ወሒድ ዑመር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
19፥71 *ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው*፡፡ ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ وَإِن مِّنكُمْ إِلَّا وَارِدُهَا ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتْمًا مَّقْضِيًّا ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا
“ዒሊዪን” عِلِّيِّين “ማለት “ከፍተኛ” ወይም “አርያም” ማለት ሲሆን “ዐሊየት” عَالِيَة ማለት ደግሞ “ከፍተኛይቱ” ማለት ነው፤ የምእምናን መጽሐፍ በእርግጥ በዒሊዮን ውስጥ ነው፦
88፥10 *በከፍተኛ ገነት* ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
69፥22 *በከፍተኛይቱ ገነት* ውስጥ፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ
“ሢጂን” سِجِّين የሚለው ቃል “ዩሥጀነ” يُسْجَنَ ማለትም “ታሰረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እስር” ወይም “እንጦሮጦስ” ማለት ነው፤ “ሠጅን” سِّجْن ማለት “መታሰር” ማለት ሲሆን “መሥጁኒን” مَسْجُونِين ደግሞ “እስረኞች” ማለት ነው፤ የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ
“ሲራጥ” صِرَٰط በጀነት እና በጀሀነም መካከል ያለ “ድልድይ” ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 81 , ሐዲስ 124
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ”ረ.ዐ.” እንደተተከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ምእመናን ከእሳት ይድናሉ፤ በጀነትን እና በጀሃነም መካከል ድልድይ ይቆማል። قَالَ حَدَّثَنَا سَعِيدٌ عَنْ قَتَادَةَ عَنْ أَبِي الْمُتَوَكِّلِ النَّاجِيِّ أَنَّ أَبَا سَعِيدٍ الْخُدْرِيَّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” يَخْلُصُ الْمُؤْمِنُونَ مِنَ النَّارِ، فَيُحْبَسُونَ عَلَى قَنْطَرَةٍ بَيْنَ الْجَنَّةِ وَالنَّارِ،
ሁሉም የሰው ልጆች ወደዚያ ድልድይ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፤ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው፤ ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን ይድናሉ፤ በደለኞችንም ግን የተንበረከኩ ኾነው ተንሸራተው በጀሃነም ይተዋሉ፦
19፥71 *ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው*፡፡ ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ وَإِن مِّنكُمْ إِلَّا وَارِدُهَا ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتْمًا مَّقْضِيًّا ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا
ነጥብ አንድ
“ሲራጥ”
በሱረቱል መርየም 19፥71 ላይ “ሃ” ُهَا ማለትም “እርሷ” የሚለው ሦስተኛ መደብ ተሳቢ ተውላጠ-ስም ”ሲራጥ” መሆኗን ነብያችን”ﷺ” ነግረውናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 44, ሐዲስ 235
በሃፍሳ ፊት ከነብዩ”ﷺ” ሰምታ ኡሙ ሙበሽር እንደተረከችው፦ “በአላህ ፈቃድ የጀነት ባለቤቶች በዚያው መሠረት ታማኝነታቸውን ከሚቀበሉት መካከል ወደ እሳት አይገቡም። ሃፍሳም የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! ለምን?
ብላ ጠየቀቻቸው፤ እርሳቸውም ገሰጿት፤ እርሷም፦ “ከእናንተም ወደ ድልድይ ወራጅ እንጂ አንድም የለም” አለች፤ ነብዩን”ﷺ”፦ “የላቀውና ክብራማው አላህ፦ “ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን” ብሏል፤ አሉ። يَقُولُ أَخْبَرَتْنِي أُمُّ مُبَشِّرٍ، أَنَّهَا سَمِعَتِ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ عِنْدَ حَفْصَةَ ” لاَ يَدْخُلُ النَّارَ إِنْ شَاءَ اللَّهُ مِنْ أَصْحَابِ الشَّجَرَةِ أَحَدٌ . الَّذِينَ بَايَعُوا تَحْتَهَا ” . قَالَتْ بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ . فَانْتَهَرَهَا فَقَالَتْ حَفْصَةُ { وَإِنْ مِنْكُمْ إِلاَّ وَارِدُهَا} فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ” قَدْ قَالَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ { ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوْا وَنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا}
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 17, ቁጥር 1475
ዐብደላህ ኢብኑ መሱድ እንደተረከው፤ የአላህ መልክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ሰዎች ወደ ድልድል ይወርዳሉ፤ ከዚያም ከርሷ በሥራቸው ይወጣሉ። Narrated Abdullah ibn Mas’ud
Allah’s Messenger (peace be upon him) said, “mankind will go down to bridge and then come up from it because of their deeds.
