የሕያ ኢብኑ ኑህ
በግብፅ ከ1925-1935 ባሉ ጊዜያት ውስጥ የነበረትን የሚሽነሪ እንቅስቃሴዎች መሠረት በማድረግ በዑመር ሪያድ የተሰራው ጥናታዊ ወረቀት እንደሚገልፀው በግብፅ ምድር ብቻ በ1930 ዓ.ል 450 የሚሆኑ የውጭ ሀገር ዜጋ ሚሽነሪዎች የነበሩ ሲሆን 1500 የሚሆኑ ደግሞ ግብፃዊ ሰራተኞች ነበሩ። አመታዊ በጀታቸውም $700,000 ዶላር ነበር። ከምንም በላይ የሚያስደንቀው ግን ለአላማቸው የነበራቸው ድፍረት ነበር። አዝሀር ኢስላማዊ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ሳይቀር ገብተው ለተማሪዎች ፓምፍሌትና ብሮሹር እስከመበተን የደረሱ ነበሩ።
በወቅቱ በፕሮፌሰር ሀሠን አልበና የተመሠረተው ሙስሊም ወንድማማቾች/Muslim Brotherhood/ ሲመሰረት ቀዳሚ አላማው እነሱን ለመከላከል ታስቦ የነበረ ቢሆንም ከነበራቸው የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት ሳቢያ ያሰበውን ያህል ሳይሰምርለት ቀርቷል። ድርጅቱም መዋቅሩን አርሞ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መስመሩ ውስጥ (በዋናነት የፖለቲካው አለም) ዘለቆ እንዲገባ ሰበብ ሁኖታል (ገፅ 302 ላይ ጥናቱ ገረፍ አድርጎት ያልፋል)
.
ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው መሠረታዊ አጀንዳ ግን ይህንን አይነት የሚሽነሪዎች እንቅስቃሴ ማድረግ ለኛ ኢትዬጵያውያን ሙስሊሞች ለምን ተሳነን? የሚል ነው። ለዚህ የተለያዩ ምክንያቶች ሊጠቀሱ የሚችሉ ሲሆን በግል ከዚህ ጋር ተያይዞ የማነሳቸው ግን የሚከተሉትን ነው።
❶ ያለመደራጀት ችግር
በየግል የሚሰሩ ስራዎች ጊዜያዊ ችግርን ሊፈቱ ይችሉ ይሆናል እንጅ ዘላቂ መፍትሄ አይሆኑም። ለዘላቂና ጠንካራ ስራ የህብረት መኖር ወሳኝ አካሄድ ነው። አንድ ብሄራዊ ቡድን ጠንካራና ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ቢኖሩትም መናበብ ካልቻለና በህብረት ካልሰራ ለብሄራዊ ቡድኑ የሚፈይደው ነገር አይኖርም (ምሳሌዋ የኡስታዝ Sadiq Mohammed Ahmed ናት፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ስናወራ በግል ከመከረኝ ምክር ውስጥ የሳበችኝ ምሳሌ ነበረች )
❷ ችግሩን አቅሎ መመልከት
አብዛኛው ሰው የሚሽነሪ አደጋን ቀላል አድርጎ የመሳል የተሳሳተ አመለካከት አለው። ከቤተሰቦቹ ወይንም በአካባቢው ከሚያውቀው አካል አንደኛው ሲከፍር ብቻ የሚባንን ሰው አለ። በዚህ መልኩ ሁለት ሰዎች ገጥመውኛል። የሚሽነሪዎችን ጠንካራ ስራ ለመረዳት የግድ ቤተሰባችን ውስጥ ሰው መክፈር አይኖርበትም።
❸ ሁሉኑም ስራ በጥቂት ሰዎች ትከሻ ላይ መጣል
የሚሽነሪ ስራ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተደቀነ አጀንዳ እንደመሆኑ መጠን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ነው። ሁላችንም እንደየአቅማችን ምን መስራት እንዳለብን ማሰብና መምከር ይኖርብናል። በተወሰኑ የንፅፅር ዳኢዎች ላይ ብቻ የተጣለ ሀላፊነት አድርጎ ማሰብ ፈጽሞ ስህተት ነው። በሀገራችን እኔ እስከማቀው ድረስ በንፅፅሩ መስክ የሙሉ ጊዜ ዳኢ የለም። ሁሉም ከራሱ መደበኛ ህይወት የተረፈውን ጊዜ ለዚህ ስራ የሰጠ ነው። በሺህ የሚቆጠሩ ጊዜያቸውን ለዚህ የሰጡ ሙሉ ወንጌልና አቃቤ እምነት/Apologists/ ባሉበት ሀገር ውስጥ ከንፅፅር ዳኢ ጋር ያለው ሬሽዬ ዜሮ የሚያስብል ነው። ስለዚህ ለዚህ ዋነኛው መፍትሄ ሁሉም በየፊናው መደራጀቱና ለዲኑ ዘብ መቆሙ ነው። በዚህ መልኩ መስራትና መናበብ ከተቻለ በአላህ ፍቃድ ትልቅ ስኬት መምጣት እንደሚችል አልጠራጠርም።
አላህ ያግዘን
_
ምንጭ፦
✔ Muslim response to missionery activities in egypt : with a special reference to the al azhar high corps of ulama (1925-1935) page 284
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


