ወንድም ሳላህ
ሥላሴያውያን በ4ኛው ክፍለዘመን የቁስጥንጥንያ ጉባኤ ላይ በአብላጫው ድምፅ ከአምላክ ጋር እኩል ይሆን ዘንድ የተወሰነውን መንፈስ ቅዱስ ባይብላዊ መሠረት ለማስያዝ በርካታ ጥቅሶችን አዛብተው ሲያቀርቡ ይስተዋላሉ። መንፈስ ቅዱስ በትኛውም የብሉይም ሆነ የሐዲስ ኪዳን መፅሐፍ ላይ እራሱን የቻለ ኑባሬያዊ መለኮት መሆኑን አይናገርም። ይህን ስንል አብዛኛውን ጊዜ ሚሽነሪዎች የሚከተለውን ጥቅስ ለመንፈስ ቅዱስ ፈጣሪነት ለመጠቀም ይሞክራሉ። እስኪ እንፈትሸው:-
“የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።”
— ኢዮብ 33፥4
በዚህ አንቀጽ የእግዚአብሔር መንፈስ ተብሎ የተገለጸው እራሱን የቻለ አንድ ኑባሬ (Person) ሳይሆን የእግዚአብሔር ኃይል ነው። በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚባለው የእርሱ ጉልበት (ኃይል) እንጂ አካል ያለው የተለያ ማንነት አይደለም ፣ እስኪ ይህን ከራሱ ከኢዮብ መጽሐፍ እንመልከት:-
“እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ ገና ሳለ፥”
— ኢዮብ 27፥3
በዚህ አንቀጽ ላይ በአፍንጫዬ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር መንፈስ ብሎ ሲል እግዚአብሔር ወደ ግዑዛን ነገሮች “እፍፍፍ” ብሎ ሕያው የሚያደርግበት የሕይወት እስትንፋስ (ኃይሉ) መሆኑን በቀላሉ መረዳት እንችላለን። እስኪ በዚህ አንቀጽ ዙሪያ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት በማብራሪያቸው ያስቀመጡትን ትንታኔ ተመልክተን እንምጣ:-
‟And the spirit of God is in my nostrils – As long as I live. The “spirit of God” here means the breath that God breathed into man when he created him, Genesis 2:7”
ትርጉም:- በሕይወት እስካለሁ ድረስ የእግዚአብሔር መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ አለ ሲል እዚህ ጋር «የእግዚአብሔር መንፈስ» የተባለው በዘፍጥረት 2:7 ላይ ፈጣሪ አምላክ ሰውን ሲፈጥረው የነፋበት እስትንፋስ ነው።
(Barnes’ Notes on the Bible Commentary on job 27:3)
‟And the spirit of God is in my nostrils. The spirit of God, originally breathed into man’s nostrils, whereby he became a living soul (Genesis 2:7),
ትርጉም:- የእግዚአብሔር መንፈስ በአፍንጫዬ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ከጀምሩ ሕያው ያደርግ ዘንድ ወደ አፍንጫ የተነፋ እስትንፋስ ነው ዘፍጥረት 2:7።
(Pulpit Commentary Explanation of job 27:3)
ኢዮብ የእግዚአብሔር መንፈስ እያለ የሚጠራው የአምላክን ኃይል መሆኑን ከራሱ መፅሐፍ መረዳት ችለናል። ሌሎች ብዙ አንቀጾችን መጥቀስ እንችላለን ለአስተዋይ ሰው አንዱ ብቻ ከበቂ በላይ በመሆኑ ጹሑፍ ላለማንዛዘት እናልፋቸዋለን። እስኪ ስለ እግዚአብሔር መንፈስ የተለያዩ ምሁራንና መድብለ-እውቀቶች (Encyclopedias) የተናገሩትን እንመልከት:-