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ Book 37, ሐዲስ 4420
“ዓኢሻ”ረ.ዐ.” ስትናገር እንደተረከችው፦ እኔ የአላህን መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ስል ጠየኲቸው፦ “ምድር በሌላ ምድር የምትለወጥበትን ሰማያትም እንደዚሁ አንድ አሸናፊ ለኾነው አላህም ፍጡራን ሁሉ የሚገለጹበት ቀን አስታውሱ” የሚል አለ፤ ታዲያ የዚያ ቀን ሰዎች የት ይሆናሉ? እርሳቸውም፦ “በድልድይ ላይ” ሲሉ መለሱ። حَدَّثَنَا أَبُو بَكْرِ بْنُ أَبِي شَيْبَةَ، حَدَّثَنَا عَلِيُّ بْنُ مُسْهِرٍ، عَنْ دَاوُدَ، عَنِ الشَّعْبِيِّ، عَنْ مَسْرُوقٍ، عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنْ قَوْلِهِ {يَوْمَ تُبَدَّلُ الأَرْضُ غَيْرَ الأَرْضِ وَالسَّمَوَاتُ } فَأَيْنَ تَكُونُ النَّاسُ يَوْمَئِذٍ قَالَ ” عَلَى الصِّرَاطِ ”
“ዐላ” ﻋَﻠَﻰٰ ማለት “ላይ”over” ማለት ነው፤ እንጂ ውስጥ ማለት አይደለም፤ ሲቀጥል
“መውረድስ” ማለት “መግባት” ብቻ ነው ያለው ማን ነው? ውሃ ቀጂዎች ወደ ውሃ ኩሬ “ወረዱ” ማለት ውሃ ውስጥ ገቡ ማለት ነውን? አይደለም፦
12:19 *መንገደኞችም መጡ፡፡ ውሃ ቀጂያቸውንም ላኩ*፡፡ አኮሊውንም ወደ ጉድጓዱ ሰደደ «የምስራች! ይህ ወጣት ልጅ ነው» አለ፡፡ ሸቀጥ አድርገውም ደበቁት፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَجَاءَتْ سَيَّارَةٌ فَأَرْسَلُوا وَارِدَهُمْ فَأَدْلَىٰ دَلْوَهُ ۖ قَالَ يَا بُشْرَىٰ هَـٰذَا غُلَامٌ ۚ وَأَسَرُّوهُ بِضَاعَةً ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِمَا يَعْمَلُونَ
28:23 *ወደ መድየንም ውሃ በወረደ* ጊዜ በእርሱ ላይ ከሰዎች ጭፍሮችን መንጋዎቻቸውን የሚያጠጡ ሆነው አገኘ፡፡ وَلَمَّا وَرَدَ مَاءَ مَدْيَنَ وَجَدَ عَلَيْهِ أُمَّةً مِّنَ النَّاسِ يَسْقُونَ وَوَجَدَ مِن دُونِهِمُ امْرَأَتَيْنِ تَذُودَانِ ۖ قَالَ مَا خَطْبُكُمَا ۖ قَالَتَا لَا نَسْقِي حَتَّىٰ يُصْدِرَ الرِّعَاءُ ۖ وَأَبُونَا شَيْخٌ كَبِيرٌ
በተመሳሳይ ሰዎች ወደ ድልድዩ ወረዱ ማለት ጀሃነም ገቡ ማለት አይደለም።
ነጥብ ሁለት
“ሙተቂን”
“ሙተቂን” ﻣُﺘَّﻘِﻴﻦ ማለት አላህን የሚፈራ “ፈሪሃ” ነው፤ አላህ ሁሉን ያየናል ብለው ከመጥፎ ድርጊት፣ ሁሉን ይሰማናል ብለው ከመጥፎ ንግግር፣ ሁሉን ያውቃል ብለው ከመጥፎ ሃሳብ የሚጠነቀቁ ሲሆን አላህ ከጀሃነም ያድናቸዋል፦
78:31 *ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አላቸው*። إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ مَفَازًا
19፥72 ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን*፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን፡፡ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا
አላህ ጀነትን ያዘጋጀው ሙተቂን ለሚባሉት ባሮቹ ነው፦
3፥133 *ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት ለጥንቁቆቹ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ*፡፡ وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ
68:34 “ለጥንቁቆቹ” በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው። إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ
44፥51 ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي مَقَامٍ أَمِينٍ
77:41 ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي ظِلَالٍ وَعُيُونٍ
38፥49 ይህ መልካም ዝና ነው፡፡ *ለጥንቁቆቹ በእርግጥ ውብ የኾነ መመለሻ አላቸው*፡፡ هَـٰذَا ذِكْرٌ ۚ وَإِنَّ لِلْمُتَّقِينَ لَحُسْنَ مَآبٍ
ስለዚህ ሙስሊሞች ሁሉ ገሃነም ይገባሉ የሚለው ፕሮፓጋንዳ ከጥራዝ-ነጠቅ ዕውቀት የሚመጣ ጥያቄ ነው፤ የሙስሊሞችማ እጣ
ፈንታ ጀነት እንደሆነ በግልፅና በማያሻማ መልኩ ተቀምጧል፦
