ጋብቻ የጌታ አላህ ትእዛዝ፣ የነቢያት ሱንና እና የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሕይወት ፈለግ ነው፡፡ አላህ ትዳር የሌላቸውን ሰዎች እንድናጋባቸው ትእዛዝን ሰጥቷል፡፡ ለጊዜው ችግረኞች ቢኾኑ፡ ከሱ በኾነ ቸርነት እንደሚያብቃቃቸውም ቃልን ገብቶላቸዋል፡፡ ቀደምት ነቢያትንም በትዳር እንዲጣመሩ በማድረግ የነቢያት ሱንና መኾኑንንም አበክሮ ነግሮናል፡፡
Category: መሰረታዊ የእስልምና አስተምህሮ
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -29
እስካሁን በቆየንባቸው ሃያ ዘጠኝ ክፍሎች ውስጥ ስለ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” መሰረታዊ የሆኑ ዘጠኝ ነገሮችን በመጠኑ ተመልክተናል አልሐምዱ ሊላህ፡፡ ለዛሬ ማጠቃለያ እንዲሆነን ስለ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” የሚናገሩ የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾችን በመጠኑም ቢሆን በተወሰነ መልኩ ከፍለን እንመለከታቸዋለን፡፡
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -28
ከ‹‹ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ›› አንዱና ዋነኛ ጥቅሞች ውስጥ ባለቤቱን ለጀነት ማብቃቱ ነው፡፡ የዚህ እምነት ባለቤቶች በዚሁ ‹‹ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ›› ጸንተው ከሞቱና በተለይ የመጨረሻ ቃላቸው በ‹‹ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ›› ከተዘጋ የጀነት ይሆናሉ፡፡ አላህ ይወፍቀን፡-
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -27
ዑለማእ (የሃይማኖት ሊቃውንት) የነቢያት ወራሽ ናቸው (አቡ ዳዉድ፣ ኢብኑ ማጀህ)፡፡ ከአማኞች መካከልም አላህን በእጅጉ ፈሪዎች ናቸው (ፋጢር 28)፡፡ አላህ ዘንድም በክብርና በደረጃ የላቁ ናቸው (አል-ሙጃዲላህ 11)፡፡ ይህ ሁሉ የትክክለኛ ሊቃውንት (ለሐቅ የቆሙት) ባሕሪ ነው፡፡
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -26
ባለፈው ለሺርክና ለኩፍር መስፋፋት ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱና ዋነኛው ‹‹የዕውቀት ማነስ››ን አንስተን ተነጋግረን ነበር፡፡ ሌላው ምክንያት ደግሞ በሷሊሖች (ደጋግ የአላህ ባሮች) ላይ ወሰን ማለፍ ነው፡፡ አላህ ከፍጥረታቱ መሐል የሰውን ልጅ አክብሮታል (አል-ኢስራእ 70)፡፡ ከሰዎች ውስጥ ደግሞ ‹‹ሷሊሖች›› የተሻለ ደረጃ አላቸው (አል-ሙጃዲላህ 11)፡፡ ከሷሊሖች ደግሞ ‹‹ነቢያት›› የላቁና የበለጡ ናቸው፡፡ ከነቢያት መካከል ‹‹ሩሱሎችን›› በደረጃ ከፍ አደረጋቸው፡፡
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል- 25
በቁጥር ሰባት ስር ለተከታታይ ጊዜያት የ‹‹ላ ኢላሀ ኢልለሏህ››ን እምነት አፍራሽ የሆኑ ተግባራትን (ሺርክ፣ ኩፍር፣ ኒፋቅ) ስንመለከት ቆይተናል፡፡ ዛሬ ደግሞ በሰዎች መሐል የ ‹‹ሺርክ›› እና የ ‹‹ኩፍር›› ስራዎች እንዲስፋፉ ምክንያት ከሆኑ ነገሮች የተወሰኑትን እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -24
