ከዕለታት በአንዱ ቀን ተማሪው መምህሩ ፊት ቆመና፡- ክቡር መምህር ሆይ! አንዳንዴ እንግዳ አስተሳሰብ በህሊናዬ ብቅ ይላልና፡ መፍትሔ ካገኘሁ በማለት ለእርስዎ ማቅረብን ወደድሁ፡፡ እሱም፡- አምላካችን አላህ ለተወሰኑ ሕዝቦች ሰዓዳህ (ዘላለማዊ ደስታን) ለተቀሩት ደግሞ ‹ሸቃዋህ› (ዘላለማዊ ስቃይን) ለምን ወሰነ? ለምን ዘላለማዊ ደስታን (የጀነት መሆንን) ብቻ አላደረገም?
Category: መሰረታዊ የእስልምና አስተምህሮ
ልፋት ለምኔ? | ክፍል ስምንት
ስለ አላህ ማንነት መጠነኛ ግንዛቤ ያለው ሙስሊም ‹‹አላህ የፈለገውን ያጠማል፣ የፈለገውን ደግሞ ያቀናል›› የሚለው ሀሳብ ከእምነት አንጻር ምንም ችግርና ግራ የመጋባት ስሜት አይፈጥርበትም፡፡ ምክንያቱም ‹ፈቃድ› ሁሉ የአላህ እንደሆነ ስላወቀና ስላመነ!፡፡ ከሱ የሚጠበቀው፡ አቅሙ በቻለው መጠን የጌታውን ትእዛዝ በመፈጸምና ከከለከለው ነገር ለመራቅ እየታገለ የአላህን እገዛ መሻት፣ በኃጢአቱ ሰበብ ደግሞ የራሕመት በሩን ዘግቶበት እንዳያጠመው መፍራትና መጠንቀቅ፣ ኃጢአት ላይ ከወደቀም ቶሎ በተውበት መነሳት እንጂ፡ እንዴት እሱ የፈለገውን ያጠማል? ብሎ በመለኮታዊ አሰራሩ ጣልቃ በመግባት፡ የተቃውሞ ጥያቄ ማቅረብ አይደለምና፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
ልፋት ለምኔ? | ክፍል ሰባት
ባለፈው በክፍል ስድስት ላይ ‹‹አላህ የፈለገውን ይመራል፣ የፈለገውን ደግሞ ያጠማል›› የሚለውን አምላካዊ ቃል አንስተን፡ በዚህ ሀሳብ ዙሪያ የሚነሳውን የፍትሕ ጥያቄ ከነመልሱ ለማየት ሞክረናል፡፡ ይህ ሀሳብ ጥቅላዊ እንደመሆኑ መጠን፡ ሀሳቡን የሚያብራሩና የሚገልጹ ሌሎች የቁርኣን ክፍሎችን በማንሳት፡ ለጥመት የሚዳረጉ ሰዎችንና ለምሪት የሚዳረጉትን አይተናል፡፡ ከጥቅል ሀሳብ ብቻ ተነስተን ‹‹አላህ የፈለገውን ይመራል፣ የፈለገውን ደግሞ ያጠማል›› የሚለውን መተንተን ስህተት ላይ እንደሚጥለንና፡ የግድ በሌላ ቦታ ከተነገሩ ዝርዝር ሀሳቦች ጋር ማስማማትና ማገናኘት እንዳለብን ተመልክተናል፡፡ በዝርዝር ሀሳቦቹም ላይ ሰዎችን ለጥመት ወይም ለምሪት የሚዳርጋቸው ምን ምን እንደሆነ የተወሰኑ ማስረጃዎችን ተመልክተናል፡፡ ዛሬ ደግሞ ከጥያቄው ሳንወጣ ሌላኛውን የመልስ አይነት በአላህ ፈቃድ እንመለከተዋለን ኢንሻአላህ፡፡
ልፋት ለምኔ? | ክፍል ስድስት
በዚህ ሀሳብ ዙሪያ የሚናገሩ የቁርኣን ክፍሎች ብዙ ናቸው፡፡ መልእክታቸውን በመረዳት ዙሪያ ግን መስመር የሚስት አልለ (አላህ ያሳወቀው ሲቀር)፡፡ አንዳንድ ሰውም የፍትሕ ጥያቄ ያነሳል፡፡ እንዲህ ሲልም የተቃውሞ ጥያቄ የቀርባል፡- የሂዳያ ነገር ‹አላህ ካልሻ በስተቀር› በሚለው ሀሳብ በሩ የተዘጋና የተቆለፈ ሁኖ እያለ፡ እንዴት የሂዳያውን መንገድ ማግኘት ይቻላል? አንድ ሰው አላህ ልቡን ካሸገውና በአይኑ ላይ መጋረጃን ካደረገበት እንዴት የሐቅን መንገድ ማግኘት ይችላል? የሚል፡፡
ልፋት ለምኔ? | ክፍል አምስት
ሰው ነጻ ፈቃድ አለው ማለት፡ ያለምንም ተቆጣጣሪ የፈለገውን ነገር ይተገብራል፡ ፈላጭ ቆራጭ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ያ ቢሆን ኖሮ የሰማይና የምድር ስርአት በተበላሸ ነበር፡፡ ነገር ግን ጥበበኛው አላህ ሰውን ከፈጠረው በኋላ፡ ነጻ ፈቃድ የሚባልን ነገር ሰጥቶ በልቅ አልተወውም፡፡ ይቆጣጠረዋል፡፡ እሱ አላህ የፈለገውን ነገር እንዲሳካለት ይፈቅዳል፡፡ ያልፈለገለትን ደግሞ እውን እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ ጥበቡ የሱ ብቻ ነውና የሚል ነው፡፡ ዛሬ የምናየው የዚህን ሀሳብ ቀጣይ ክፍል ሆኖ፡ ቀደምት ነቢያትና (ዐለይሂሙ-ሰላም) አማኞችም በጉዳዩ ላይ ምን አይነት እምነት እንደነበራቸው የተወሰኑትን ለናሙና በመጥቀስ ይሆናል ኢንሻአላህ፡፡ መልካም ንባብ!
