ወንድም ሳላህ
‟እኔ የተላኩት መልካም የሆነ ሥነ-ምግባራዊ ባሕርይን ለሟላ ነው።”إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ صَالِحَ الْأَخْلَاقِ
(ሙሰነድ አህመድ 8729፣ ሶሂህ አል-ጃሚዕ 2349)
የነቢዩን ሐያዕ እና ውብ ሥነ-ምግባር ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት እና ለማደብዘዝ ሌት-ከቀን የሚሰሩ አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት በርካታ የሕይወት ታሪካቸውንና ንግግራቸውን ከማጥመምም አልፈው ሐዲስ እስከ መፈብረክ እንደ ደረሱ ይታወቃል። ሐሰተኛ ነው የሚሉትን ነቢይ በእውነት ሚዛን ሐሰተኛ ማድረግ ስላልቻሉ መሰረት አልባ ክሶችን ማዘውተር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከእነርሱ መካከል ከታች የሚገኘውን ሐዲስ በማጥመም ነቢያችሁ የብልግና ቃል ተናግረዋል ይላሉ:-
كنا نؤمر إذا رجل تعزّى بعزاء الجاهلية فأعِضّوه بِهَنِ أبيه ولا تَكْنُوا
አንድ ሰው በዘመነ-ጃሒልያ ጊዜ በነበረው (ዘር/ስርዓት) ከተኩራራ የአባቱን “ነገር” (ብልት) ንከስ ብለን እናዘው ነበር፣ በምሳሌያዊ ንግግርም አታናግሩት።
(ተኽሪጅ አል-ሙስነድ አህመድ 21236)
رَأَيْتُ عِنْدَ أُبَيٍّ رَجُلاً تَعَزَّى بِعَزَاءِ الْجَاهِلِيَّةِ، فَأَعَضَّهُ أُبَيٌّ وَلَمْ يُكْنِهِ، فَنَظَرَ إِلَيْهِ أَصْحَابُهُ، قَالَ: كَأَنَّكُمْ أَنْكَرْتُمُوهُ؟ فَقَالَ: إِنِّي لاَ أَهَابُ فِي هَذَا أَحَدًا أَبَدًا، إِنِّي سَمِعْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ: مَنْ تَعَزَّى بِعَزَاءِ الْجَاهِلِيَّةِ فَأَعِضُّوهُ وَلا تَكْنُوهُ
ኡበይ ዘንድ በዘመነ-ጃሒልያ የሚኩራራን ሰው አየሁ፣ ኡበይም በግልጽ እንዲነክስ ነገረው (አስነወረው) ሕዝቦቹም ወደ እርሱ ሲመለከቱ ‟ምነው አልወደዳችሁትም ?፣ እኔ ለእንደዚህ አይነት አካል ምንም ውዴታ (አክብሮት) የለኝም። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁና ‟በዘመነ ጃሒሊያ ጊዜ በነበረው (ዘር/ስርዓት) የሚኩራራን ሰው ካያችሁ ንከስ በሉት በስውር ንግግርም አታውሩት።”
(📗Al-Adab Al-Mufrad, 963: Book 41, Hadith 12)
በእርግጥ ሚሺነሪዎች ይህን ሐዲስ በዚህ መልክ አይደለም የሚያሰራጩት፣ ለመስማት በሚከብዱ የብልግና ቃላት አጅበው እንጂ። ለማንኛውም:-
