ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ከካፊሮች በኩል የተነሳ አንድ ስሞታ አንብቤ ነው፡፡ እሱም፡- በሙስሊሞች ዘንድ ስለጀነት ሲወሳ ሁሌም የሚያስቡት በውስጧ ሚስቶች መኖራቸውንና የስጋ ፍላጎትም እንደሚከናወንባት ብቻ አድርገው ማሰባቸው ነው፡፡ በርግጥ እነዚህን ሰዎች እስኪ በናንተ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ገነት ጸጋዎች ምን የተዘረዘረ ነገር አልለ? ብለን ብንጠይቃቸው ምንም መመለስ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም መጽሐፉ ይህን ነገር ከመዘርዘር ተቆጥቧልና!!፡፡ እነሱም መመሪያ መጽሐፋቸውን ተከትለው ዝም ማለት ሲገባቸው፡ ጭራሽ በማያውቁት በሌላ ዕምነት ውስጥ ገብተው መዘባረቅ ከጀመሩ የኛ ዝምታ እስከመቼ ነው? ቢያንስ እንኳ ምላሹን ለሙስሊም ወንድሞችና እህቶች በተጠየቁበት ጊዜ እንዲረዳቸው፡ በዛውም አላህ ልቡን የከፈተለት የሌላ ዕምነት ተከታይ ካለም ጉዳዩን በልበ-ሰፊነት እንዲመለከተው ለማገዝ ተዘጋጅቷል፡፡
Category: መሰረታዊ የእስልምና አስተምህሮ
እኔ እና እሱ “በቀደር ዙርያ የተደረገ ውይይት”
በኡስታዝ አቡ ሀይደር በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው እሱ፡- ቁርኣን የማን ቃል ነው? እኔ፡- ቁርኣን የአላህ ቃል ነው፡፡ እሱ፡- ምን ማስረጃ ይኖርሀል? እኔ፡- ቁርኣን ራሱ የአላህ ቃል መሆኑን ይናገራል!፡፡ እሱ፡- የቱ ጋር? እኔ በሱረቱ ተውባህ ምእ 9 ቁ 6 ላይ ‹‹ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው…
ተኝቼ ፈጅር ሶላት አመለጠኝ!
ሶላት በተግባር ከሚገለጹ የዒባዳህ (አምልኮ) ዘርፎች ውስጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሹ ነው፡፡ ከሶላት የሚበልጥ የዒባዳ ዘርፍ በኢስላም ውስጥ የለም፡፡ ሶላት በአላህና በባሪያው መካከል ያለ ብቸኛ የግንኙነት መስመር ነው፡፡ አንድ ሰው በሶላት ውስጥ ሆኖ ጌታውን ያወድሳል፣ ችግሩን በመግለጽ አላህን ይማጸናል፣ የኃጢአት ይቅርታን ይጠይቃል፣ የመጨረሻው ቤቱ እንዲስተካከል ዱዓእ ያደርጋል…፡፡ በቃ ሶላት ለሙስሊም ሁሉ ነገሩ ነው፡፡ ከዱንያ ጭንቆች፣ ከስራ ድካም ሁሉ የሚያርፈው ሶላት ውስጥ ሲገባ ነው፡፡
“ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” | ክፍል -9
ባለፈው ክፍል ስምንት ላይ በቁጥር ሦስት ስር የነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተልእኮ በተመለከተ፡ የተላኩት ለመላው የሰው ዘር መሆኑን በሰፊው ተመልክተናል፡፡ ዛሬ የምንመለከተው ደግሞ፡ እሳቸው ከነቢያትና ከመልክተኞች የመጨረሻና መደምደሚያ መሆናቸውን ነው፡፡ ከሳቸው በኋላ የሚነሳ የአላህ ነቢይም ሆነ መልክተኛ የለም፡፡ የሚወርድ መለኮታዊ መጽሐፍም የለም፡፡ ነቢይነት በሳቸው እንደተደመደመው ሁሉ፡ መለኮታዊ መጻሕፍትም በቅዱስ ቁርኣን ተደምድመዋል፡፡ ይህን አቋም በተመለከተ የሚናገሩ ቁርኣዊና ነቢያዊ ሐዲሦችን እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-
“ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” | ክፍል -8
በቁጥር አንድ ትምሕርታችን ላይ ስለ ነቢይነታቸው በቀደምት ነቢያት፣ መለኮታዊ መጽሐፍትና ሊቃውንት አንደበት የተነገረ ትንቢት በሚለው ስር፡ ለሶስት ተከታታይ ክፍሎች የተነገረላቸውን ትንቢት አይተናል፡፡
“ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” | ክፍል -7
አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ፡- “ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘውራዕ በተባለው ስፍራ ከባልደረቦቻቸው ጋር እያሉ ውሃ መያዣ እቃ መጣላቸው እጃቸውንም በእቃው ላይ አስቀመጡና አነሱት ከዚያም ከጣታቸው መካከል ውሃ መፍለቅ ጀመረ፡፡ ህዝቦቹም ውዱእ አደረጉ” ቀታደታ የተባለው ሰው (ረሒመሁላህ) አነስ ኢብኑ ማሊክን (ረዲየላሁ ዐንሁ) (በወቅቱ ከጣታቸው ይፈልቅ በነበረው ውሀ ለዉዱእ የተጠቀማችሁት) ስንት ነበራችሁ? ብሎ ጠየቀው፡፡ አነስም ‹‹ሶስት መቶ ነበርን›› አለ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት)፡፡
“ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” | ክፍል -6
ለነቢይነታቸው ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸው ማስረጃ
“ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” | ክፍል -5
በክፍል አራት ላይ የነቢዩ ሙሐመድን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይነት ሊያረጋግጡ ከሚችሉ ማስረጃዎች ሁለቱን ተመልክተን ነበር፡፡ እነሱም፡- የጌታ አላህ ምስክርነት እና የቁርኣን ተአምርነት ማለት ነው፡፡ ከዛ የቀጠለውን ማስረጃችንን ዛሬ እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-
“ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” | ክፍል -4
በቁጥር አንድ ትምሕርታችን ስለ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይነት በቀደምት ነቢያት፣ መለኮታዊ መጽሐፍትና በመጽሐፍቱ ሊቃውንት አንደበት የተነገረ ትንቢት በሚለው ስር ለሶስት ተከታታይ ክፍሎች መረጃዎቹን ስንማር ቆይተናል አልሐምዱ ሊላህ፡፡
“ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” | ክፍል -3
ከዚህ በፊት ስለ ረሱላችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይ ሆኖ መነሳት የተነገረ ትንቢት በሚለው ስር፡ ሁለተኛውን ነጥብ፡ ቀደምት መለኮታዊ መጽሀፍት ስለ እሳቸው ነቢይነት መናገራቸውን ተመልክተናል፡፡ ዛሬም የጌታችን አላህ ፈቃድ ከሆነ ሶሥተኛውን ክፍል፡ ማለትም የመጽሀፉ ባለቤቶች የሆኑት (የአይሁድና የክርስቲያን) ሊቃውንት የሳቸውን ነቢይነት በሚገባ ያውቁ እንደነበር እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-











