅ ሰው ሚስጥራዊ ቪዲዮ ተላከለት። የዚህ ቪዲዮ ¹ ይዘት አስደንጋጭ ነበርና ይፋ ከማድረጉ በፊት የተወሰነ ቀን አሰበበት፥ ለሚቀርባቸውም ሰዎች አጋርቶት ተማከረበት። በስተመጨረሻም ይፋ አደረገው። ይፋ ከተደረገ በኃላ ብዙውን ሰው አስደነገጠ፣ መነጋገርያም ሆነ። ቪዲዮውን ለማስታወስ ያክል አንድ የሙስሊም አለባበስ የለበሰ ሰው የሆነ መጋዘን ውስጥ ለወንጌላውያን የሰጡትን ተልዕኮ እንዴት እየፈጸመ እንዳለ በዝርዝር የሚተነትንበት ነው።
ጅሀድ በትክክል ምንድን ነው?
“ጂሃድ” የሚለዉ ቃል ሲወሳ ብዙ ሰዎች በተለይም ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች አስፈሪ ምስል ይደቀንባቸዋል። ከተለያዩ የሚዲያ ምንጮች የሚያገኟቸው የተለያዩ መረጃዎች በዚህ አረዳዳቸው ላይ የራሳቸው ተፅእኖ አላቸው። እነዚህ ሰዎች ስለ ጂሃድ ሲያስቡ ምናልባትም ፊልም ላይ እንደሚያዩት ጺሙ የተንዥረገገ፣ፊቱ የተኮሳተረ፣ በቀኝ እጁ ቁርአን በግራ እጁ ሰይፍ የያዘ ሰዉ በአይነ ህሊናቸዉ ሊመጣባቸዉ ይችላል፡፡ ይህም ሰዉ ከፊት ለፊቱ ያገኘዉን ሁሉ “ትሰልማለህ ወይስ አትሰልምም” በማለት ይጠይቃል “ሰልሜያለዉ” ያለዉን ይተዋል “አልሰልምም” ያለዉን ግን “አሏሁ አክበር” በማለት አንገቱን በሰይፍ ይቀላል ወይም ደግሞ ቦንብ አንግቦ ሰላማዊ ህዝብ የተሰበሰበባቸዉን ቦታዎች በማጋየት ንፀሃንን ሲጨርስ ይታያቸዋል፡፡
ሙስሊሙን ማክፈር – የዘመናዊው አለም የሚሽነሪ እንቅስቃሴ
ወቅቱ በ1930 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠርር ነበር፤ የግብፁ አል-አዝሀር ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንግዳ ነገር ተሰማ። በሳሙኤል ዚውመር የተመራው የሚሽነሪ ቡድን ያለምንም ፍርሀት ቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ዘልቆ በመግባት የተለያዩ ፓምፍሌቶችንና ብሮሹሮቹን በተነ።በተግባሩ የአዝሀር ዑለሞች ተቆጡ፤ “ፈጽሞ አይደረግም” በሚል ሀሳብ ያንቀላፉት ሳይቀር ባለማመን ሰመመን ውስጥ ሁነው ድንጋጤ አላወሳቸው። የሁሉም ጥያቄ ግን “እነዚህ አካላት በዚህ ደረጃ እንዴት ደፈሩ?” “በርግጥ የዚህ ተግባር መንስኤ የነሱ ድፍረት ነው ወይንስ የኛ ድክመት?” የሚሉት ነበሩ









