ወንድም ሳላህ
ብሪታንያዊው የታሪክ ጸሐፊና ሚሺነሪው ዊልያም ክሌር በ1905 በጻፈው “The Original Sources Of The Qur’an” በተሰኘው መጽሐፉ ላይ ነቢዩ ሙሐመድ ከቀደሙት መጽሐፍት ማለትም ከአይሁዳውያን ጹሑፍ፣ ከባይብል፣ ከዞርስትያንስ፣ ከሳቢያኖች እና ከጣዖታዊያን ኮርጀዋል በማለት የተለመደውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ከፍተው ከደሰኮሩ ክርስቲያኖች መካከል አንዱ ሲሆን እርሱም እንደ ቀደሙት ተቺዎች ሞተው ከበሰበሱት ውስጥ ነው። ለነቢያችን የመጣው መገለጥ ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ እንደሆነ ቁርዓን ይነግረናል [1] ከሃዲዎች ከነቢያችን ዘመን ጀምረው ቁርዓንን ላለመቀበል ከሚያቀርቧቸው ማስተባበያዎች ውስጥ አንዱ ቁርዓን ከሌላ መጽሐፍ ዘንድ ኮርጇል የሚለውን ጸለምተኛ ክስ ነው:: [2] ወደ ርዕሳችን ስንመለስ ይህ ብሪታንያዊው ተቺ ከላይ በተመለከትነው መጽሐፉ ላይ “ቁርዓን የአዳምን ሁለት ልጆች (ሀቢል እና ቃቢልን) ታሪክና ንግግር ከአይሁዳውያን ጹሑፍ ማብራሪያ ማለትም ከ “ታርጉም ዮናታን” እና ከ “ታርጉም የሩሰሌም” (Pirqey Rabbi Eli’zer” እና “Mishnah Sanhedrin) የተኮረጀ ነው በማለት እንዲህ ብሎ ይጽፋል ‟conversation, or rather argument, between Cain and Abel is mentioned in Jewish legend both in the Targum of Jonathan 14 and in the Targum of Jerusalem” [3]
ከእርሱም ውጪ “ኢብኑ ወረቅ” በሚለው የብዕር ስም የሚንቀሳቀስ ሚሺነሪ እንዲህ በማለት ሐሳቡን ለማጠናከር ሞክሯል ‟The murder of Abel in the Koran is borrowed from the Bible, but the conversation of Cain with Abel before Cain kills him is taken from the Targum of Jerusalem, generally known as pseudo-Jonathan. In the Koran, after the murder God sent a raven that scratched the earth to show Cain how to bury Abel [4] ከእነዚህ ሁለቱ ውጪም ብዙ የክርስቲያን ሰባኪዎች እንደነ “አነስ ሸሮሽ” [5] “አብዲየ አክበር” [6] “ማቲን ኤላስ” [7] “ኖርማን ጊስለር” [8] የመሳሰሉ ሚሺነሪዎች ይህንን ዲስኩር (ሐሰተኛ ክስ) መክፈታቸው ይታወቃል።
ታድያስ ቀጥታ ወደ ምላሹ ስንገባ ቁርዓን ከአምላክ ዘንድ የሆነ ግልጠተ መለኮት በመሆኑ ከየትኛውም ጹሑፍ ላይ አልኮረጀም፣ ክርስቲያን ሚሺነሪዎች ቁርዓን ኮርጇል ብለው የጠቀሱት በሱረቱል ማዒደህ 5:27-32 ላይ የሰፈረው ሀሳብ ከ “Talmud Jerusalem” (Mishnah Sanhedrin) ነው ብለው እንደነበር ተመልክተናል፣ ግልጽ ለማድረግ ያክል “ታልሙድ” תַּלְמוּד የረባናዊያን አይሁዶች ሥነ-መለኮት እና ዋና ምንጭ ሲሆን በውስጡ ሁለት አበይት መዛግብቶችን ይዟል እነርሱም “Babylonian talmud” እና “Jerusalem talmud” ይባላሉ፣ ሁለቱም በውስጣቸው ብዙ ጹሑፎችን ይዘዋል ለምሳሌ “Jerusalem talmud” በሚለው ስብስብ ውስጥ ወደ 39 የሚጠጉ ጹሑፎች ሲኖሩ “Jerusalem talmud sanhedrin” “Jerusalem talmud barakhot” Jerusalem telmud demai” “Jerusalem talmud sheva’it”….