4:124 *ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም*፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا
40:40 *እርሱ አማኝ ሆኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፤ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ*። مَنْ عَمِلَ سَيِّئَةً فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا ۖ وَمَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ
ነጥብ ሦስት
“ዛሊም”
“ዛሊም” ﻇَﺎﻟِﻢ ማለት “በዳይ” ማለት ሲሆን በአላህ ላይ ሌላ ሃልዎትንና ኑባሬን ማጋራት ትልቁ በደል ነው፤ አላህ በደለኞቹንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ ይተዋቸዋል፦
31፥13 ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! *በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና* ያለውን አስታውስ። وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
4፥30 ወሰን በማለፍ እና *በመበደልም ይህንን የሠራ ሰው እሳትን እናገባዋለን*። ይኸም በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَانًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا
19፥72 ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ *በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا
አላህ በደለኞቹንም የተንበረከኩ ኾነው በእሳት ውስጥ ይተዋቸዋል፤ “ፊሃ” ﻓِﻴﻬَﺎ ማለት “በእርሷ ውስጥ” የሚለው መስተዋድድ አገልግሎት ላይ የዋለው ለበደለኞች እንጂ ለሙተቂን በፍጹም አይደለም። “አምን” أَمْن ማለት “ጸጥታ” ማለት ሲሆን አላህን በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ነው ብሎ በማመንና በብቸኝነት በማምለክ በቀልብ ላይ የሚመጣ “ጸጥታ” “መረጋጋት” እና “ሰላም” ነው፦
6፥82 *እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው*፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يَلْبِسُوٓا۟ إِيمَٰنَهُم بِظُلْمٍ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ ።
የአላህ ሃቅ የሆነውን አምልኮ ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠት በእርሱ ላይ የሚፈፀም ዙልም ነው፤ “ዙልም” ظُلْم ማለት “በደል” ማለት ሲሆን በአላህ ላይ ማጋራት ታላቁ በደል ነው፤ ሱረቱል አንዓም 6፥82 አንቀጽ በወረደ እና በተነበበ ጊዜ “ዙልም” የተባለው ሺርክን መሆኑን በዚህ ሐዲስ ላይ ተገልጿል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65 , ሐዲስ 4776:
“እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው” የሚለው አንቀፅ በወረደ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ባልደረቦች የሆኑት ቃሉ ከባድ ስለነበር እነርሱም፦ “ከእኛ ውስጥ በደለኛ ያልሆነ ማን አለ?” ብለው ሲጠይቁ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሉቅማን ለልጁ፡- በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት “ታላቅ በደል” ያለውን አልሰማችሁምን? ብለው ተናገሩ። حَدَّثَنَا قُتَيْبَةُ بْنُ سَعِيدٍ، حَدَّثَنَا جَرِيرٌ، عَنِ الأَعْمَشِ، عَنْ إِبْرَاهِيمَ، عَنْ عَلْقَمَةَ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ {الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ} شَقَّ ذَلِكَ عَلَى أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَقَالُوا أَيُّنَا لَمْ يَلْبِسْ إِيمَانَهُ بِظُلْمٍ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّهُ لَيْسَ بِذَاكَ، أَلاَ تَسْمَعُ إِلَى قَوْلِ لُقْمَانَ لاِبْنِهِ {إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ}”
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