ልፋት ለምኔ? | ክፍል አራት
በዛሬው ክፍላችን በአላህ ፈቃድ የምንመለከተው፡ ባለፈው ክፍል ላይ ያነሳነውን ጥያቄ ነው፡፡ እሱም፡- ሰው የሚባለው ፍጥረት ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር መሆኑን ከተስማማን፣ ደግሞም በፈቃዱ መልካምም ይሁን መጥፎ ስራዎችን መስራት ከቻለና፡ በነዚህም ስራዎቹ ኃላፊነትን ወስዶ በየውሙል ቂያም በአላህ ዘንድ ተጠያቂ ከሆነ፣ እንዲሁም ቀዷ ወል-ቀደር የሚባል ነገር በእምታችን ውስጥ ካለና፡ በዚህ ማመናችንም የአላህን ሁሉን አዋቂነት፡ የፍጥረተ ዓለሙን የበላይ ተቆጣጣሪነትና ገዢነት፡ እንዲሁም ከሱ ፈቃድና ይሁንታ ውጪ ሊከሰት የሚችል ነገር አለመኖሩን የሚጠቁም እንጂ፡ የሰዎችን ነጻ ፈቃድ የሚጋፋና ትርጉም አልባ የሚያደርግ አለመሆኑን ከተረዳን፣ ታዲያ ‹‹አላህ ካልሻላችሁ በስተቀር እናንተ አትሹም›› የሚለውን እንዴት ነው መረዳት ያለብን? የሚል ነበር፡፡ በአላህ ፈቃድ ምላሹን ይከታተሉ፡፡ አላህ ኸይሩን የተሻለውን ግንዛቤ ይለግሰን፡-
ልፋት ለምኔ? | ክፍል ሶስት
ለዛሬ ባሸጋገርነው ጥያቄ ደግሞ፡- እንግዲያውስ ሰው ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር ከሆነ፡ የፈለገውን ነገር ሁሉ በራሱ ፈቃድ ብቻ ነው የሚያከናውነው ማለት ነውን? የሚለውን ጥያቄ አንስተን፡ ምላሹን በቀጣዩ ተባብለን ነበር፡፡ ዛሬ ላይ በአላህ ፈቃድ ደርሰናልና አልሐምዱ ሊላህ፡፡ ምላሹን ይከታተሉ፡-
ልፋት ለምኔ? | ክፍል ሁለት
ቀዷ ወል-ቀደር ማለት፡- በዚህ ዓለም ላይ የሚከሰት ማንኛውም ክስተት ጥሩም ሆነ መጥፎ፡ ከሰውም ይገኝ ከእንሰሳት፣ ከመላእክትም ይገኝ ከጂንኒዎች፣ ከበራሪዎችም ይሁን ከነፍሳት፣ በፈቃድና በምርጫም የተገኘ ይሁን በግዳጅ፡ ጉዳዩ አስቀድሞ አላህ ዘንድ የታወቀ፡ በለውሐል መሕፉዝ (ጥብቅ ሰሌዳ) ላይ ተወስኖ የተጻፈ፡ በአላህ ፈቃድና ይሁንታ የተከናወነ ነው ብሎ ማመን ማለት ነው፡፡
ልፋት ለምኔ? | ክፍል አንድ
አንድም ትክክለኛውን የቀዷ ወል-ቀደር ጽንሰ-ሀሳብ ባለመገንዘብ፡ አልያም ራስ ግራ ተጋብቶ ሌላውንም ግራ ለማጋባት በተደጋጋሚ የሚነሳ ጥያቄ አልለ፡፡ እሱም፡- እኛ የምንሰራው ስራ በጠቅላላ አስቀድሞ የታወቀ፣ የተጻፈና የተወሰነ ከሆነ ለምን እንለፋለን ታዲያ? ደግሞስ የኛ ነጻ-ፈቃድ ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው? በመጨረሻው ቀንስ ጌታችን ለምን ይተሳሰበናል? የሚል ነው፡፡ ለነዚህ ጥያቄዎች በአላህ ፈቃድ የቻልኩትን ያህል ምላሹን ለማብራራት እሞክራለሁ ኢንሻአላህ፡-
“አል-ሐምዱ ሊላህ” ማለትን እናብዛ!
“አል-ሐምዱ ሊላህ” ማለት፡- ፍጹም የኾነ ልባዊ ምሥጋና ለአላህ ብቻ የተገባ ነው ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህን ስናመሰግነው በሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛ፡- በማንነቱ ፍጹም የኾነ የምሉእ ባሕሪያት ባለቤት በመኾኑ፣ እንከንና ጉድለት ፈጽሞ የሌለበት በመኾኑ ብቻ ይመሰገናል፡፡ ከፍጡራን ምሥጋና በፊትም እራሱን ያመሰገነና ያወደሰ አምላክ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ፡- ክፍያንና ወሮታን ሳይጠይቅ ለባሪያዎቹ የሚለግስ ደግ አምላክ በመኾኑ፣ ለለመኑትና ለተማጸኑት ደግሞ ፈጥኖ ደራሽ በመኾኑ ስለ-ጸጋዎቹ ይመሰገናል፡፡ አላህ በራሱ በማንነቱም ኾነ በጸጋዎቹ የሚመሰገን ጌታ ነውና፡፡