1- ሐዲሱ በኢስላም ጠላቶች ተተርጉሞ እንደሚሰራጨው የብልትን ስም ቀጥታ የተጠቀሰበት አንድም ሐረግ የለም። አይደለም ‟ቊ” ብሎ ሊናገር ይቅርና ሻል ባለው አነጋገር ብልት ብሎ እንኳ አልገለፀም። ሚሺነሪዎች ‟ቁ” ብለው የተረጎሙት የዐረብኛው ቃል “ሂና”هِنَّ ሲሆን ቀጥተኛ ትርግሙ “ነገር” thing ማለት ነው። በዚህ ዐውድ ውስጥ “ብልትን” ለመግለጽ የመጣ Euphemism የሆነ ንግግር ነው። በአጭሩ ቃሏ በግልጽ ስሙ የማይጠራውን ማንኛውንም ነገር ለመወከል ግልጋሎት ላይ የምትውል “metonymy” ናት። ሐዲሱ የትኛውንም የመራቢያ አካል ስሙን በግልጽ ጥሬ ቃል አይጠቅስም። ይህ ማለት ስለ አባቱ ብልት አይናገርም ማለት አይደለም።
2- የአባቱን ብልት መጥቀሱ ወይም እንዲነክስ መንገሩ ለምን አስፈላገ ? ከተባለ ለተግሳጽ መሆኑን ኢብኑል ቀይም እንዲህ በማለት ይናገራሉ። ❝ለዚህ በጃሒልያ ዘመን በነበረው ስርዓት ለሚኩራራ ኩራተኛ የአባቱን ብልት መጥቀስ የወጣበትን (የእርሱን ግኝት) እንዲያስታውስ ያደርገዋል❞ (ዛዱል መዓድ 2/400) ስለዚህ ለደናቁርት ይህን ቃል መናገር ሚሺነሪዎች እንደሚቀጥፉት ደረቅ የሆነ ስድብ ሳይሆን መልዕክት አዘል የሆነ ተግሳጽ መሆኑን ከዚሁ መረዳት እንችላለን።
3- ስድብ ያልሆነው እንዴት ነው ? ከተባለ:- መጀመሪያ ስድብ ማለት በየመንገዱ ለየትኛውም አካል በስሜት ተነሳሽነት የምንናገረው ጸያፍ ቃል ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ መናገር ለሚችል ሰው “ዲዳ” ፣ ለሚሰመው ደግሞ “ደንቆሮ” ብለው ለሚመለከት ሰው “ዐይነ-ስውር” ብል ይህ ስድብ ይሆናል። ነገር ግን ዲዳ፣ ደንቆሮ፣ ዐይነ-ስውር ለሆኑት አካላት እነዚህን ስያሜዎች ብጠቀም ስድብ ሊሆን አይችልም። ልክ እንደዚሁ የሐዲሱንም መልዕክት ለማንም መጠቀም ከስድብ ይቆጠራል፣ ነገር ግን ለእነዚያ ሴት ልጅ በሕይወት በምትቀበርበት ስርዓት የሚኩሯሩትን አካላት በዚህ ቃል ማስነወር በፍጹም ከስድብ ሊቆጠር አይችልም።
4- ማስነወርስ ቢሆን ለምን ተፈቀደ ? ይህ በመልካም ጠባይ ላይ ነህ ከተባለው ነቢይ ይጠበቃል ወይ ? ከተባለ እነሆ:- መግደል እርም ሆኖ ሳለ በጦር ሜዳ ተፈቅዷል፣ ኸምር እርም ሆኖ ሳለ ተጠምቶ በሞት አፋፍ ላይ ለሆነ ሰው ተፈቅዷል፣ እንደዛው ይህ ንግግር እርም ሆኖ ሳለ በጃሒሊያ ስርዓት የሚመራውን ሰው በሚገባው ቋንቋ ለማናገር ተፈቅዷል። በዚህ ንግግር ሌላውን ማሸማቀቅ እና ልኩን እንዲያውቅ ማድረግ ከነቢዩ ውልደት በፊትም በዓረቦች ዘንድ ይታወቅ ነበር (ሲራ አል-ነበዊያህ ለኢብኑ ከሲር 1/85) ስለዚህ በእነርሱ የመግባቢያ ቋንቋ ከእነርሱ ጋር ማውራት በፍጹም ስድብ ሊባል አይችልም፤ ሲቀጥል በታላቅ ጠባይ ላይ የሆነ ሰው «እንዴት ወንጀለኛ ነብስን ይገድላል?» «እንዴት ተጠምጥል ኸምርን ይጠጣል?» «እንዴት ወሰን ባለፈ ሰው ላይ ወሰንን ያልፋል?» ብሎ መክሰስ ይቻላል እንዴ? አይቻልም እሱ ንግግርም በማን ላይ መናገር እንዳለብን ተነግሮናል ከጠባይ ጋርም አይገናኝም !
