ወንድም ሳላህ
በክፍል አንድ አርቲክል ላይ አዒሻህ በአካልና አዕምሮ የበሰለችና ለአቅመ-ሔዋን የደረሰች እንስት መሆኗን እንዲሁም ጋብቻው እንዲፈጸም የተወሰነው በጉልምስና እንድሜዋ ወቅት እንደሆነ ሐዲሶችንና እስላማዊ ምንጮችን እያጣቀስን አይተናል። ልጃገረዶች በልጅነት እድሜያቸው እንደሚያገቡ የማያውቁ (ወይም እያወቁ የሚቀጥፉ) ሰዎች የአዒሻን ትዳር እንደ አዲስ ክስተት በመመልከት እያጋነኑ ጉዳዩን ያልተለመደ መጥፎ ልማድ በማስመሰል “over exaggeration fallacy” ሲፈጽሙ ማየት የተለመደ ነገር ነው። ይህ ፋላሲ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ተጨማሪ ምክንያትና ተጽዕኖዎችን በማካተት ነገሩ መጥፎ እንደሆነ አድርጎ በማጋነን ለታዳሚ የሚቀርብ ህጸጽ ነው። አዒሻህ በትዳሯ ደስተኛ እና ፍቃደኛ ሆና ሳለ የተበደለች በማስመሰል፣ ለአካላዊ እና ሞራላዊ ብስለት እጅጉን ብቁ ሆነ ሳለ ያልደረሰች አድርጎ በማቅረብ፣ አባቷ እና እናቷ ተስማምተው ለነቢዩ አጭተዋት ሳለ ነቢዩ በጉልበት ያገቡዋት በማስመሰል፣ በእስልምና ድንግል ልጅ በፍቃዷ ቢሆን እንጂ ከእርሷ ጋር ግኑኝነት ማድረግ ክልክል እንደሆነ ነቢዩ አስተምረው ሳለ አዒሻህ የተደፈረች በማስመሰል እንዲሁም ልጃገረዶችን በልጅነት እድሜያቸው ማግባት ከነቢዩ በፊት በሰፊው የሚታወቅ ልማድ ሆኖ ሳለ እርሳቸው ያመጡት አዲስ (እንግዳ) ነገር አድርገው በማቅረብ ጭፍንተኝነታቸውን በአደባባይ አሳይተዋል።
በዚህ ጹሑፋችን ላይ ልጃገረዶች በልጅነት (ከ6-12 ባለው እድሜያቸው) እንደሚያገቡ ከቀደሙት ሀይማኖቶች ማለትም ከሂንዱዝይም፣ አይሁዳውያን፣ ክርስትና በተጨማሪም ይህ ከታሪክ አንጻርም የተለመደ እና እንግዳ ያልሆነ ተግባር እንደሆነ በማስረጃ እናያለን። እስኪ ከታሪክ እንጀምር፣ ከመካከለኛው ክፍለዘመን ቡኋለ የጋብቻ ጣሪያ እድሜው (Marriageable age) ስንት እንደሆነ በሀገረ ብሪቲሽ የሶሺዮሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆነችው ሲኒካ ኤልኮት በመጽሐፏ ላይ እንዲህ ትላለች ❝የጋብቻ ጾታዊ ግኑኝነት እድሜን በተመለከተ ለምሳሌ በቅኝ ግዛት ወቅት ከ 7 ዓመት ወደ 10 ብሎም ወደ 12 ከፍ ያለ ሲሆን በመጨረሻው በ18ኛው ክፍለዘመን ወደ 14 አድጓል❞
(Not My Kid: What Parents Believe about the Sex Lives of Their Teenagers By Sinikka Elliott page 14-15)
‟በቅኝ ግዛት ዘመን እንደ ብሪትሽ ያለ ሀገራት (የጋብቻ እድሜ) የጋራ ስምምነት ህግ 7 ዓመት ነበር”
(American Families Past and Present: Social Perspectives on Transformations by Susan M. Ross page 40)