ወዘተ ይጠቀሳሉ። አሁን ዋና ነጥቡ የ “ኢየሩሳሌም ታልሙድ” ጸሐፊ ማነው ብለን ስንጠይቅ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም፡ ነገር ግን በ16ኛው ክፍለዘመን AD ላይ መጽሐፉ በሕትመት ስራ ላይ ሳለ በሽፋኑ ላይ ጸሐፊው “Yonatan ben Uziel” የሚባል ሰው ነው ብለው የፈረጁ ሲሆን ምሁራን ግን መጽሐፉን ሲጠሩት “Targum Pseudo-Jonathan” (ሐሰተኛው የዮናታን ቅጂ) ብለው ነው::
የዚህን የአይሁዳውያን መጽሐፍት ስብስብ “Targum Pseudo-Jonathan” እድሜ በተመለከተ አንዳንድ ምሁራን ከ9-10ኛው ክፍለዘመን AD ቢሉም እውነታው ግን እስከ 14ኛው AD እንደሚያስጠጋው የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ እስኪ ከእነርሱ መካከል አንድ ሁለቱን እንመልከት:- Professor Michael Maher በ1992 ስለ “Targum Pseudo-Jonathan” በጻፈው መጽሐፍ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል ❝የየሩሰሌም ታልሙድ (ዮናታን) ጹሑፎች ስብስብ ስለ ጥንት ነገሮች ለመጻፍ ቢሞክርም በውስጡ ያሉት ታሪኮች ግን እስከ መጨረሻ የአረብ ድል እንደተጻፈ ያሳያሉ፣ Professor D.M spankly እነዚህ ጹሑፎች ከ9-10 ክፍለዘመን የተጻፉ ናቸው ብሎ እንዲያምን ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ በ”Ps.-J. Gen. 21:21″ ላይ የነቢዩ ሙሐመድን ሚስቶች በስም በመጥቀሱ ነው….The findings of these and other scholars who have dedicated special studies to both the content and the language of Ps.-J. allow us to accept with confidence the view that this Targum in its final form cannot be dated before seventh or eighth century…እነዚህ እና ሌሎች ምሁራዊ ጥናቶች እነዚህ ስብስቦች ከስምንተኛ ክፍለዘመን በፊት ሊጻፉ አይችሉም የሚለውን አመለካከት በልበሙሉነት እንድንቀበል ያስችለናል❞ [9] በብሉይ ኪዳን የእጅ ጹሑፎች እና እደክታባት ላይ ከሚሰሩት ምሁራን ውስጥ አንዱ የሆነው “Dr.Leeor Gottlieb” እነዚህ ጹሑፎች በ12ኛው ክፍለዘመን እንደተጻፉ ይነግረናል [10]
እንደው ሌላው ይቅርና በ1995 የታተመው የአይሁዳውያን መድበለ እውቀት “Talmud Jerusalem” በፍጹም ከ7ኛ ክፍለዘመን በፊት መሆን እንደማይችል ጽፈዋል “is not earlier than the seventh century” [11] ምንም ያክል አንዳንዶቹ የ 5ኛ ክፍለዘመን ጹሑፍ ነው ቢሉትም በውስጡ የያዛቸው የቅርብ ግዜ ክስተቶች በፍጹም ያንን እንዳንቀበል ያደርጉናል። የሚገርመው ደግሞ ይህ የአይሁዳውያን ጹሑፍ ስብስብ ውስጥ ሰዎች ተነስተው የፈለጉትን እንጨመሩበት እና እንደ ቀነሱት እንዲሁም እንደቀያየሩት የዘርፉ ምሁራን በግልጽ ይናገራሉ [12]
