(የሕያ ኢብኑ ኑህ)
“እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።”
— ዮሐንስ 13:13
◾️ መግቢያ
የኢየሱስን መለኮታዊነት አስመልክቶ በክርስቲያን ወገኖቻችን በኩል ለማስረጃነት ከሚያገለግሉ ጥቅሶች መካከል ከላይ የተጠቀሰው ዋነኛው ነው። በተለይም ለዘመናት “እየሱስ እኔ አምላክ ነኝ ካለ እንደዛ ያለበትን ቦታ አሳዩን” ለሚለው የሙስሊሞች ጥያቄ ያገለግላል በሚል ከሚቀርቡ “ማስረጃዎች” ይጠቀሳል። በዚህ ጽሁፍ ይህንን አንቀጽ በተመለከተ “እውን የኢየሱስን መለኮታዊነት ይገልፃልን?” በሚል መነሻ የተወሰኑ ሐሳቦችን በማስፈር ሙግቶቻቸውን በማስረጃ ልንፈትሸው እንሞክራለን።
◾️ ጌታ የሚለው ቃል ትርጓሜ
ጌታ የሚለው ቃል መሠረታዊ በሆነ መልኩ ለሁለት አይነት መጠሪያዎች አገልግሎት ላይ ውሏል። ይኸውም “አምላክ” ለሚለው ቃልና “መሪ” ወይንም “አለቃ” ለሚለው ትርጉም አገልግሎት ላይ ውሏል፦
The essential bible dictionary “Lord” የሚለውን ቃል ሲፈታው ከአምላክ ትርጓሜ በተጨማሪ አለቃ የሚል ፍችም እንዳለው ያስቀምጣል፦
lord – As a title of men, lord can mean simply “master” or “sir,” but it is
especially applied to governmental, religious, and military officials.
በተመሳሳይ Dictionary of bible types በገጽ 329 በተመሳሳይ ቃሉ ለመሪዎችና ለአለቆች አገልግሎት ላይ እንደሚውል ይገልጻሉ።
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል የተዘጋጀው የአማርኛ መዝገበ ቃላት በገጽ 519 ላይ “ጌታ” የሚለውን ሲፈታው፦
ከአምላክ በተጨማሪ “አለቃ” ወይንም “የበላይ” ለሚለው ትርጉም አገልግሎት ላይ ይውላል ሲል ይገልጸዋል።
◾️ ታዲያ እንዴት እንለያቸዋለን?
የመጽሀፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ሁለቱን ለመለየት የመጀመሪያው “ጌታ” የሚለውንና ኃያሉን አምላክ የሚጠቁመውን “ያህዌ” ሲተረጉሙ በካፒታል “LORD” አድርገው ሲሆን አለቃ የሚለውን ቃል በትርጉም የሚገልጸውን “አዶኒ” የሚለውን ቃል ሲተረጉሙ ደግሞ በስሞል ሌተር “Lord” ሲሉ አስቀምጠውታል። የዚህ ልዩነቱ ምንድን ነው? የሚለው ግን መሠረታዊ ጥያቄ ነው። ሁለቱም ቃላት “ጌታ” የሚል ትርጉም ቢኖራቸውም፤ በሚጠቁሙት ስልጣን በኩል ግን ሰፊ ልዩነትን የያዙ ናቸው። ሙሉ ለሙሉ ካፒታል ሌተር ያለው “ጌታ” የያህዌ ትርጉም ሲሆን ለአምላክ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውል ነው። በተቃራኒው በስሞል ሌተር የተቀመጠው “ጌታ” ደግሞ በተለያዩ ምህዳር ውስጥ ለሰዎች መሪ የሆኑ አልያም አለቃ የሆኑ የበላዮችን ለመጥራት አገልግሎት ላይ የሚውል ነው። የተወሰኑ ማስረጃዎችን ከዚህ በታች ለማስቀመጥ እንሞክር
◾️ ያህዌን በተመለከተ “LORD”
“እግዚአብሔር እርሱ አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኑን፣ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን ታውቁ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እንድታዩ ተደረገ።”
— ዘዳግም 4:35 (አዲሱ መ.ት)
“To you it was showed, that you might know that the LORD he is God; there is none else beside him.”
— Deu 4:35 (AKJV)
“እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው፤ ሕዝቦችም ከምድሩ ይጠፋሉ።”
— መዝሙር 10:16 (አዲሱ መ.ት)
“The LORD is King for ever and ever: the heathen are perished out of his land.”
