ወንድም ሳላህ
ዛሬ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ተብሎ በሰፊው የክርስቲያን ማህበረሰብ ዘንድ እንደ አምላክ ቃል የሚታመንበት ባይብል ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግልጽ ብርዘትን እያስተናገደ የመጣ መፅሐፍ ነው። ባይብል ክፉኛ መበረዙን ለማወቅ የTextual criticism (ምንባበዊ ኅያሴ) ሊቅ መሆን አይጠበቅባችሁም። ለአፍታ ብቻ ሁለት ወይ ሦስት የአማርኛ ባይብል ቅጂዎችን አንድ ቦታ አድርጋችሁ ብታስተያዩት በመካከላቸው ያለው ግጭት እና ቅያሬ በቀላሉ የኃለ ታሪክ ችግሮቹን ያስገነዝባችኃል። እስኪ መለስ ብለን ይህን እውነታ ከራሳቸው ሊቃውንት እንስማ:-
ከጥንታዊያን የቤተክርስቲያን አበዎች መካከል አንዱ የሆኑት ቅዱስ ዮስጢኖስ ሰማዕት (150 AD) በታዋቂው ጹሑፋቸው ከአይሁዳውያን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ እነርሱ ከመጽሐፈ ዕዝራ እና ከትንቢተ ኤርሚያስ ቆርጠው ያስቀሩት ሀሳብ መኖሩን እንዲህ በማለት ይናገራሉ:-
❝ከመጽሐፈ ዕዝራ እንዲህ የሚለውን ቃል ቆርጣችኃል…‟ዕዝራም ለሕዝቦቹ እንዲህ በማለት ተናገረ ‟ይህ ፋሲካ አዳኛችንና መጠጊያችን ነው፣ እናንተም ይህንን ብታስተውሉ ልባችሁም ቢቀበለው ይህ ስፍራ ለዘለዓለም አይጠፋም” ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር፣ ነገር ግን በእርሱ የማታምኑ ትዕዛዙንም የማትቀበሉ ከሆነ የአሕዛብ መሳቂያ ትሆናለችሁ።….ከዚህ ውጪም ከትንቢተ ኤርሚያስ ይህንን ቃል አጥፍታችኃል ‟‘እግዚአብሔር አምላክ በመቃብር ውስጥ የተቀመጡትን የሞቱትን የእስራኤልን ሕዝቡን አሰበ፣ የራሱንም ማዳን ሊሰብክላቸው ወረደ።”
(📘The Apostolic Fathers with Justin Martyr and Irenaeus chapter 72)
ይህ ጥንታዊው ዐቃቤ እምነት አይሁዳውያን መጽሐፍት ላይ እንዴት ሲጫወቱ እንደነበር ይነግረናል። የዘመናችን ክርስቲያኖች ይህንን እውነታ መቀበል ለምን ከበዳቸው ? ለማንኛውም እንቀጥል። የአራተኛው ክፍለዘመን የቁስጥንጥንያ ኤጲስ ቆጶስ የነበረው ዮሐንስ አፈወርቂ የብሉይ ኪዳን መፅሐፍት በባለቤቶቹ ተደምስሰው እና ተቃጥለው ድምጥማጣቸው እንደጠፋ እንዲህ በማለት ይናገራል:-
❝ብዙ የነቢያት ጹሑፎች መጥፋታቸውን ከዜና መዋዕል ታሪክ መረዳት እንችላለን። እነርሱ (አይሁዳውያን) ቸልተኞች በመሆናቸው እና ድንቁርና ውስጥ በመውደቃቸው ብዙ ጹሑፎች ጠፍተዋል፣ ሌሎችን ደግሞ በእሳት አጋይተዋል፣ የቀሩትን ቆረራርጠው ጥለዋል…የኤርምያስ የኃለኛው እውነታ፣ አራተኛውን የንግሥታት መጽሐፍ የሰበሰበው ሰው ኦሪት ዘዳግም ከረጅም ጊዜ ቡኋለ ተገኝቶ የሆነ ቦታ ቢቀበርም ቡኋለ ላይ መጥፋቱን ዘግቧል። አረመኔዎች በሌሉበት ጊዜ እነርሱ (አይሁዳውያን) የገዛ መጽሐፍቶቻቸውን የካዱ ናቸው።❞
