የሕያ ኢብኑ ኑህ
ለንግስናው ሲል ተከታዮቹ የተቃወሙትን ያርዱ ዘንድ ያዘዘ ፖለቲከኛ ያልሆነ ግለሰብ ምናልባት ኢየሱስ ብቻ ሊሆን ይችላል። ሰዎች ለተለያየ አላማ ሊዋጉ አልያም ሊጋደሉ ይችላሉ። ራሳቸውን ለመከላከል፣ አስተሳሰባቸውን ለማስረፅ፣ መደመጥን በመሻት ወዘተ የሰው ልጅ ሊታገልና ሊጋደል ይችላል። ሁሉም አላማ ተከታይ ከመኖሩ ጋር ሊያከራክር ይችላል። ነገር ግን በግልፅ “እኔ እንድነግስ ዘንድ ሙቱልኝ፤ ያልተቀበሉትንም ግደሏቸው” ብሎ በግልፅ ቋንቋ በአደባባይ ተናግሮ ንግግሩም “ቅዱስ” የተባለለት ሰው ለኔ ከኢየሱስ ውጭ ያለ አይመስለኝም።
“ነገር ግን እነዚያን #በላያቸው #ልነግሥ #ያልወደዱትን #ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው #በፊቴም #እረዱአቸው።”
— ሉቃስ 19፥27
እዚህ አንቀጽ ውስጥ የኢየሱስ አስገራሚው የ “ግደሉልኝ” ንግግር ብቻ አይደለም ያለው፤ ከዚያም በተረፈ ብዙ አስተምህሮቶቹን የሚያፋልሱ ቃላት ተከምረውበታል። ጠላትክን እንደ ራስህ ውደድ ብሎ ያስተማረው ኢየሱስ ለሱ ሲሆን ግን ጠላቶቹ መታረድ እንዳለባቸው ንግግሩ ከቃሉ በተቃረነ መልኩ አስተማረ። ኢየሱስ መገደላቸው ብቻ አላረካውም በፊቱ አምጥተው እንዲገደሉም ነበር የነገራቸው። ደማቸውን ማየት ሁሉ ፈልጎ ይሆናል፤ ምናልባትም “ገድለናቸዋል” ብለው ተከታዮቹ ሳይገድሉ በመቅረት እንዳያታልሉትም ሰግቶ ይሆናል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ሀ/ማርያም እንዲገደሉ ያዘዟቸውን ወይንም የግድያ ትዕዛዝ የተላለፈባቸውን ሰዎች ከተገደሉ በኃላም ቢሆን ፊታቸውን አቅርበው ያዩ እንደነበሩ የአባታቸው ጀኔራል ጌታቸው ናደውን ምሳሌ አድርገው ሻለቃ ጳውሎስ ጌታቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ። ትክክለኛውም ምክንያቱን እራሱ ኢየሱስ ያቃል፤ ግን አንድ በእርግጠኝነት ያወቅነው ነገር የሚገደሉ ሰዎች ከፊቱ እንዲታረዱ ይፈለግ እንደነበር ነው።
.
መጽሀፍ ቅዱስ በመሠል የኮሚንስቶች ዘመን የሰማናቸው ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችና የግድያ ትዕዛዛትን በውስጡ አቅፎ የያዘ መጽሀፍ ነው። ይህ ተግባር በብሉይ ኪዳን በነበረው እግዚአብሔር ዘንድ ብቻ የተተው አልነበረም። ራሱን ለወጥ አድርጎ መጥቷል ተብሎ ከሚታሰበው የአዲስ ኪዳኑ አምላክ ዘንድም ቢሆን ግን እነኝህ አይነት የቆዩ ልማዶቹ አልተውትም ነበር።