— Ps 10:16 (AKJV)
ከላይ ያሉት ሁሉም እግዚአብሔርን ለመግለጽ አገልግሎት ላይ የዋሉ ናቸው። በስሞል ሌተር ሎርድ በሚል ጌታ ተብለው የተጠቀሱ ሌሎች ግለሰቦች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለመኖራቸው ደግሞ ከዚህ በታች የተወሰኑትን በማሳያ ለመመልከት እንሞክር፦
◾️ ዳዊት ጌታ ተብሏል
“ዮናታንም እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ነገሩ ከቶ እንዲህ አይደለም! ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አንግሦታል።”
— 1ኛ ነገሥት 1:43 (አዲሱ መ.ት)
“And Jonathan answered and said to Adonijah, Truly our lord king David has made Solomon king.”
— 1Kin 1:43 (AKJV)
◾️ ሙሴ ጌታ ተብሏል
“እንዲህም አሉ፤ “ምድሪቱን በዕጣ ከፋፍለህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ እንድትሰጣቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) አንተን ጌታዬን ባዘዘ ጊዜ የወንድማችንን የሰለጰዓድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዞሃል።”
— ዘኍልቁ 36:2 (አዲሱ መ.ት)
“And they said, The LORD commanded my lord to give the land for an inheritance by lot to the children of Israel: and my lord was commanded by the LORD to give the inheritance of Zelophehad our brother to his daughters.”
— Num 36:2 (AKJV)
◾️ ዮሴፍ ጌታ ተብሏል
“የጠፋው ዕቃ ከአገልጋዮችህ የተገኘበት ይሙት፤ የቀረነው የጌታችን ባሮች እንሁን።””
— ዘፍጥረት 44:9 (አዲሱ መ.ት)
“With whomsoever of your servants it be found, both let him die, and we also will be my lord’ slaves.”
— Gen 44:9 (AKJV)
◾️ ኢየሱስ “ነኝ” ያለው “ጌትነት” የቱን ጌትነት ነበር?
አሁን አንቀጹን በማስቀመጥ ኢየሱስ የትኛውን “ጌታ” የሚለውን አጠቃቀም ለራሱ እንደተጠቀመ ለማየት እንሞክር፦
“እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።”
— ዮሐንስ 13፥13
“You call me Master and Lord: and you say well; for so I am.”
— John 13:13 (AKJV)
አንቀጹ በግልጽ እንደሚነግረን እየሱስ እዚህ ላይ እነሱ “ጌታ” ብለው ጠርተውት እሱም “አዎን” ብሎ ያጸደቀላቸው ጌትነት “ያህዌ” የሚለውን የአምላክነትን መገለጫ ሳይሆን በስሞል ሌተር የሚቀመጠውን “አለቃ” ወይንም “መሪ” የሚለውን ጌትነት ነው። ይህ ደግሞ ቀደምት ነብያት በመጽሀፍ ቅዱስ የተጠቀሱበት የጌትነት መጠሪያ ነው። የሙሴ የአብርሃም፣ የዮሴፍ እና የዳዊትን አጠራር ለኢየሱስ መጠቀሙ በደረጃ በኩል ያለው ቦታ ከነሱ የተለየና ወደ መለኮት የተጠጋ አለመሆኑን በተቃሪኒው የሚጠቁም ነው።
የመጽሀፍ ቅዱስ ምሁራንም በዚህ ረገድ ያላቸው ትንታኔ “አምላክነቱን” በሚገልጽ መልኩ ሳይሆን የራቢ ወይንም መምህር ተቀያያሪ አቻ ትርጉም እንደሆነ ነው የሚገልጹት። ለአብነት Cambridge Bible for Schools and Colleges ማብራሪያ ብንመለከት እንዲህ ያስቀምጠዋል፦
- Master and Lord] Or, The Master (Teacher) and the Lord. These are the ordinary titles of respect paid to a Rabbi: ‘Lord’ is the correlative of ‘servant,’ so that ‘Master’ might be a synonym for that also; but the disciples would no doubt use the word with deeper meaning as their knowledge of their Master increased. In the next verse the order of the titles is reversed, to give emphasis to the one with this deeper meaning.
◾️ አምላክ ከፍጡራኑ አይበልጥም?