(📘The Homilies of S. John Chrysostom on the Gospel of St. Matthew, Vol.1, P. 125)
ይህ የቤተክርስቲያን አባት አይሁዳውያን የአምላክን ቃል ደምስሰው እንዳጠፏቸውና እንዳቃጠሏቸው ይመሰክራሉ፣ ታድያስ የነቢያት ጹሑፎች በእነዚህ ሰዎች ተቃጥለው የጠፉ ከሆነ ዛሬ ላይ መሰረታቸው በማይታወቁ መጽሐፍት የምናምነው ለምን ሲባል ነው ? እኛንስ የነቢያትን መጽሐፍት አሳዩን የምትሉን ለራሳችሁ እንኳ መች ትክክለኛውን ጹሑፎች ያዛችሁ ? ጥያቄዎቻችን ይቀመጡና ማስረጃችንን ማዝነብ እንቀጥል። እስኪ አሁን ደግሞ ወደ ፕሮቴስታንቱ ዓለም እንምጣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አዳም ክላርክ የተባለው የሥነ-መለኮት ምሁር እና ሙፈሲር በመጽሐፉ ላይ እንዲህ በማለት ይናገራል:-
❝And have no doubt that the Jews have here corrupted the text through their enmity to the Samaritans.
፨ ትርጉም:- አይሁዳውያን ለሳምራውያን ካላቸው ጥላቻ የተነሳ መጽሐፍትን ስለመበረዛቸው ምንም ጥርጥር የለንም❞
(📘The Holy Bible: Containing the Old and New Testaments, Vol 1, Page 804)
አራት ነጥብ ! ከዚህ በላይ ምን ትፈልጋለህ ? የገዛ የቤተክርስቲያን ታሪክ ይህንን የሚልህ ከሆነ አንተ ከማን በልጠህ ነው ባይብል አልተበረዘም የምትለው ? አበዎች መጽሐፍት ተበርዘዋል እያሉህ አንተ “አይ አልተበረዙም” የምትለው በየትኛው ሞራልህ ነው ? እስኪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በታሪክ መጽሐፏ ውስጥ በዚሁ ነጥብ ላይ ያስቀመጠችውን ምስክርነት አንብበን እንምጣ።
❝አሁንም ኹላችሁ ማኀበረ አይሁድ ስሙ እንንገራችሁ…እነሆ የነቢያትን ቃል አጠፋችሁ መጽሐፍቶቻቸውንም ፍቃችሁና ደምስሳችሁ የታመነውንና እውነተኛውን የትንቢታውንም ቃል ለውጣችሁ ለራሳችሁ የውሸት መጽሐፍ ጻፋችሁ❞
(📕መጽሐፈ ሜላድ ዘወርኋ የካቲት 7÷፳፮)
ይህ ነው እውነታው ! ቤተክርስቲያን ከጥንት ዘመን ጀምራ አይሁዳውያን የነቢያትን መጽሐፍ በመበረዛቸው ምክንያት ለ2000 ዓመታት ትወቅሳቸዋለች። የቆሎ ተማሪዎች ደግሞ ከእኛ ጋር የጀመሩትን ሙግት ለማሸነፍ ሲሉ የገዛ ቤተክርስቲያናቸውን ውሸታም አድርገው አይሁዳውያን የአምላክን ቃል አልበረዙም ይሉናል?! ያለው ሐቅ ግን በመረጃ ከላይ ያሳየናችሁ ነው። እውነት ሁሌም ያሸንፋል።
وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا
‟በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡» (Qur’an 17:81)
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


