“ክርስቶስ ሞትን ድል ነስቷል” የሚለውን ቃል እየደጋገመ እንደሚፎክር ሰባኪ የሚያሳዝነኝ ፍጡር የለም። ግለሰቡ የዚህ እምነቱ “ድንቅነት” ያስገረመበት ምክንያት ኢየሱስን አስመልክቶ ያለው ምልከታ በጥርጣሬ ወጀብ የተመታ ስለሆነ ነው። ከመነሻው ፈጣሪ ሞት የሚባለውንና እራሱ የፈጠረውን ነገር ማሸነፉ ምኑ ነው እንደ ትልቅ ጀብድ የእድሜ ልክ የሰበካ ርዕስ የሚሆነው? ምናልባት በሰባኪው ልቦና ውስጥ የኢየሱስ ቦታ የተደናገረ ደረጃ ካለው (ፍጡር ወይንስ ፈጣሪ የሚለው) ክስተቱን ቢያገዝፈው አይደንቅም። አንድ ፍጡር ሞትን ድል አድርጎ ቢነሳ የምርም ይገርማል፤ በዚህ መሀል በጥርጣሬ ለሚዋልል ሰው የኢየሱስን ከሞት መነሳትን ማመን እንደ ትልቅ ነገር ቢመለከተው ግን አይገርምም።
Category: የኦርቶዶክስ መጽሀፍት
“ልበ አምላክ” ዳዊት
ዳዊት ንጉስ ብቻ አልነበረም “ልበ አምላክ” ሳይቀር የተባለለት ፃድቅ ሰው ነበር። መጽሀፍ ቅዱስ በእርግጥ ስለ ዳዊት ሲነግረን አይደለም ጻድቅ ይቅርና ተራ አማኝ እንኳን እንዳይመስለን አድርጎ በሀጥያት አጨማልቆ ነው የገለፀልን። የሰው ሚስት ከጋብቻ ውጭ ማማጋጡ ሳይቀር የተረገዘው ልጅ የባሏ እንደሆነ ለማስመሰል ጦር ሜዳ የነበረውን ባሏን አስመጥቶ ከሷ ጋር እንዲተኛ ሊያግባባው ሞከረ። ባሏ ግን ጓዶቹ ጦርሜዳ ሁነው እሱ ምቾትን እንደማይፈልግ በመግለፅ ራሱን ማቀቡን ገለፀ። መጨረሻ የወሰደው እርምጃ ታዲያ ባሏን እንዲገደል ማድረግ ነበር። ይህ የምነግራችሁ ታሪክ ተራ የልቦለድ ድርሳን ውስጥ ያለ ሳይሆን መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ በ2ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 11 ጀምሮ የተተረከ ታሪክ ነው።
ምስጢረ-ሥላሴ
“ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርዕስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ባሳተሙት መጽሀፍ ገፅ 37 ላይ የሚከተለው ቃል ሰፍሮ ይገኛል። እንደ እሳቸው ገለፃ መሠረት ምስጢር ማለት ድብቅ ወይንም ሽሽግ ማለት ሲሆን በሀይማኖታዊ እሳቤው ደግሞ የሰው ልጅ አእምሮ አስቦና መርምሮ የማይደርስበት ማለት ነው። እዚህ ውስጥ “ምስጢረ ሥላሴ” እንደሚካተተም ገልፀዋል። እንደ አንድ የንፅፅር ሰው የሚከተሉትን ጥያቄዎች ማንሳት አስፈላጊ ነው…