ታላቁ የመካከለኛው ዘመን ሊቅ አል-ሒራዊ እንዲህ በማለት ያብራራሉ:- ❝በጃሒልያ ዘመን ወደ ነበረው የድንቁርና ስርዓት እራሱን የሚያስጠጋ፣ የስድብ እና የመርገም ልማዳቸውን በመከተል በእነዚያ ጸያፍ ቃላትና ክራት ሊያሸማቅችሁ ለመጣ ማንኛውም አካል የአባቱን ብልት (ምንጩን)፣ አምልኮተ ጣዖቱንና የዝሙት ሱሳቸውን እንዲሁም ስካራቸውን በግልጽ ጥቀሱለት ይህ ለእነርሱ ተግሳጽ ይሆናልና።❞
(📗አሊ ቃሪ፤ ሚርቀት አል-መፋቲህ 7/3076)
5- የአላህን መልዕክተኛ የሕይወት ታሪክ ያነበበ ማንኛውም ሰው እሳቸው አይደለም እንዲህ ያለ ቃል ለስድብ ሊጠቀሙ ይቅርና ለአስተምህሮ እንኳ ህፍረተ-ሥጋን በስም መጥቀስ በጣም ያፍሩ እንደነበር ይገነዘባል። እስኪ አንድ ታሪክ እንመልከት:-
عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ امْرَأَةً، سَأَلَتِ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم عَنْ غُسْلِهَا مِنَ الْمَحِيضِ، فَأَمَرَهَا كَيْفَ تَغْتَسِلُ قَالَ خُذِي فِرْصَةً مِنْ مِسْكٍ فَتَطَهَّرِي بِهَا قَالَتْ كَيْفَ أَتَطَهَّرُ قَالَ تَطَهَّرِي بِهَا قَالَتْ كَيْفَ قَالَ سُبْحَانَ اللَّهِ تَطَهَّرِي
ከአዒሻህ (ረ.ዐ) እንደተተረከው፤ አንዲት እንስት የአላህን መልዕክተኛ (ﷺ) ከወር አበባዋ ቡኋለ እንዴት መጽዳዳት እንዳለባት ጠየቀቻቸው። እሳቸውም ‟ሚስክ ያለው ቁራጭ ልብስ ወስደሽ በእርሱ እራስሽን አፅጂ” አሏት። እርሷም “እንዴት ላጽዳ?” አለችያቸው እሳቸውም ‟በእርሱ አፅጂው” አሏት፣ አሁንም “እንዴት ነው የማጸደው?” ብለ ጠየቀች፣ እሳቸው ‟ሱብኃን አሏህ በጨርቁ አጽጂው” ብለው መለሱላት።
(📗ኢማም አል-ቡኻሪ 314: መፅሐፍ 6, ሐዲስ 19)
ተመልከት ! የአላህ መልዕክተኛ አይደለም ለተራ ነገር ይቅርና ለዚህ እጅግ አስፈላጊ ትምህርት እንኳን የብልትን ስም ጠርተው እንዲህ አድርጊ ብለው ከመናገር ያፍሩ ነበር። ለትምህርት ቃሉን ከመጠቀም የሚፈራ (የሚቆጠብ) ነቢይ እንዴት ለስድብ ይጠቅመዋል ተብሎ ይከሰሳል ? የአላህ መልዕክተኛ ከድንግል ሴት በላይ ዓይናፋር መሆናቸውን አታውቁምን ?
عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم أَشَدَّ حَيَاءً مِنَ الْعَذْرَاءِ فِي خِدْرِهَا.”
አቡ ሰዒድ አል-ኹድሪይ:- የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) በዓይነ-ዕርግቧ ውስጥ ካለች ድንግል ልጃገረድ በላይ ዓይናፋር ናቸው።
(📗ኢማም አል-ቡኻሪ 3562: መፅሐፍ 61 ሐዲስ 71)
፨ ማጠቃለያ:- ሐዲሱ ላይ የአላህ መልዕክተኛ የትኛውንም የመራቢያ አካል ስም አልጠቀሱም። ሌላው ቀርቶ “ብልት” የምትለው ቃል እንኳ በማብራሪያ ደረጃ እንጂ በሐዲሱ ውስጥ አትገኝም። ንከስ ያሉት ስለ ብልት መሆኑን ያወቅነው በራሱ ቃል በቃል ከነቢዩ ንግግር ላይ ሳይሆን ከእርሱ ደቀመዛሙርት ሀሳብ ነው። የአባቱን ብልት እንዲነክስ በመናገር ሌላውን ማሸማቀቅ እና መግሰጽ ቅድመ ሙሐመድ የሚታወቅ አነጋገር ቢሆንም የአላህ መልዕክተኛ ይህን ቃል ለየትኛውም አካል ከመሬት ተነስታችሁ ያለምክንያት ተናገሩ ብለው አላዘዙም። የተፈቀደበት ዐውድ ቢኖርም በዚያ አውድ ይህ ንግግር ስድብ አለመሆኑን አሳልፍናል። ወሰላሙ አሌይኩም።
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


