ወንድም ሳላህ
ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ነቢዩ ሙሐመድን ሐሰተኛ ነቢይ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማይግጡት ሳር፣ የማይንዱት ተራራ እንዳሌላ በተደጋጋሚ አሳይተውናል። ልፉ ቢላቸው !! የሚገርመው ግን ይህንን ሁሉ ሲያደርጉ ጥቁር ጥላሸት የሚቀቡት ኢስላም ዓለምን እያጥለቀለቀ ይገኛል። እሳትን «ኡፍፍ» ባሉት ቁጥር ይቀጣጠላል እንጂ አይጠፋም ኢስላምም ባንቋሸሹት ቁጥር ዓለምን ይወርሳል። ዛሬ ላይ በሚያስደነግጥ ፍጥነት እየተስፋፋ ያለው ሀይማኖት ቢኖር እስልምና ነው፣ ታዋቂው የምርምር ማዕከል (PEW) እስልምና እና ሙስሊሞች በሚለው መጽሔት ላይ “Islam is the fastest-growing religious group in the world” በማለት ይናገራል፣ ከእርሱ ቡኋለም ይህን ጉዳይ ሌሎች ዓለማቀፋዊ የሆኑ ሚዲያዎች አጀንዳ ማድረጋቸው አይዘነጋም።
ግን ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ? በርካታ ሙስሊም ጠል ሀገራት ሙስሊሞች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ እያከናወኑ፣ እስልምናን እንዲተው እያስገደዱ፣ በርካቶች ደግሞ እስልምናን ጥቁር ጥለሸት በመቀባት እና በማብጠልጠል ሰዎችን ከእስልምና ለማስወጣት እየዳዱ እስልምና መጥፋት ሲኖርበት እንዴት በከፍተኛ ሁኔታ ሊስፋፋ ቻለ ? በእርግጥም ይህ ጥያቄ “መለኮታዊ ሀይማኖት ስለሆነ ነው” ከሚለው ምላሽ ውጪ የትኛውም መልስ አጥጋቢ ሊሆን አይችልም። የሰው ስሪት የሆኑት የተለያዩ እምነቶችና ልማዶች ጫና ሲደረግባቸው ለመጥፋት ብዙ ዓመታት አይፈጁም። Even ክርስትና ራሱ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የውሃ ሽታ እየሆነ እንደሚገኝ ብዙ ምንጮች ያትታሉ፣ እስልምናስ ለምን የዚህ ተቃራኒ ሆነ ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሆነው ከላይ እንዳልኩት “መለኮታዊ ሀይማኖት ስለሆነ” ነው ብቻ ነው። እንዳይረዝምባችሁ ርዕስ ወዳደረኩት ጉዳይ ልግባ።
መናፍቃን በእስልምና ላይ ከሚሰነዝሯቸው ትችቶች መካካል የናንተ ነቢይ ለትዳር ያልደረሰችን የዘጠኝ ዓመት ልጅ አግብቷል ይህ ደግሞ ከአንድ ነቢይ የሚጠበቅ ተግባር ስላልሆነ ነቢያችሁ ሐሰተኛ ናቸው የሚል ዲስኩር ያራግባሉ (ትችቱን የሚያቀርቡት እንደዚህ ስርዓታዊ በሆነ መንገድ ባይሆንም ነጥባቸው ተመሳሳይ ነው) ይህንን ነጥብ በመያዝ ነቢዩን የሚከሱ አብዛኞቹ ተቺዎች የሚከተሉትን ህጸጾች ይፈጽማሉ እነርሱም:- ከመጠን በላይ ማጋነን (Over-exaggeration)፣ የውሸት ብልጠት (Manipulation)፣ እውነታውን ያለማከለ ሙግት በማንሳት መደምደም (conclusion with false premises)፣ ማዛባት (Distortion) እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ። እነዚህን በሙሉ በጹሑፉ ውስጥ የምናየው ይሆናል። እንግዲህ እነዚህ አካላት ለሴቶች የተቆረቆሩ ይመስል ይህን ጉዳይ ያነሱት አዒሻህ ዘጠኝ ዓመቷ ስለነበር ለአቅመ-ሔዋን (ጉልምስና) “puberty” አልደረሰችም ይሉናል ! ለመሆኑ አንዲት እንስት ለጉልምስና የምትደርሰው በስንት ዓመቷ ነው ? እስኪ ዘመናዊው ሳይንስ የሚለውን እንመልከት።
የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ ማዕከል ሴት ልጅ ለአቅመ-ሔዋን የምትደርሰው በስንት ዓመቷ ነው ? የሚለውን ጥያቄ እንዲህ ይመልሳል «Girls usually begin puberty between the ages of 8 and 13 years old» ‟ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ የጉርምስና እድሜ የሚጀምሩት ከ8 እስከ 13 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ነው”
(🌐HealthyChildren.Org American Academy of Pediatrics 6/4/2019 (https://www.healthychildren.org/English/ages-stages/gradeschool/puberty/Pages/Physical-Development-Girls-What-to-Expect.aspx))
ከአንድ መቶ ሀምሳ በላይ በሆኑ ፕሮፌሽናል የህክምና ባለሙያዎች በመገምገም የሚታወቀው ስመጥሩ የህክምና መረብ (Health Line) ድረገጽ ሴት ልጅ ለአቅመ-ሔዋን የምትደርሰው ከ9‑11 ዓመት ባለው እድሜ ክልሏ ውስጥ እንደሆነ ይገልጻሉ። «Girls Puberty usually starts between ages 9 and 11»
(🌐Healthline: The Stages of Puberty: Development in Girls and Boys August 23, 2018 (https://www.healthline.com/health/parenting/stages-of-puberty))
ሳይንስ ይህን ከሆነ የሚለን የዘጠኝ ዓመቷ አዒሻህ ለአቅመ-ሔዋን የማትደርስበት ምክንያት ምንድነው ? እራሷ አዒሻህ በሐዲስ ላይ እንዲህ ትላለች:-
إِذَا بَلَغَتِ الْجَارِيَةُ تِسْعَ سِنِينَ فَهِيَ امْرَأَةٌ
«አንዲት ልጅ ዘጠኝ ዓመት ከሞላት ያኔ ሴት ትሆናለች (ትደርሳለች)።
(Jami` at-Tirmidhi, 1109: Book 11, Hadith 30)
‟ፈሂያ ኢምረዓህ” فَهِيَ امْرَأَةٌ የሚለው የተለመደው አባባል “ደርሳለች” ማለት እንደሆነ እሙን ነው፣ ይህ ብቻ የተቺዎቹን ክስ የሚያወድም ዘገባ ነው። ለማንኛውም እንቀጥል ! ሴት ልጅ ለአቅመ-ሔዋን ደርሳለች የምትባለው ምን ምን መስፈርቶችን ስትሟላ ነው ? ከተባለ የመጀመሪያው የወር አበባዋን ማየት ስትጀምር ነው። ታድያ ሴት ልጅ የወር አበባ ማየት የምትጀምረው በስንት ዓመቷ ነው ከተባለ አሁንም ለህክምና ባለሞያዎች ቦታውን እንልቀቅ።
የካናዳ የሕፃናት ሕክምና ማህበር (Canadian Paediatric Society) ሴቶች ለአቅመ-ሔዋን መች እንደሚደርሱ እና የመጀመሪያውን የወር አበባ መች ማየት እንደሚችሉ እንዲህ ይገልጻል ❝የጉርምስና ወቅት የሚባለው ሰውነት ብዙ ለውጦችን የሚያልፍበት ጊዜ ነው፣ ይህም በአካል እና አዕምሮ ከልጅ ወደ ጉርምስና ብሎም ወደ አዋቂነት የምንሻገርበት ጊዜ ነው። ምንም እንኳን የጉርምስና እድሜ በሁሉም ሰው ላይ በተመሳሳይ ጊዜ ባይከሰትም አብዛኛውን ጊዜ ለሴት ልጆች ከ8 እስከ 13 ዓመታት ውስጥ ይጀምራል…አንዳንድ ሴቶች የመጀመሪያውን የወር አበባቸውን ገና ከ8 እስከ 13 እድሜ ክልል ውስጥ እያለ የሚያዩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በአሥራዎቹ ውስጥ እንኳን ላያዩ ይችላሉ።❞
(🌐Canadian Paediatric Society: Growing up Information for girls about puberty March 2018 (https://caringforkids.cps.ca/handouts/behavior-and-development/information_for_girls_about_puberty))
