ወንድም ሳላህ
ክርስቲያን ሚሺነሪዎች የአዒሻን ለጉልምስና ዕድሜ (Puberty) መድረስ ከጥንታዊያን ሰነዶች እና ከዘመናዊው ሳይንስ ጥናቶች ስናሳያቸው እንደ ሙግት የሚያነሷት ነጥብ አለች። እሷም “አዒሻህ በአሻንጉሊት እንደምትጫወት ሐዲስ ላይ ተጽፏል ስለዚህ ለአቅመ-ሔዋን አልደረሰችም ነበር” እያሉ የተፋለሰ አመክንዮ (Logic) ያቀርባሉ። ለማንኛውም እንደሚከተለው ምላሽ እንሰጣለን:-
በአሻንጉሊት መጫወት እና ለአቅመ-ሔዋን መድረስን የሚያገናኛቸው ምንም ነገር የለም። አሻንጉሊት መጠቀም ለጉልምስና አለመድረስን አያመላክትም፣ በአሻንጉሊት አለመጫወትም የጉልምስና ምልክት አይደለም። ከጥንት ጀሞሮ እስከ ዘመናዊው ዘመን ድረስ ትልቅ ሆነው አሻንጉሊትን የሚይዙ (በአሻንጉሊት የሚጫወቱ) እንስቶች አሉ። ህጸናት ሆነውም በፍጹም አሻንጉሊት የማይፈልጉ ብዙ ልጆች አሉ። ስለዚህ በአሻንጉሊት መጫወትንና አለመጫወትን ከጉልምስና ጋር ማያያዝ የአላዋቂዎች አመክንዮ ይሆናል ማለት ነው።
ዶ/ር ጁሊየት ፒርስ የምትባል የታሪክ ጸሐፊ በዚህ ዙርያ እንዲህ በማለት ትጽፋለች:- ❝ አሻንጉሊቶች ከሴት ልጆች ስነምግባር ጋር በቅርበት እየታዩ ሲመጡ እጅግ ብዙ የአዋቂዎች የአሻንጉሊት አይነቶች በ1920ዎቹ እና 1930ዎቹ መመረት ተጀመሩ…During the 1920’s it was Trendy For Adult woman to carry Dols in public…በ1920’ዎቹ ውስጥ የአዋቂዎች አሻንጉሊትን በአደባባይ መያዝ (መሸከም) የተለመደ ነገር ነበር…❞
(📗Girl Culture: An Encyclopedia, Jacqueline Reid-Walsh (editors), by Dr. Juliette Peers, vol.1, page 28
በ2013 BBC ያወጣው አንድ መፅሔት አለ ርዕሱ “Teddy bears: Adults on their stuffed toy companions” ይሰኛል። በዚህ አርቲክል ላይ በአሻንጉሊቶች እና አዋቂዎች (>80 yrs) መካከል ያለውን ጥብቅ ቁርኝት ከነታሪክ ሕይዎታቸው ጋር ያስነብበናል። የሚያስገርመው ነገር ልጆችን የወለዱ በርካታ ጎልማሶች እንኳ ለእነዚህ አሻንጉሊቶች ትኩረት ሰጥተው እንደ ልጅ እንደሚንከባከቧቸው፣ ለረጅም ዘመናትም እራሳቸው ጋር እንደሚያኖሯቸው ተጽፎ እናገኛለን።
https://www.bbc.com/news/magazine-21367728
ስለዚህ አሻንጉሊቶችን መጠቀም ለጉልምስና አለመድረስም ሆነ ለጉልምስና መድረስ ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም ማለት ነው። ልክ ጎልማሶች ሆነው አሻንጉሊትን የሚጠቀሙ እንስቶች እንዳሉ ሁሉ ያልደረሱ ህጻናት ሆነው አሻንጉሊትን በፍጹም የማይፈልጉ ልጆች ይገኛሉ። አሻንጉሊት የጉልምስና መለኪያ በፍጹም አይደለም። ካደጉ ቡኋለ በአሻንጉሊት የሚጫወቱትን ሴቶች ለአቅመ-ሔዋን አልደረሱም፣ ህጸናት ሆነው ደግሞ በአሻንጉሊት የማይጫወቱትን ለአቅመ-ሔዋን ደርሰዋል ብሎ ማሰብ ቂልነት ነው። ስለዚህ የአዒሻህ በአሻንጉሊት መጫወት በፍጹም ያለመድረስ ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም ማለት ነው።
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


