«ሉቃስ ማለት የጳውሎስ ተማሪ ጋደኛው የነበረና የሕክምና ሙያ ጭምር የነበረው ሰው ነበር። ጳውሎስም ኾነ ሉቃስ ኢየሱስን አያውቁትም በዘመናቸውም አልተገናኙም። ይሁንና የዚህ የጳውሎስ ጓደኛ የሆነው ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈበትን ዘመን ምሁራን እንደሚያስቀምጡት ከ80-90 AD እንደተዘጋጀ ይናገራሉ። እስከ 110 AD ያደረሱትም አልጠፉም። ይህ የመጀመሪያው ቅጂ {manuscript} ጽሑፍ ደብዛው ጠፍቷል ምኑም የለም። ዛሬ ላይ የዚህ ወንጌል ቀዳማይ ጽሑፍ {Manuscript} አለ የሚባለው በ 250 AD ላይ የተዘጋጀ ፓፒረስ 75 {Papyrus 75} ነው።
Category: ክርስትና
የማርቆስ ወንጌል
የማርቆስ ወንጌል «ከአራቱ ወንጌላት መካከል የመጀመሪያውና በቀዳሚነት እንደተጻፈ የሚታመነው የማርቆስ ወንጌል ነው። ይህ ወንጌል ከ66- 70-4) AD ባሉት ጊዜያት እንደተጻፈ ይገመታል። ምሁራን አራቱም ወንጌላት ጸሐፊያቸው በእርግጠኝነት አይታወቅም ይላሉ። አክለውም ጸሐፊዎቹ የኢየሱስ ሐዋሪያት ወይም የዘመኑ የአይን- ምስክሮችም አይደሉም ይልቁንስ ዛሬ ላይ ያለው ስያሜያቸው በ2ኛው ክፍለ ዘመን ላይ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አባቶች የተሰየሙ ባዶ ስያሜዎች ናቸው ይላሉ።…
እውን ክርስትና መጤ አይደለምን?
እውን ክርስትና መጤ አይደለምን?




