ወንድም ሳላህ
‟ሪዷዓቱል ከቢር”رَضَاعَةُ الْكَبِيرِ ማለት “ጎልማሶችን ማጥባት” ማለት ሲሆን ግኑኝነት ሐራም የሚደረግበት መንገድ ነው። በእስልምና አንድ ወንድ እናቱንም ሆነ ያጠባችውን ሴት ማግባት እንደማይችል ጌታ አምላካችን በቁርኣኑ ተናግሯል (Qur’an 4:23)። መጋባት የሚፈቀድላቸው ሰዎች እንኳ እርሷ ወተቷን ካስጠባችው ያ ሰው በእርሷ ላይ እርም ስለሚሆን እንደ እናት እና ልጅ ይሆናሉ። አንድ ሰሊም የተባለው ሶሃቢይ ሰህላን ለመጎብኘት ወደ አቡ ሑዘይፋ ቤት መግባቱ ለባሏ ምቾት እንዳልሰጣው የተረደችው ሚስት ወደ ነቢዩ በመምጣት ስለ ጉዳዩ ነገረችያቸው።
عن عائشة قالت: جاءت سهلة بنت سهيل إلى النبي صلى الله عليه وسلم فقالت: يا رسول الله إني أرى في وجه أبي حذيفة الكراهية من دخول سالم علي. فقال ” أرضعيه” قالت: كيف أرضعه وهو رجل كبير؟ فتبسم وقال: “قد علمت أنه رجل كبير” ففعلت، فأتت النبي صلى الله عليه وسلم فقالت: ما رأيت في وجه أبي حذيفة شيئا أكرهه بعد
አዒሻህ (ረ.ዐ) እንደተረከችው አንዴ ሰህላ ቢንት ሱሃይል ወደ ነቢዩ (ﷺ) መጣችና እንዲህ አለችያቸው ‟የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ሰሊም ወደ እኔ ቤት በመምጣቱ የአቡ ሑዘይፋ (የባሌ) ፊት ላይ ጥሩን ነገር (አለመደሰትን) እያየሁ ነው፣ ምን ላድርግ?” አለች። እሳቸውም ‟አጥቢው” አሏት፣ እርሷም ‟እንዴ…ትልቅ ሰው እኮ ነው” በማለት መለሰች ይሄኔ የአላህ መልዕክተኛ እየሳቁ ‟ትልቅ መሆኑንማ አውቃለሁ እኮ” አሏት። ከዚያም የታዘዘችውን አደረገች። በሌላም ቀን ወደ ነቢዩ ተመልሳ ‟የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ከዚያ ቡኋለ እኮ በባሌ ፊት ላይ መጥፎን ገፅታ አይቼ አላውቅም” አለችያቸው።
(📘Sahih Muslim, 1453: Book 17, Hadith 33)
የአላህ መልዕክተኛ “አጥቢው” ብለው ሲናገሩ ለጎልማሳው ሰሊም ጡትሽን ስጪው ማለታቸው እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ምክንያቱም በእስልምና አንድ ወንድ የእርሱ ያልሆነችውን ሴት በእጁ መንካት አይፈቀድለትምና። ታድያስ አጥቢው ሲሉ ምን ማለታቸው ነው?…ጥቢውስ እንዴት ነው የሚፈፀመው?…የሚለውን በማስረጃ እንመልከት።
فَإِنَّ عِيَاضًا أَجَابَ عَنِ الْإِشْكَالِ بِاحْتِمَالِ أَنَّهَا حَلَبَتْهُ ثُمَّ شَرِبَهُ مِنْ غَيْرِ أَنْ يَمَسَّ ثَدْيَهَا
‟ዒያድ በጉዳዩ ዙርያ ተጠይቆ እርሷ ወተቷን አልባ በእቃ አድርጋ እንደሰጣችው፣ እርሱም ጡቷ ጋር ሳይደርስ ከእቃው እንደ ጠጣ ተናግሯል።
(📚ኢብኑ ሐጀር፤ ፈትሕ አል-ባሪ ክፍል 9 ገፅ 127)
