የወንጌላውያን ወጥመድ -1
…
❝የፖለቲካ መሪዎችን ወይንም በማኅበረሰቡ ላይ ተጽእኖ የሚፈጥሩ አካላት ላይ ትኩረት ማድረግ❞
..
በሳውዘርላንድ ባፕቲስት ቲኦሎጂካል ሴሚናሪ ውስጥ የሚስዮን እና የወንጌል ስርጭት ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆነው ጆን ማርክ ሙስሊሞችን በወንጌል ስለመድረስ በጥልቀት ለመጻፍ ሞክሯል። እንደ ጆን ማርክ እሳቤ መሠረት ሚስዮናውያን ተርታው ህዝብ ላይ ትኩረት ከሚያደርጉ ይልቅ መሪዎችና የማኅበረሰቡ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ጋ ትኩረት ቢያደርጉ መልካም እንደሆነ ቅድሚያ ሰጥቶ ይመክራል። በዚህ ተግባራቸው በርካታ ፍሬዎችን ማግኘት እንደሚቻል ይነግራል፤ ከነዚህም ውስጥ፦
..
1/ ሰዎቹ ወንጌልን ከተቀበሉ እነሱን በማየት የሚመጣው ህዝብ በርካታ በመሆኑ በቀላሉ ስራቸውን ያቀልላቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ አካላት ህዝባቸው እነሱ የተቀበሉትን ትምህርት እንዲቀበል መምከራቸው ስለማይቀር ከዚህ በፊት በፈጠሩት ተቀባይነት ሳቢያ ብዙ ሰው በቀላሉ እንዲከተላቸው ያደርጋል።
..
2/ ይህ ደግሞ ሳይሳካ ቀርቶ መሪዎቹ ወንጌልን ባይቀበሉ እንኳን ከነሱ ጋ የሚፈጠረው ሰላማዊ ወዳጅነት ለሌላው ህዝብ ወንጌልን ለማድረስ እንቅፋት አስወጋጅ ነው። እነኝህ ሰዎች ጋ ጥሩ ወዳጅነት ከፈጠሩ ለሚሰሩት ስራ ተቃዋሚ እንዳይኖራቸው ያግዛል። ስለዚህም ሚሽነሪዎች በዋነኛነት ሲንቀሳቀሱ ቅድሚያ ሰጥተው የሚሰሩት የአካባቢው አስተዳደሮች ጋር በተለያዩ መንገዶች ትስስር መፍጠር ነው።
..
CONTEXTUALIZATION OF THE GOSPEL AMONG THE OROMO TRIBE OF THE EASTERN WOLLEGA REGION: THE MESERETE KRISTOS CHURCH EXPERIENCE በሚል ርዕስ ጥናታቸውን ያቀረቡት በድሩ ሁሴን የተባሉ የከፈሩ ወንጌላዊ ከላይ ያለውን ሀሳብ ያስረግጡልናል። በተለይም በኦሮሚያ ወለጋ አካባቢ የፕሮቴስታንት እምነት እንዲስፋፋ ይህ አጭር መንገድ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል።
..
N.B – ይህ ጉዳይ በመሪዎች ላይ ብቻ የሚገደብ አይደለም። በቤተሰብ በኩል እንኳን ቢሆን ብዙውን ጊዜ አባወራው ተጽእኖ ፈጣሪ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ትኩረት የሚደረገው እሱ ላይ ነው። የእሱ መቀየር የሌላው ቤተሰብ የመቀየርን እድል ከፍ ያደርገዋልና።
© የሕያ ኢብኑ ኑህ
https://t.me/+A9f1rDgYDRYzYTY0