ፕሮፌሰር አርተር ሲካን በመጽሐፉ ላይ እንዲህ ይላል ❝በዓለም ዙሪያ ለፆታዊ ግንኙነት የሚፈቀደው እድሜ የጎሳው ባህላቸው ላይ የተመረኮዘ ነበር…ኤድዋርድ ኮክ በ17ኛው ክፍለዘመን እንግሊዝ ከ12 ዓመት በታች ያሉ ልጃገረዶችን ለጋብቻ መፍቀዷ በግልፅ ተናግሯል…ለምሳሌ የቨርጂኒያዋ ሜሪ ሃታዌይ ከዊልያም ጋር በትዳር ውስጥ በነበረችበት ጊዜ ገና 9 ዓመቷ ነበር። ፖርቹጋል፣ ስፔን፣ ዴንማርክ እና የስዊስ በመጀመሪያ የጋብቻ ፍቃድ እድሜን ከ10-12 ዓመታት ካስቀመጡ በኋላ በ19ኛው ክፍለዘመን አጋማሽ ላይ ወደ 13 እና 16 ዓመታት አሳድገውታል። በታሪክ የእንግሊዝ የጋራ የጋብቻ ህገ-ፈቃድ እድሜ ከ10-12 ድረስ ወስነዋል። በዩናይትድ ስቴትስ በ1880ዎቹ ውስጥ አብዛኞቹ ግዛቶች የጋብቻ ስምምነት እድሜን ከ10-12 ድረስ አድርገዋል፣ ዴላዌር በምትባል ግዛት ጋብቻ በ7 ዓመት እድሜ ተፈቅዶ ነበር።❞
(What’s Wrong in America: A Look at Troublesome Issues in Our Country By Arthur Siccan)
ሜሪል ዲ.ስሚዝ ባዘጋጀችው ዓውደ-ጥበብ ላይ እንዲህ በማለት ትናገራለች ❝በታሪክ ውስጥ በዘመንና ባህል ላይ በመመርኮዝ የጋብቻ እድሜ በ10 ዓመትና 13 ዓመት ውስጥ ይፈጸም ነበር…ያኔ ሴት ልጅ ያለ አባቷ ፍቃድ ማግባት የማትችልበት ዘመን ነበር።❞
(Encyclopedia of Rape by Merril D. Smith page 40)
ከእነዚህ የታሪክ መጽሐፍት የምንረዳው በታሪክ ውስጥ ልጃገረዶችን በለጋ እድሜያቸው ለጋብቻ መስጠት የተለመደ እና ታላላቅ ሀገራት እንኳ የልጅነት ጋብቻን መፍቀዳቸውን ነው። እስኪ አሁን ደግሞ ከአይሁዳውያን ጹሑፎች እንመልከት። በባቢሎናዊው ታልሙድ መሰረት አንዲት ልጅ 3 ዓመት ከ1 ቀን ሲሆናት ለጾታዊ ግኑኝነት ትሰጣለች።
Mishnah: A girl of the age of three years and one day may be betrothed by intercourse…Gemara: Our Rabbis taught: A girl of the age of three years may be betrothed by intercourse; so R. Meir. But the Sages say: Only one who is three years and one day old.
‟ሚሽና፡ የሦስት ዓመት ከአንድ ቀን ሴት ልጅ ለግብረ ሥጋ ግንኙነት ልትታጭ ትችላለች…ገማራ በእርግጥ ሊቃውንቶቻችን አስተምረዋል የሦስት ዓመት ሴት ልጅ በግብረ ስጋ ግንኙነት ልትታጭ ትችላለች። ጠቢባኑ ይላሉ፡ የሦስት ዓመት እና የአንድ ቀን ልጅ ብቻ ናት።
(Babylonian Talmud: Tractate Niddah 44b)
Rabbi Joseph said: Come and hear! A maiden aged three years and a day may be acquired in marriage by coition, and if her deceased husband’s brother cohabits with her, she becomes his.”
