በኡስታዝ አቡ ሐይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድ የተከበራችሁ ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ
ይህ ሊንክ ዐረብኛ ቋንቋን መማሪያ ሊንክ ነው፡፡ በውስጡ 306 ክፍሎች አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክፍል 40 ደቂቃ የሚፈጅ ትምሕርት አለው፡፡ ዐረብኛን ከፊደሎቹ(አሊፍ፣ባእ) በመጀመር እስከ ከፍተኛ ትምሕርት ድረስ ይሰጣል፡፡
1. እንዴት ልገለገልበት እችላለሁ?
ሀ. መጀመሪያ ይህን ሊንክ በመጫን ቴጁን ይክፈቱት፡፡ ምናልባትም አልከፍትም ካላችሁ ሊንኩን ኮፒ አድርጉትና ጎግል ላይ ለጥፈው ይፈልጉት
http://waqfeya.com/book.php?bid=7845
ለ. ከተከፈተልዎት በግራ በኩል የአስተማሪው ምስል አለ፡፡ ፕሮፌሰር አብዱ-ረሒም የሚባሉ ፓኪስታናዊ ናቸው፡፡
ሐ. ወደ ውስጥ ከቁጥር 01-23 የተዘጋጁ አድራሻዎች አሉ፡፡ እያንዳንዱ ቁጥር ውስጥ እስከ ስድስት የሚደርሱ የቪዲዮ አድራሻዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ቁጥር ዜሮ አንድን ይጫኑት፡፡ ከዛም ሲከፍትልዎት ወደ መሐል አካባቢ individual files የሚል ያገኛሉ፡፡ በውስጡ በሁለት ፓርት የተዘጋጁ ፋይሎች ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ እሱን ነው ከፈለጉ ቀጥታ በመክፈት ካልሆነም ወደ ኮምፒውተሮት በመጫን በፈለጉት ጊዜ ሊማሩበት የሚችሉት፡፡
2. እንዴት ላውርደው?
ሀ.ይህን ሶፍትዌር ከጫኑት በቀላሉ ለማውረድ ያግዝዎትል፡-
http://www.filehippo.com/search?q=idm
internate download manager ተጭነው በኮምፒውተሮት ውስጥ ካወረዱት በኋላ install ድርጉት፡፡ ለ አንድ ወር ያህል ነጻ ሶፍትዌር ስለሆነ ሊገለገሉበት ይችላሉ፡፡ ከዛም ወደ ዐረብኛ መማሪያው በመሄድ ማውረድ የሚፈልጉትን እየተጫኑ በተጫነው ሶፍትዌር አማካይነት ይገልገሉ፡፡ አላህ ያግዛችሁ
ለዚህ ስጦታ መነሻ ክፍያ የሚፈልጉትን ወስደው መጠቀም ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ ወደ አላህ እንድንጠቀምበትና ሌሎችንም ለሱ ብለን እንድንጠቅምበት ዱዓ ማድረግ ነው፡፡
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