ስራውና ተግባሩ የመናፍቃን ሆኖ፡ ባለቤቱን ከኢስላም የማያስወጣው፡ ነገር ግን በኃጢአት የሚያስከስስ ተግባር የሆነው ‹‹ኒፋቁን ዐመሊይ›› (በስራ የሚታይ መናፍቅነት) ይሰኛል፡፡ የዚህ ባሕሪ ባለቤት በልቡ ክህደትን አልያዘም፡፡ ውስጡ አማኝ ነው፡፡ ሆኖም ከኢማኑ ድክመት የተነሳ በንግግሩና በተግባሩ ከፊል የመናፍቃን ባሕሪ ይታይበታል፡፡ ያም ኃጢአተኛ ያደርገዋል እንጂ ከኢስላም አጥር አያስወጣውም፡፡ እነዚህን ባሕሪያት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በአንድ ሐዲሥ ጠቅለል አድርገው እንዲህ ይገልጹታል፡-
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -23
ሌላኛው የ”ላ ኢላሀ ኢልለሏህ”ን እምነት ከሚያፈርሱት ውስጥ አንዱ ‹‹ኒፋቅ›› ነው፡፡ ሙናፊቅ ማለት ቀጥታ ፍቺው፡- አስመሳይ ማለት ነው፡፡ ያም ማለት፡- ከውጭ ኢስላማዊ ገጽታን እያሳዩ በልብ ክህደትን አምቆ መያዝ ማለት ነው፡፡ ውጪያዊ ተግባሩ የሙስሊሞች አይነት ሆኖ፡ ልቡ ግን ከከሀዲያን ጋር ያደረ ማለት ነው፡፡ ሙናፊቅ፡ ከሙሽሪክና ከካፊር የበለጠ የሙስሊሞች ጠላትና አደጋ ነው፡፡ ምክንያቱም፡- ካፊሮችና ሙሽሪኮች ጠላትነታቸው በይፋ የሚታይ በመሆኑ ለመጠንቀቅ ይረዳል፡፡ ሙናፊቅ ግን የልቡን በልቡ ይዞ በውጪያዊ ማንነቱ ካንተ ጋር ተመሳስሎ የሚውል በመሆኑ መለየት አይቻልም፡፡ ወንድም መስሎ በመቅረብ ሚስጥርን በማውጣት ለጠላት አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ቅዱስ ቁርኣን በሱረቱል በቀራህ መግቢያ ላይ ከ2-20 ባለው 19 አንቀጽ ውስጥ፡ ስለ ሙእሚኖች 4፣ ስለ ካፊሮች 2፣ ስለ ሙናፊቆች ደግሞ 13 አንቀጾችን አውርዷል፡፡ ይህም የሚያሳየው፡- ሙናፊቆች ለኢስላም ምን ያህል ጠንቅ እንደሆኑ ነው፡፡
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -22
ንግግሩና ተግባሩ ‹‹ኩፍር›› የሚል ስያሜ የሚሰጠው ሆኖ፡ ነገር ግን ባለቤቱን ከኢስላም አጥር የማያስወጣው፡ ስራን ሁሉ የማያበላሸው፡ ነገር ግን ለአላህ ቅጣትና ዛቻ አሳልፎ የሚሰጠው ተግባር ትንሹ ኩፍር ‹‹ኩፍሩን አስገር›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ለምሳሌ ያህል ፡-
የኢስላም መልእክት “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” | ክፍል -21
በጥርጣሬና በመዋለል፡- ደግሞም እንዲህ አይነት ሰው አለ፡፡ ወይ በያዘው እምነት ተረጋግቶ ቀጥ አይል፡፡ ወይ የለየለት ከሀዲ አይሆን!:: ነገር ግን በዚህ መሀል በጥርጣሬ ይመላለሳል፡፡ ይሄ ነገር እውነት ይሆን ወይስ ሀሰት? እያለ እራሱን ይጠይቃል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰው ካፊር ተብሎ ይጠራል፡፡ ምክንያቱም አላህ ከባሪያዎቹ በእምነታቸው እርግጠኝነትን እንጂ ጥርጣሬን አይፈልግም፡፡ እርግጠኝነት የአማኞች ባሕሪ ነው (ሱረቱል በቀራህ 4፣ አል ሑጁራት 15)፡፡ መጠራጠር ደግሞ የከሀዲያንና የመናፍቃን ባሕሪ ነው፡፡ ስለዚህ በእምነት ጉዳይ እርግጠኝነት እንጂ ጥርጣሬ ተቀባይነት የለውም፡-