‟ረቢ ዮሴፍ እንዳለው ኑ እና ስሙ ! የሦስት ዓመት እና የአንድ ቀን ልጃገረድ በትዳር ውስጥ ልትገባ ትችላለች እናም ባሏ ከሞተ ወንድሙ ከእሷ ጋር አብሮ የሚኖር ከሆነ የእርሱ ትሆናለች።
(Babylonian Talmud, Tractate Sanhedrin 55b)
እንግዲህ ይህ ነው ! የሚገርመው ይህ ደንብ እንደ ሂንዱይዝም ባሉ በዳርሚክ ሃይማኖቶች ውስጥም አለ። እስኪ እንከታተል:- ከዚህ በታች የምታነቡት ጥቅሶች ከአርያ ቅዱሳን ህግጋት የተወሰዱ ናቸው፣ ምዕራፉንና ቁጥሩን ከታች ስለሚቀመጥ ገብታችሁ አንብቡ።
«ሴት ልጅ የጉልምስና እድሜ ላይ ከመድረሷ በፊት ለትዳር መሰጠት አለባት፣ ቸል የሚል ኃጢአትን ይሠራል።
(Sacred Laws of Arya:Gautama 18:21)
«እድሜው ሀያ ዓመት የሆነው ሰው የሰባት ዓመት ልጃገረድ ማግባት አለበት።»
(Mahabharata XLIV (p.18)
«ራማ እንዳለው እርሱ ሲታን ሲያገባ እርሷ ገና ስድስት ዓመቷ ነበረች።»
(Valmiki Ramayana, Aranya Kanda 3.47.3-5)
«ክሪሽና ገና የስምንት ዓመት ልጅ ሳለች ሩክሚኒን እንዳገባት ተናግሯል። ምንም እንኳን የሂንዱ ጽሑፍ ከሩክሚኒ ጋር በተጋባበት ወቅት የክርሽናን ዕድሜ ባይጠቅስም የሂንዱ ጽሑፍ እሱን የሚገልፅበት መንገድ ትልቅ ሰው እንደነበር ነው።»
(Skanda Purana V.iii.142.8-79)
እስኪ አሁን ደግሞ ወደ ክርስትናው ዓለም ገብተን በክርስቲያን ግዛቶች ውስጥ ልጃገረዶች በስንት ዓመታቸው ለጋብቻ ሲታጩ እንደነበር እንመልከት። ጄራልድ ሴጋል ሴቶች በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዘመን (Biblical time) በምን አይነት የእድሜ ክልል ውስጥ ሲታጩ እንደነበር እንዲህ በማለት ይናገራል ❝በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ወቅት ሴቶች የሚያቡት ገና በለጋ እድሜያቸው እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል።❞
(Gerald Sigal, The Jew and the Christian Missionary, Ktav Publishing House,1981, page 28)
በመካከለኛው ክፍለዘመን የቢዛንታይን ንጉሠ-ነግስት የነበረው ዳግማዊው አሌክሲዮስ ሚስቱ ከፈረንሳይ ወደ ቆንጣንጥኖፕል ስትመጣ 8 ዓመቷ እንደሆነችና በለጋ እድሜዋ እንዳገባት የጢሮሱ ሊቀጳጰስ ዊልያም ይናገራል።
(William of Tyre, History of the Deeds Done Beyond the Sea,13.4)
ሌላው ይቅርና የክርስቲያኖች አምላክ እናት የሆነችው ማሪያም ለዮሴፍ ስትታጭ እርሷ 12 ዓመቷ እርሱ ደግሞ 90 ዓመቱ እንደነበር ብዙ የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ። ሞርቲመር ቤነት እንዲህ ይላል ❝Joseph married Mary she was 12 years old and he was 90 years old. ዮሴፍ ማርያምን ሲያገባ እርሷ 12 ዓመቷ ነበረች፣ እርሱ ደግሞ የ 90 ዓመት አዛውንት ነበር»