❝ብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔርን መንፈስ በፍፁም የተለያ አካል (ኑባሬ) አድርጎ አቅርቦት አያውቅም…የአምላክ መንፈስ ማለት በቀላሉ የአምላክ ኃይል ነው። አንዳንዴ (ከእግዚአብሔር) የተለያ ተደርጎ የሚገለጸው የያሕዌ እስትንፋስ በውጫዊ መልኩ ስለሚሰራ ነው። አብዛኞቹ የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊያን መንፈስን የሚገልጹት መንገድ እንደ “ነገር” እንጂ እንደ ተለያ “አካል” አይደለም።❞
(New Catholic Encyclopedia, 1967, Vol.13, page 574-5)
❝አይሁዳውያን መንፈስ ቅዱስን እንደ አካል (Person) በፍፁም አይቆጥሩትም፣ ወይም ደግሞ ከብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች ውስጥ ይህን አመለካከት ያለው ሰው መኖሩን የሚያሳይ አንድ ማስረጃ የለም። በሲኖፕቲክ ወንጌሎች ውስጥ አንዳንዴ መንፈስ ቅዱስ እንደ እግዚአብሔር ጉልበት ወይም እንደ ኃይል ተገልጿል። ምንም ያክል አንዳንዴ ጊዜ በግል አገላለጽ ቢገልጹትም እንደ አካል እንዳልቆጠሩት እሙን ነው።
(Edmund Fortman, The Triune God, pp. 6,15)
❝በአዲስ ኪዳን ውስጥ መንፈስ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ የሚሉት ቃላት ወደ 275 ጊዜ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል፤ ይሁን እንጂ ከእግዚአብሔር የተለያ አካል ተደርጎ አይደለም። በአይሁዳውያን እምነት መሠረት ‟የእግዚአብሔር መንፈስ” ማለት ያ አዳምን ሕያው ያደረገው፣ ነቢያትን የመራው የእግዚአብሔር እስትንፋስ (breath of God) ነው።❞
(Denova, R. (2021, May 03) Trinity World History Encyclopedia)
የቆስጠንጥንያው ኤጲስቆጶስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ (329 AD) ዛሬ በክርስቲያን ማህበረሰብ ዘንድ የሚመለከውን እርግብ በተመለከተ እንዲህ ብሎ ነበር:-
❝…ከገዛ ሊቃውንቶቻችን መካከል መንፈስ ቅዱስ “ብርቱ ሂደት” ነው ያሉ አሉ። ከፊሎቹ ደግሞ ፍጡር ነው ብለዋል፣ አንዳንዶቹ ደግሞ እንደ አምላክም ገልጸውታል። ሌሎች ደግሞ በነጥቡ ላይ ኖስቲክ ነበሩ። ቅዱሳት መጻሕፍት ሐፍት ውሰጥ ግን ከእነዚህ መካከል ለአንዱም ግልጽ የሆነ ራዕይ (መረጃ) የለም።”
(📗Gregory of Nazianzus, The Five Theological Orations and Two Letters to Cledonius, 117-47, 120 Chapter 5)
ልብ በሉ አበው ከሊቃውንቱ መካከል መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን የሚናገሩ ሰዎች መኖራቸውን ከገለጸ ቡኋለ ለዚህ ዕምነታቸው በቅዱሳት መፅሐፍ ውስጥ ምንም አይነት ግልጽ ማስረጃ እንዳሌላ በመናገር እውነታውን አስቀምጠዋል።
ስናጠቃልል:- ኢዮብ “የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ” ሲል የእግዚአብሔር ኃይል ሕያው አደረገኝ እያለ እንጂ በአይሁዳውያንም ሆነ በብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የማይታወቀው መንፈስ ቅዱስ ተብሎ የሚጠራው አካል ፈጠረኝ እያለ አይደለም። ኢዮብ በሌለ አንቀጽ የእግዚአብሔር መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ ነው ማለቱ ይህንኑ ያሳያል። ክርስቲያኖች ወገኖቼ ሆይ አምላክ ነው ያልተባለውን መንፈስ በግድ አምላክ ለማድረግ ከምትለፉ ለምን ወደ ቀጥተኛው መንገድ መጥታችሁ አንዱንና ብቻኛውን አምላክ አላህን አታመልኩም ? ፈጣሪዬ ልቦና ይስጣችሁ።
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


