..
ይህ ነገር በኦሮሚያ ብቻ አይደለም የሚገጥመው። ሌላ ቦታም በተለይም ሙስሊሙ በብዛት የሚኖርባቸው አካባቢዎች መሠል ነገር ገጥሞን ከአካባቢው ተወላጆች ጋር ስናወራ ጉዳዩን አለመስማታቸው እጅጉኑ ያስገርማቸዋል። እዚህ ጋ መዘንጋት የሌለብን ትልቅ ቁምነገር አለ። ህዝባችንን በተለይም የገጠሩን ህዝብ የሚያከፍሩት በድብቅ አይደለም። በስርአቱ ቪዲዮ እየቀረጹና አልፎ ተርፎም በቴሌቭዥናቸው እያሰራጩ ጭምር ነው። ሌላው አካባቢ ሞራል እንዲያገኝ ስራቸውን በአደባባይ ነው የሚገልጹት።
..
በቀላሉ ያለማወቃችን ምክንያት ምንድን ነው ከተባለ በዋናነት ሁለት ምክንያቶች ናቸው። አንደኛው ምክንያት ለችግሩ ትኩረት የምንሰጠው ቤታችን ሲገባ ብቻ በመሆኑ ነው። ከተወሰነ ጊዜ በፊት “እኛ አካባቢ የሚሽነሪ ስጋት የለም” ብሎ የተከራከረኝ አንድ ወንድም ከሆነ ጊዜ በኃላ የባለቤቱ ዘመዶች ከፍረውበት በግራ መጋባት አማክሮኝ ያውቃል። ይህኛው አንደኛው ችግራችን ነው። ሁለተኛው ችግር ትኩረታችን በአብዛኛው ሌላ ቦታ ላይ ነው። ወይ ፖለቲካው ነው አልያም የዱንያ ሀጃ ነው። በዚህ ሳቢያ ዱኑን በተመለከተ በዙሪያችን እየተከናወኑ ያሉ ነገሮች ብዙም አይታዩንም።
..
በአሁኑ ሰአት አልሐምዱሊላህ በከተማ አካባቢ እስልምናን የሚቀበለው ሰው ከምንጊዜውም በላይ የጨመረበት ሰአት ላይ ነን። ያም ሆኖ አብዛኛው ህዝባችን የሚገኝበት የገጠሩ አካባቢ ግን የሚገባውን ትኩረት ባለማግኘቱ ከመክፈር አደጋ መዳን አልቻለም። ይህ ተግባር በጥቂት ሰዎች አልያም ተቋም ላይ ብቻ የሚንጠለጠል ኃላፊነት አይደለም። የሁላችንንም ትኩረት የሚፈልግና በርብርብ ደረጃ ደግሞ የተቀናጀ ትብብር የሚያስፈልገው ስራ ነው። ህዝባችንን ታች ወርደን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። የገጠሩ ህዝባችን የኛ ኺላፍ ጉዳዮች አይደሉም ቢዚ እያደረጉት ያለው። ከነ አካቴው እስልምናውን ነው እያጣ ያለው። ይህ ደግሞ ቀላል ነገር አይደለም። አሁንም ቢሆን ችግሩን አጢኖ የሚንቀሳቀስ አካል ካለ ግን ጊዜው አልረፈደም..!
T.me/Yahya5
© የሕያ ኢብኑ ኑህ