አንቀጹ ስለ አምላክ እንደማያወራ የሚጠቁመው እራሱ ኢየሱስና የተናገረበት አውድ ነወ። ወደ ታች ወረድ ብለን 16ኛው አንቀጽ ላይ ያለውን ጥቅስ ስንለመለከት እንዲህ ይላል፦
“እውነት እላችኋለሁ፤ አገልጋይ ከጌታው፣ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።”
— ዮሐንስ 13:16 (አዲሱ መ.ት)
ባሪያ ከጌታው ጋር የሚኖረውን ደረጃና መስተጋብር ሲገልጽ ስለየትኛው ጌትነት እያወራ እንደነበረ በግልጽ የሚጠቁመን ነው። ከላይ ጀምሮ እየተናገረ ያለው በዚህ ምድር ላይ ስላለው የባርያና የአሳዳሪ/ጌታ/የመደብ ልዩነት እንጅ በአምላክና በፍጡራኖቹ መካከል ስላለው የደረጃ ልዩነት አይደለም። እንዲያማ ቢሆን እግዚአብሔር ከሁሉም በላይ እንደመሆኑ መጠን “ጌታ ከባሪያው አይበልጥ” ብሎ ፈጣሪን ከፍጡራኖቹ ጋር ትህትናን አታኮ አያስተካክልም ነበር። በሉቃስ ወንጌል እንደተገለጸው ተማሪ ከመምህሩ ባይበልጥም ፈጽሞ ከተማረ ግን እንደ መምህሩ ይሆናል።
“ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ፈጽሞ የተማረ ሁሉ ግን እንደ መምህሩ ይሆናል።”
— ሉቃስ 6፥40
ይህ መተካከል በፍጡርና በፈጣሪ መሀል የለምና አውዱ ይህንን እንደማይገልጽ መናገር ይቻላል። መጽሀፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚናገረው አምላክ ከፍጡራኖቹ የበለጠና ልዕለሃያል ጌታ ነው።
“ከሁሉም በላይ የሆነ፣ በሁሉም የሚሠራ፣ በሁሉ የሚኖር የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።”
— ኤፌሶን 4:6 (አዲሱ መ.ት)
“እግዚአብሔር ታላቅ እንደሆነ፣ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና።”
— መዝሙር 135:5 (አዲሱ መ.ት)
◾️ የተረሳው ትህትና
የአስተምህሮቱ ዋነኛ ጭብጥ እየሱስ በደቀ መዛሙርቱ መካከል ትህትናን ማስተማር ነበር። እሱ “መምህራቸው” ወይንም “አለቃቸው” ሆኖ ዝቅ ብሎ አግራቸውን ካጠበ እነሱ ከዚህም በታች ትሁት መሆን እንዳለባቸው እየጠቆማቸው ነበር። ስለመምህርነቱና ስለጌትነቱም አዲስ መጠሪያ አምጥቶም አላስተዋወቃቸውም። መጀመሪያውኑ እነሱ ይጠሩት የነበረውን ቃል አንስቶ “እንዲህ ብላችሁኝ እኔም ዝቅ ካልኩኝ፣ እናንተ ይበልጥ ዝቅ ልትሉ ይገባል” የሚለውን እየጠቆማቸው ነበር። እዚህ ውስጥ ነገረ መለኮት የለም፣ የስነ ምግባር ትምህርት ግን ነበር። መምህሩ ከንግግሩ በተጨማሪ በተግባርም እያስተማራቸው ነበር። አምላክ በከፍታ ውስጥ የሚኖር እንጅ በዝቅታ ውስጥ የሚተናነስ አይደለም። ኢየሱስ ከአምላክ ባህሪያት ከብዙዎቹ እራሱን በማራቅ አዲስ ኪዳን ውስጥ ደጋግሞ እንዳሳየ ይህ በቂ ማሳያ ነው።
◾️ማጠቃለያ
ሲጠቃለል ኢየሱስ በንግግሩ የገለጸው “ጌትነት” አምላክነትን የሚጠቁም ሳይሆን አለቃነትንና መሪነትን የሚጠቁም ነው። ይህንን አንቀጽ ለኢየሱስ መለኮታዊነት ያግዛል በሚል ለሥላሴ ምሽግነት ማቅረብም መልዕክቱን መሳትና አውዱን ማዛባት ነው።
📌 ማጣቀሻዎች
- The essential bible dictionary
- Dictionary of bible types ገጽ 329
- በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል የተዘጋጀው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ 519
- Cambridge Bible for Schools and Colleges (Online Source)


