ወንድም ሳላህ
ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ቁርኣንን ለመተቸት ከሚያነሷቸው ሙግቶች መካከል ቁርኣን ስለ ሥነ-ፈለክ “astronomy” የሚናገረው ነገር በዘመናዊው ሳይንስ መነፅር ውድቅ ስለሆነ የአምላክ ቃል ሊሆን አይችልም የሚል ነው። ለዚህም የሚከተለውን አንቀጽ ያለ አግባብ በመጥቀስ ቁርኣን ምድርን ጠፍጣፋ አድርጎ እንደገለጻት ይናገራሉ:-
۞ ‟ምድርንም ከዚህ በኋላ “ዘረጋት”፡፡ (ሱራ 79፥30) وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا
በዚህ አንቀጽ ላይ ዘረጋት ተብሎ የተቀመጠው የአረበኛው ቃል “ደሃሀ” دَحَاهَا የሚል ሲሆን “ደሃ”دَحَاى ከሚለው ትርጉመ ብዙ ቃል የመጣ ነው። ከቃሉ ፍቺዎች መካከል “ክብ” round/spherical አንዱ ነው። አረቦች ይህንን ቃል ጥንት ክብ ነገርን ለመግለጽ እንደሚጠቀሙበት ኢብኑ ሙንዘር ሊሳን አል-አረብ በተሰኘው የአረብኛ ቋንቋ መዝገበ-ቃላት መጽሐፉ ላይ እንዲህ ይነግረናል:-
إندحَّ بطنه إندحاحاّ اي إتّسع
‟ከርሱ (ሆዱ) ክብ (In-dahaha) እና ትልቅ ሆነ” His tummy became “round” and bigger.
و بطنٌ مُنداحُ أي خارخٌ مُدوّر
‟ቦርጩ ሙን-ደህ (Mundah) ነው ማለት ወጣ ያለ እና ክብ ነው ማለት ነው። His tummy is mun-daahun means it is OUT THERE AND ROUND.
(📜Lisan Al-Arab dictionary Book 2, p.215/436)
አረቦች “ደሃ” دَحَا የሚለውን ቃል የእንቁላል ቅርጽ ላለው ክብ ነገርና እራሷን እንቁላልን ለመጥራት እስካሁን ድረስ እንደሚጠቀሙበት ምሁራን ይናገራሉ “daha means to “shape like an egg”, its noun being dahiyah, which the Arabs still use to mean an egg¹. ስለዚህ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ በቋንቋ ደረጃ በዚህ መንገድ መውሰድ እንችላለን።
وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا
79፥30 ‟ምድርንም ከዚህ በኋላ የእንቁላል ቅርጽ አደረጋት።”
የምንኖርባት ምድር ክብ እንደሆነች ግልጽ ነው፣ ይሁን እንጂ ክብ “Round” ናት ሲባል (እንደዚህ ○) ሙሉ በሙሉ Circular ናት ማለት አይደለም። የምድር ቅርጽ እንደ እንቁላል Ellipsoid shape እንደሆነ የሥነ-ፈለክ “Astronomy” ተመራማሪዎች ያትታሉ “The Earth is not a perfect sphere, but is instead more like a slightly squashed sphere called an ellipsoid.²
ሌላኛው ትርጉሙ “በሰጠ” بَسَط የሚል ሲሆን ይህ የጁሙሑር ኡለማዕ ትርጓሜ ነው። ትርጓሜውም “አሰፋ” “ለጠጠ” “ዘረጋት” ማለት ነው። ምድር ዝርግ ናት ማለት ከAbsolute shape ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። አል-ራዚ (b.854 AD) ቁርኣን ምድርን ዘረጋት ሲል ዝርግ መሆኗን ያሳያልን ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ አሉ ❝ምድር ምንም ያክል ክብ እና ሉል “sphere” ብትሆንም የግዙፍ አካሏ ወለል ጠፍጣፋ ነው❞³ ኢብኑ ከሲርም ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት የሚለውን ቃል እንዲህ ይፈስራሉ ❝ይህም ማለት ሰዎች በውስጧ እንዲኖሩ አመቻቸት፣ አጠነከራት ማለት ነው❞⁴ ስለዚህ ምድር ተዘረጋች ሲባል ለሰዎች ምቹ መደረጓን፣ መለጠጧን፣ ሰፊ መሆኗን እንጂ ትክክለኛ ቅርጿን ለማመልከት አይደለም።⁵
