ወንድም ሳላህ
ሚሽነሪዎች እንደለመዱት ሐዲሳትን ከፊት እና ከኋላው እየቆራረጡ መልዕክቱን በማዛባት እንደው ከተሳካልን በማለት ስለ ዲናቸው መረዳት ያሌላቸውን ሙስሊሞች ለማሳሳት እንዲሁም ወደ እስልምና እየጎረፈ ያለውን የህዝበ ክርስቲያኑን ቁጥር ለመቀነስ ደፋ-ቀና ማለታቸውን ቀጥለዋል። “ነቢዩ ሙሐመድ ሀሰንና ሁሴን የተባሉትን ህጸናት (የልጅ ልጃቸውን) ምላሳቸውን (የነቢዩን ምላስ) እንዲጠቡ አስደርገዋል፣ ይህ ደግሞ የግብረሰዶማውያን ተግባር ነው” በማለት ይናገራሉ (ወነአዑዙቢላህ)። ጥላቻቸው እዚህ ደረጃ ደርሷል። በተመሳሳይ ፆታ አላስፈላጊ ንክኪ ላይ በጣም የከረራ አቋም ያላቸው አካል ላይ እንዲህ አይነት ተራ ትችት መክፈቱ በእውነቱ በጣም ያሳፍራል። አይደለም ታላቅ ነቢይን ይቅርና አንድ ተራ ሙስሊምን ራሱ በዚህ መወንጀል እንደ እውነቱ ከሆነ ይከብዳል። ለማንኛውም ወደ ምላሹ እንግባ:-
▸ በመጀመሪያ ደረጃ አዎ ነቢዩ ሙሐመድ ሀሰን እና ሁሰይን (የልጅ ልጃቸው) ምላሳቸውን እንዲጠቡ አድርገዋል ! ግን ለምንድነው ያደረጉት ? ከተባለ ሙሉውን ሐዲስ እናንብብ።
سمِع رسولُ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم الحَسَنَ والحسينَ وهما يبكيان وهما مع أمِّهما فأسرَع السَّيرَ حتَّى أتاهما فسمِعْتُه يقولُ ما شأنُ ابنَيَّ فقالَتِ العطشُ، هَلْ أَحَدٌ مِنْكُمْ مَعَهُ مَاءٌ ؟ نَاوِلِينِي أَحَدَهُمَا، فَأَدْلَعَ لَهُ لِسَانَهُ فَجَعَلَ يَمُصُّهُ حَتَّى هَدَأَ أَوْ سَكَن
‟የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ሀሰን እና ሁሰይን በእናታቸው ዘንድ እያሉ በጣም ሲያለቅሱ ሰምተው ‟ህጸናቶቹ ምን ሆኑ (ለምንድነው የሚያለቅሱት?) ብለው ጠየቁ፣ እናታቸውም “በውሃ ጥም ምክንያት ነው” አለች። ከእናንተ መካከል ውሃ የያዘ የለም ወይ ? ብለው ጠየቁ። አንዳቸው ውሃን አመጡ፣ ከዚያም (የአላህ መልዕክተኛ) ህጻናቱ ዝም እስኪሉ ድረስ ከምላሳቸው ውሃን አጠጧቸው።
(📗መጅሙዕ አል-ዘዋዒድ 9/183፤ አል-ሙዕጀም አል-ከቢር 2588)
وَأَعْطَى الْحَسَنَ وَالْحُسَيْنَ لِسَانَهُ فَمَصَّاهُ وَكَانَ يَبْكِيَانِ عَطَشًا فَسَكَتَا
በውሃ ጥም ለሚያለቅሱት ሀሰን እና ሁሰይን ከምላሳቸው (ውሃን) በማስጠባት ዝም እንዲሉ አድርገዋል።
(📗ኪታብ አል-ሺፋዕ 1/326)
አራት ነጥብ ! ነገሩ ሙስሊም ባልሆኑ አካላት ተቆርጦ እንደሚዘዋወረው ሳይሆን የአላህ መልዕክተኛ ያንን ያደረጉበት ምክንያት ለህጻናቱ ሲሉ ብቻ ነው። ለጨቅላ ህጸናት ምግብን በአፍ መስጠት በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች እንኳ የተለመደ ሆኖ ሳለ ነገሩን ወደ ብልግና በመለወጥ መልዕክቱን ማዛባታቸው ምን ያክል ጭፍንተኝነት እንደተጠናወታቸው ያሳብቅባቸዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በራሳቸው የተንሸዋረረ ሚዛን የእግዚአብሔርን ነቢይ ሳያውቁ መሳደባቸው ነው፣ እንዴት ከተባለ ? ነቢዩ ኤልሳዕ የሱነማይቱን ልጅ ከሞት በሚያስነሳበት ግዜ በላዩ ላይ ተኝቶ ከንፈሩን በከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር። ነቢዩ ኤልሳዕ ግብረ-ሰዶም ስለሆነ ይሆን ?
“መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ።”
— 2ኛ ነገሥት 4፥34
አፍን በአፍ ገጥሞ መሳሳም የግብረሰዶም ምልክት ነው ከተባለ ታድያስ ነቢዩ ኤልሳዕ ጌ-ይ የማይሆንበትን ምክንያት ልታብራሩልን ትችላላችሁ ? ከሁሉም በላይ አስከፊው ነገር ደግሞ ከኢየሱስ ጋር አፍ ለአፍ የተሳሰሙ ወንዶች ብዛት ነው። በገድላትና ድርሳናት ታሪክ ውስጥ እንደ ኢየሱስ የወንዶችን አፍ የሳመ አንድ ወንድ ማግኘት ይከብዳል። ይህንንም ስንል በማስረጃ ነው፣ እስኪ እንመልከት:-
▸ የኢየሱስ ልማድ በኦርቶዶክስ መዛግብት ውስጥ።
“ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን አፉን ሦስት ጊዜ ሳመው በዚያንም ጊዜ ከፍቅሩ ጣዕም ብዛት የተነሣ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ጌታችንም ተቀብሎ አቅፎ ከእርሱ ጋር አሳረጋት። በመላእክት ጉባኤም ብዙ ምስጋና ተደረገ።”
[📕ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር ምዕራፍ 26]
‟ዳግመኛም ጌታችን እንዲህ አለው። የግሼው አባ በጸሎተ ሚካኤል ወደ አለበት ሥፍራ ወደ አማራ ምድር ሂድ ውጣ ብዬ እስክነግርህ ድረስ ከዚያው ተቀመጥ። የምክር አበጋዝ መልአክ ሚካኤል ከአንተ ጋር ይሁን ብሎ አፉን ሳመው።”
[📕ገድለ ተክለ ሃይማኖት 39÷8]
“የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው በኋላ ጌታችን አፉን ሶስት ጊዜ ሳመው። ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች።”
[📕ነገረ ቅዱሳን አበው ምዕራፍ 8]
በናንተ ሒሳብ ከዚህ በላይ ግብረሰዶማዊነት ይኖር ይሆን ? አፍ ለአፍ መሳሳም በክርስትና እንዴት ይታያል? ይህ እውን የአምላክ ተግባር (ባሕርይ) ነው? ገና ከዚህ የበለጠ አለ:- የክርስቲያኖች አምላክ የሆነው ኢየሱስ ጣቱን ለወንድ ያስጠባ ነበር ! ትርጉሙ ምን ይሆን ? ፍርዱን ለእናንተው።
‟ይህን ብሎ ጣቱን አወጣ ወደኔ ቅረብ አለው ሁለመናው በመለኰት ጨውነትም ይጣፍጥ ዘንድ አውራ ጣቱን አጠባው።
[📓የአባታችን የመባዓ ጽዮን ገድል ፰፥፭]
‟በሦስቱ ስም አምነን ለሚያነበውና ልብ ብሎ ለሚሰማው አስረድተን እንናገራለን የመድኃኔ ዓለም ፍቅሩ በመባዓ ጽዮን ላይ በበዛ ጊዜ የምሕረት ቃል ኪዳንን ይሰጠው ዘንድ ጎበኘው ጣቱንም አጠባው።
[📓የአባታችን የመባዓ ጽዮን ገድል ፱፥፩]
ስናጠቃልል ተወዳጁ ነቢያችን ሙሐመድ እናንተ በምላሳችሁ አንድምትዋሹባቸው አይነት ሰው እንዳልሆኑ በደንብ ታውቃላችሁ። ለዚያም ነው ሁሌም የሕይወት ታሪካቸውን ስታቀርቡ ዋናውን መልዕክት የምትቆርጡት። በውሃ ጥም ለሚያለቅሱት የልጅ ልጃቸው ምግብን በአፍ አድርገው መስጠት በየትኛውም መንገድ አያስተችም። ፈጣሪ ልቦናን ይስጣችሁ ለእኛም ፅናቱን ይሰጠን።
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