ነቢያችን እንዴት አድርገው ነው ከእሳቸው ቡኋለ 500 ዓመታት አስቆጥሮ ከተጻፈው መጽሐፍ ላይ የሚገለብጡት ? ነጥቡን ለማጥበብ በሚለው ነው እንጂ እነርሱ እንዳሉት ያ መጽሐፍ ከነቢያችን በፊት ነው ብለን ራሱ ነጥብ በነጥብ ብንመለከት ተኮረጀ የሚያስብል ምንም ነገር አናገኝበትም።
❐ ማጠቃለያ (Conclusion)
➛ የቁርዓን አመንጪ እራሱ አላህ ነው፣ ቃሉም ሆነ ንግግሩ የእርሱ ብቻ ነው፣ የተወረደውም ከአለማት ጌታ ከአላህ ነው።تَنزِيلَ الْعَزِيزِ الرَّحِيمِ
‟አሸናፊ አዛኝ ከሆነው አምላክ መወረድን ተወረደ (Qur’an 36:5)
ነቢያችን አይደለም ከሌላ ባዕድ ነገር ሊገለብጡ ይቅርና ከአላህ ዘንድ ተንዚል የሚሆነውን ሐዲሰል ቁድሲይን እንኳ ከቁርዓን ጋር አይደባልቁትም ነበር። ከማንኛውም ሰው በላይ ነው ቁርዓን ላይ ጥንቃቄ የሚያደርጉት፣ ነቢዩ ከሌላ ባዕድ ነገርይቀዱ ነበር ብሎ ማሰብ በራሱ ቂልነት ነው። ሌላው ደግሞ ሚሺነሪዎች ከ”Jerusalem Talmud” ላይ ገለበጡት ያሉት ጹሑፍ በነቢያችን ዘመን እንዳልነበርና ከእሳቸው ቡኋለ 500 ዓመታት ያስቆጠረ ጹሑፍ መሆኑን አይተናል፣ አይደለም ከነቢያችን በፊት ሊሆን ይቅርና ለነቢያችን ትንሽ የተጠጋ እደ-ክታብ “Manuscript” ዛሬ እጃችን ላይ የለም፣ ጹሑፉም ቢሆን በምሁራን ጥናት የቅርብ ግዜ መሆኑን ተረጋግጧል ስለዚህ ይህ ክሳቸው ገለባ መሆኑን በቀላሉ መረዳት እንችላለን።
📗ማጣቀሻዎች “References” (የተወሰኑት ከIslamic Awareness የተተረጎሙ ናቸው)
[1] Qur’an suratul Fussilat 41:2
[2] Qur’an Suratul Anfal 8:31
[3] Rev. W. St. Clair Tisdall, The Original Sources Of The Qur’an, 1905, pp. 62-66
[4] Ibn Warraq, Why I Am Not A Muslim, 1995, Prometheus Books: Amherst, NY, p. 57
[5] Dr. A. A. Shorrosh, Islam Revealed: A Christian Arab’s View Of Islam, 1988, pp. 201-203.
[6] Abdul-Haqq, Sharing Your Faith With A Muslim, pp. 41-42.
[7] M. Elass, Understanding the Koran: A Quick Christian Guide To The Muslim Holy Book, 2004, Zondervan: Grand Rapids (MI), pp. 102-103
[8] N. L. Geisler & A. Saleeb, Answering Islam: The Crescent In The Light Of The Cross, 1993, Baker Books: Grand Rapids (MI), p. 309
[9] Targum The Universal Jewish Encyclopaedia, 1969, Volume 10 p 174
[10] Leeor Gottlieb, Aramaic Studies 191 (2021).pp. 104-120
[11] E. G. Clark, Targum Pseudo-Jonathan: 1998, p. 3
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