ከላይ የተመለከትነው “Health line” የተባለው የጤና ድህረገጽ ይህንን በተመለከተ እንዲህ ይላል ‟Most girls will get their first period sometime between the ages of 10 and 15. However, a first period can occur as young as 8” አንዳንድ ጊዜ አብዛኞቹ ሴቶች የመጀመሪያውን የወር አበባ ከ10 እስከ 15 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ሊያዩ ይችላሉ፣ ይሁን እንጂ የመጀመሪያው የወር አበባ በ8 ዓመት ዕድሜያቸው ላይ ሊከሰት ይችላል❞
(🌐Healthline: At What Age Do Most Girls Get Their First Period? September 29, 2021 by S. Behring (https://www.healthline.com/health/womens-health/what-age-do-girls-get-their-period))
ይህንን ለማሳየት የፈለግነው አንዳንድ ብዙም እውቀት ያሌላቸው ሰዎች ሴት ልጅ ከ16 ዓመት በታች የወር አበባ ማየት እንደማትችል ስለሚናገሩ ነው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ አዒሻህ 9 ዓመቷ ስለነበር የወር አበባ ለማየት አልደረሰችም እያሉ የአላዋቂነት ንግግር ይነዛሉ። ከላይ እንዳየነው ሴት ልጅ አይደለም በዘጠኝ ዓመቷ በ8 እንኳን የወር አበባ ማየት እንደምትል ነው ሳይንስ የሚነግረን እስኪ ይህንኑ (በወር አበባ ዙርያ) ጥንታዊያን ሙስሊም ሊቃውንት የሚሉንን እንመልከት ወደ ንባቡ።
አል-ዘሀቢይ (673 H) የተባለው የታሪክ ጸሐፊ እንዲህ ይላል ❝በየመን ውስጥ በ9 ዓመታቸው ብዙ ልጃገረዶች የወር አበባቸውን ያየሉ❞
(Dhahabi, Siyar A’lam an-Nubala Vol. 10 p.91)
ኢማሙ በሃይቂይ በዘገባው ሐዲስ ላይ ሻፊዕይ እንደተረከው ‟በዐረብ ውሰጥ ቲሃማ አከባቢ ልጃገረዶች ለአቅመ-ሔዋን የሚደርሱበት እድሜ በ9 ዓመታቸው ነበር…በሰነዓ ውስጥም አንዲት ሴት በ21 ዓመቷ አያት ሆናለች፣ እርሷ በዘጠኝ ዓመቷ ለአቅመ-ሔዋን ደርሳ በአስር ዓመቷ ወለደች ልጅም በተመሳሳይ በአስር ዓመቷ መውለድ ችላለች።”
(As-Sunan al-Kubra by al-Bayhaqi 1588 And 1/319)
ይገርማል አይደል በ21 ዓመት አያት መሆን ? አሁን የምትሰሙት ደግሞ ከዚህ በላይ ያስደንቃቹኃል በ1933 የተወለደችው Lina Medina በዚህ ዓለም በእድሜ ትንሿ እናት ተብላ በታሪክ ተመዝግባለች፣ Lina ገና በአምስት ዓመት ከ7 ወሯ ላይ መውለድ እንደቻለች ታሪክ ይናገራል፣ «Lina Marcela Medina is confirmed to be the youngest mother in history, giving birth at the young age of 5 years and 7 months old»
(📗History of yesterday: The World’s Youngest Mother Who Gave Birth at the Age of 5. Article of Jun 23, 2020)
ከዚህ በታች በሚገኘው ሊንክ ገብታችሁ ከ6-11 ባለው እድሜ ውስጥ የወለዱ አያሌ ሴት ልጆች ስም ዝርዝር ከአጭር ማብራሪያ ጋር ማንበብ ትችላላችሁ።
(Bionity.com List of youngest birth mothers (https://www.bionity.com/en/encyclopedia/List_of_youngest_birth_mothers.html#_ref-6/))
ወደ ነጥቡ ስንመለስ አዒሻህ በዚያን ጊዜ ጋቢቻው ከመፈጸሙ በፊት በአካልም ሆነ አዕምሮ ብቁ እንስት ነበረች፣ ብዙ ኢስላማዊ ምንጮች ላይም ለአቅመ-ሔዋን መድረሷ ተዘግቧል እስኪ ከእነርሱ መካካል እራሷ አዒሻህ የተናገረችውን እንመልከት።