ሸይኽ ወሊል ኢብኑ አብዱልራህማን ጥንታዊያን ሙስሊም ሊቃውንት በምድር ክብነት ላይ እንደሚስማሙ እንዲህ ይነግሩናል “the scholars affirm that it is round on the basis of sound evidence”⁶ እስኪ ከእነርሱ መካከል አንድ ሁለቱን ብቻ እንመልከት:-
▸ ኢብኑ ሐዘም (994– 1064 AD)
‟ምድር ክብ አይደለችም የሚሉ አንዳንድ ሙግቶች እንዳሉ ግልጽ ነው፣ እና ምድር ከብ ናት የሚል ምንም ማስረጃ የለም ብለውም ይናገራሉ። ይሁን እንጂህ የአላህ ማስረጃ ጠንካራ ነው። ከእኛ ቀደምት ሊቃውንቶች (ኢማሞች) መካከል አንድም ምድር ክብ አይደለችም ብሎ የሚክድ የለም። ይልቁኑ በቁርኣንና በሱና ውስጥ ያሉት ማስረጃዎች ክብ መሆኑን ይገልጻሉ።
(Al-Fasl fi’l-Milal wa’l-Ahwa’ wa’l-Nihal volume 2 pg 78)
▸ ኢብኑ ዘከሪያ “አል-ራዚ (854-925 AD)
‟ምድር ምንም ያክል ክብ ብትሆንም የግዙፍ አካሏ ወለል ጠፍጣፋ ነው”
(See reference Nŏ 3)
▸ ኢብኑ ተይሚያህ (1263–1328 AD)
‟…ምሁራን ምድር በላዩዋ ከያዘቻቸው መሬትና ባሕር ጋር እንደ ኳስ “ball” እንደሆነች በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል…ከአንዳንድ አላዋቂዎች በቀር ክብ አይደለም ብሎ የተናገረ ሰው አላውቅም።
(Majmoo‘ al-Fataawa of Ibn Taymiyyah volume 25/6 pg 195/586)
ታዋቂው የእስልምና የፈትዋ ድረገጽ እንዲህ ይላል ‟ምድር ክብ መሆኗን ዓሊሞች በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል። ነገር ግን ለሰው ዓይን ጠፍጣፋ ትመስላለች፣ ምክንያቱም በጣም ግዙፍ ስለሆነች ክብነቷ በቀላሉ አይታይምና።
(Islam Question & Answer 211655)
በእስልምና በኩል ያለው ይህን ይመስላል። እስኪ ይህንኑ ጥያቄ ለወገኖቻችን እናቅርብ፣ አላህ ምድርን መዘርጋቱ ጠፍጣፋነቷን ያሳያል ካለችሁ እግዚአብሔር ምድርን ዘረጋት ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ አስረዱን (ጥያቄው ኦርቶዶክስ ወገኖችን ብቻ የሚመለከት ነው፣ ባይብልም ከዚህ የተለያ አቋም እንዳሌለው ሌላ ጊዜ መመልከት እንችላለን)። አሁን ወደ ጥያቄው:-
‟…ምድርንም ያለካስማ የዘረጋት ለዘለዓለም እንዳትናወጥ ያጸናት እሱ ነው።”
— ድርሳነ ሚካኤል ዘወርኃ ሚያዚያ 8
‟ምድርን በባሕር ጀርባ ላይ የዘረጋት እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።”
— ድርሳነ መስቀል19፥19
‟…ምድርንም ያለመሠረት በውሃ ላይ እንደ አረንጓዴ የዘረጋት ያለ ገመድም በሰፈራት…እግዚአብሔር እናምናለን።
— ገድለ ተክለሀይማኖት 60፥2
ከእነዚህ መፅሐፍቶቻችሁ በመነሳት በእናንተ መረዳት መሰረት ምድር ጠፍጣፋ ናት ብንል ስህተታችን ምንድነው ?። ሌላው የምታነሱት ሙግት ዞሮ ወደ እናንተ ሲመጣ ፈጽሞ ልትቋቋሙት እንደማትችሉ ልታውቁ ይገባል። ይህን እኛ እንዳደረግነው መረጃን በማስረጃ አስደግፋችሁ ማብራራት የቤት ሥራችሁ ይሁን እያልኩኝ ኃያሉ አሏህ ሒዳያን እንዲሰጣችሁ እማፀነዋለሁ።
1] M. Mohar Ali, The Qur’an and the Orientalists, Jam’iyat ‘Ihyaa’ Minhaaj Al-Sunnah, p.75)
2] UNAVCO The Shape of Earth and Reference Ellipsoids
3] Tafsir Al Kabir by Al Razi Volume 19 pg 131
4] Tafsir Ibn Kathir volume 8 pg 307
5] Adwa’ al-Bayaan volume 8 pg 428
6] Fath al-Bayaan volume 8 pg 208
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