كانت تحلب في مسعط أو إناء قدر رضعة فيشربه سالم في كل يوم حتى مضت خمسة أيام
‟ሰህላ ወተቷን በኩባያ ወይም በማሰሮ ውስጥ ታልብ ነበር፣ ሰሊምም ለአምስት ቀናት ከዚያ ውስጥ ወተቱን ይጠጣ ነበር።
(📚አስ-ሱዩጢ፤ ሙስነድ አዒሻህ ገፅ 91)
ኢብኑ ቁተይባ (b. 829) እንዲህ በማለት ይናገራል:- ❝እርድዒሒ (አጥቢው) ማለት ልክ ለህጻናት እንደሚሰጣው ጡትሽን በአፉ ውስጥ አድርጊ ማለት አይደለም። የተፈለገበት ወተትሽን አልበሽ ይጠጣ ዘንድ በእቃ ስጪው ማለት እንጂ ሌላ መልዕክት የለውም። ለሰሊም የእርሷን ጡት መንካት አይገባውም። ከመሰረቱ ለእርሱ ያልተገባው ነገር እንዴት ይፈቀድለታል ? እርሱ ዘንድ የፍትወት ስሜት መኖሩን አያምንም ነበር ? ይህን ትርጓሜ ይበለጥ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርገው የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) አጥቢው ብለው ባዘዟት ጊዜ እርሷ ደንግጣ ነበር፣ የእሳቸው በድንጋጤዋ መሳቅ ነገሩ እሷ እንዳሰበችው እንዳልሆነ አንዱ ማሳያ ነው።❞
(📚ተዕዊል አል-ሙኽተሊፍ ቅፅ 1፣ ገፅ 437-8)
لعله صلى الله عليه وسلم تبسم على زعمها أنها أمرت بإرضاع سالم بن ثديها، مع أنه صلى الله عليه وسلم أراد أن تحلب له، فيشرب منه، وإنها فهمت ذلك من تبسمه أو بتصريحه عليه السلام بعد ذلك،
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ከንግግሯ ፈገግ ያሉት እርሷን ከጡጥሽ አጥቢው ያሉአት ስለመሰላት ነው። ነገር ግን እሳቸው የጠየቁት ትንሽዬ ወተት አልባ በእቃ እንድትሰጠው ብቻ ነበር። ቡኋለም ከፈገግታቸው ነገሩን መረዳት ችላለች።
(📚ተክሚለህ ፈትህ አል-ሙልሂም ቅፅ 1፣ ገፅ 71)
ከአስ-ሰዩጢ እና ከሌሎችም የሐዲስ መዛግብቶች እንደምንረዳው ሰህላ ለሰሊም ከጡቷ ሳይሆን በእቃ ወተቷን ስትሰጠው እንደነበር ነው። የአላህ መልዕክተኛም ያዘዙት ይህንኑ ነበር። አጥቢው ማለት ግዴታ ከጡትሽ ስጪው ማለት አይደለም። ይህ አይነቱ አነጋገር በዓረቦች ዘንድ የተለመደ ነው።
واسم الرضاع لا يقف على الارتضاع من الثدي فإن العرب تقول يتيم راضع وإن كان يرضع بلبن الشاة والبقر
‟ረደዓ” የሚለው ቃል ግዴታ ከጡት ውስጥ መጥባትን አያመለክትም። ዐረቦች የከብትን ወይም የበግን ወተት ለሚጠጣ ሰውም “ረደዓ” (ጠባ) ይላሉና።
(📚አል-በዲዕ አስ-ሰንዒይ ቅፅ 4፣ ገፅ 8)
ስናጠቃልል:- ጎልማሶችን ማጥባት ሲባል ትንሽዬ ወተትን ከጡት ውስጥ አልቦ መስጠት እንጂ እንደ ህጸናት በራሳቸው ላይ አስቀምጦ እሽሩሩሩ እያሉ ጡት ማስጠባት አይደለም።
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