أَنَّ عَائِشَةَ، زَوْجَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَتْ لَمْ أَعْقِلْ أَبَوَىَّ إِلاَّ وَهُمَا يَدِينَانِ الدِّينَ، وَلَمْ يَمُرَّ عَلَيْنَا يَوْمٌ إِلاَّ يَأْتِينَا فِيهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم طَرَفَىِ النَّهَارِ بُكْرَةً وَعَشِيَّةً، ثُمَّ بَدَا لأَبِي بَكْرٍ فَابْتَنَى مَسْجِدًا بِفِنَاءِ دَارِهِ، فَكَانَ يُصَلِّي فِيهِ وَيَقْرَأُ الْقُرْآنَ
የነቢዩ ሚስት የሆነችው አዒሻህ እንዲህ አለች:- ‟የጉርምስና እድሜ ላይ ከደረስኩ ጀምሮ ቤተሰቦቼ እስልምናን ሲከተሉ አይቻቸዋለሁ፣ ያኔ ነቢዩ መጥተው በቀንና ሌሊት ይጎበኙን ነበር። አባቴ በቤታችን ግቢ ውስጥ መስጂድ ለመስራት አስቦ ከዚያን አደረገው። በዚያ ውስጥም ይሰግዳል ቁርኣንንም ያነብ ነበር…”
(Sahih al-Bukhari 476: Book 8, Hadith 124)
በዚህ ሐዲስ ላይ አዒሻህ ገና በአባቷ ቤት እያለሽ ለነቢዩ ከመታጨቷ በፊት ጎልማሳ እንደነበረች በግልጽ ተጽፏል። የእንግሊዝኛው ትርጉም ለቃሉ “Puberty” በማለት ያስቀምጣል ይህም ማለት “ጉልምስና” ማለት ነው። የዐረብኛው ቃል ደግሞ “አዕቂል” أَعْقِلْ የሚል ሲሆን “የበለጠ ምክንያታዊ መሆን፣ ብልህ መሆን ማለት ነው፣ ይህን ቃል ስመጥር የዐረበኛ መዝገበ ቃላት ‟ምክንያታዊ እና ብስለት ላይ የሚደረስበት እድሜ” the years of reason and MATURITY በማለት ያስቀምጣሉ [1] ጥንታዊው የኢስላም ምሁር ኢማሙ ነወዊይ ሐዲሳት ላይ በሰጣው ማብራሪያ ስለ አዒሻህ አካላዊ ሁኔታ እንዲህ ይለናል ❝የአዒሻህ ሰውነት ያኔ ጎልማሳ በሳል ነበር (ሸባበን ሁስና) በጥሩ ወጣትነት ላይ ነበረች❞
(Sharh Sahih Muslim 9/207 by Imam Nawawi)
ታላቁ የቁርኣን ተንታኝ ኢማሙ ጠበሪ የአዒሻን አካላዊ ሁኔታ በተመለከተ እንዲህ ይላል ❝አዒሻህ ያኔ በጣም ልጅ ስለነበረች እዚያው ከቤተሰቧ ጋር ትኖር ነበር፣ ቡኋለ ላይ ለአቅመ-ሔዋን ስትደርስ ጋብቻው እንዲፈጸም ተወሰነ።❞
(Muhammad: A Biography of the Prophet, Harper San Francisco, 1992, page 157)
ከእነዚህ ሁሉ ምንጮች የምንረዳው አዒሻህ ለአቅመ-ሔዋን የደረሰች እንስት እንደነበረች ነው። ሳይንስ አንዲት ልጃገረድ ለአቅመ-ሔዋን (ጉልምስና) “Year of puberty” የምትደርሰው ከስምንት ዓመቷ ጀምሮ መሆኑን በግልጽ ይናገራል፣ የወር አበባንም ከስምንት ዓመታቸው ጀምረው ማየት እንደሚችሉ ያስረዳናል፣ በአካልም ሆነ አዕምሮ ብቁ የነበረችው አዒሻህ ከየትኛውም ሴት ሰሃቢይ በላይ ብስለት እንደሚታይባት እና ሐዲሶችን በቃል መሸምደድ ላይ ቀዳሚ እንደነበረች ታሪኳን ካነበበ ሰው የሚሰወር አይደለም። ስለዚህ አዒሻህ ለጉልምስና አልደረሰችም ነበር የሚለው ክስ የጉልምስናን ጅማሬ ወቅት ከማያውቅ እና ሳይንስን በስም እንጂ በተግባር ከማያውቁ አካላት የመጣ ገላበ ወሬ መሆኑን ከዚሁ መረዳት እንችላለን።
…ይቀጥላል…
1] Hans Wehr A Dictionary of Modern written Arabic [Edited by John Milton – Spoken Language Services, Inc. 1976], page 737
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