(History of Joseph the Carpenter By De Robigne Mortimer Bennett)
ከተደበቁት ወንጌሎች ውስጥ አንዱ የሆነው የያዕቆብ ራዕይ በምዕራፍ ስምንት ላይ ይህንኑ ሀሳብ ይደግፋል። እንግዲህ ይህ ከ2 ሺ ዓመት በፊት የነበረው ትክክለኛ ተግባር ነው፣ ከ300 ዓመታት በፊት ልጃገረዶች ከ7 ዓመታቸው ጀምረው መታጨት እንደሚችሉ ፍቃድ ተሰጥቶ ነበር¹ ይህ በዘመኑ የተለመደ ተግባር በመሆኑ በዚያን ወቅት ይህን የሚኮንን ሰው አልነበረም። ልጃገረዶች በልጅነት እድሜያቸው መታጨት የለባቸውም የሚለው ንግግር የመጣው በ19ኛው ክፍለዘመን ነው። እ.አ.አ ከ1880 በፊት የጋብቻ እድሜ ስምምነት በተለያዩ ሀገራት አብዛኛው እድሜ 10 መሆኑን አንድ ጥናታዊ ጹሑፍ ፕራይመሪ ምንጮችን በማጣቀስ ያስረዳናል ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ።
(🌐Stephen Robertson, “Age of Consent Laws,” in Children and Youth in History (https://chnm.gmu.edu/cyh/teaching-modules/230?section=primarysources&source=24))
ነቢዩ መሐመድ የዘመናቸውን ሁኔታ ፍፁም በሆነ ሞራላዊ መንገድ ስላስተናገዱ ስህተትና እንግዳ የሆነን ተግባር አልፈጸሙም። ከጥንት ጀምሮ የህብረተሰብ ልማድና ባህል ሁል ጊዜ የማይለዋወጡ የሚመስላቸው አካላት በአንድ ወቅት በህገመንግሥታት እንኳ እንደ ትክክለኛ ተግባር የሚቆጠሩ ልማዶች ከጊዜ ቡኋለ እንደ መጥፎ ድርጊት ስለሚጠቀሱ የዘመኑን ሁኔታ ከግምት ሳያስገቡ ነቢዩን መተቸት ይፈልጋሉ። ልጃገረዶችን በለጋ እድሜያቸው ማግባት እንደ መጥፎ ልማድ ተደርጎ መነሳት የጀመረው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፣ ይህ ትችት ከ300 ዓመታት በፊት የነበረውን ሁኔታ የማካለ አይደለም። በጥንት ሂንዲዩዝም ልጃገረዶችን በ7/8 ዓመታቸው ለጋብቻ ይሰጡ ነበር። አይሁዳውያንም በታልሙዳቸው የ3 ዓመት ከ1 ቀን የሆነች ልጅ ለኒካህ መሰጠት እንዳለባት ያስተምራሉ። በጥንት ክርስትናም ሴት ልጅ በለጋ እድሜዋ ለጋብቻ ትሰጣለች፣ የጋብቻ እድሜ ከዘመን ወደዘመን የሚሻሻል በመሆኑ በዚህ ዙርያ ትችት ማንሳት ከተማረ ሰው የሚጠበቅ ሙግት አይደለም። በክፍል 1 እንዳየነው ሴት ልጆች ለአቅመ-ሔዋን (ጉልምስና) የሚደርሱበት እድሜ ከ8 ዓመታቸው ቡኋለ እንደሆነ ዘመናዊውን ሳይንስ እያጣቀስን ለማየት ሞክረናል። የዘጠኝ ዓመቷ አዒሻህ በአካልም ሆነ አዕምሮ የበሰለች እንስት መሆኗን ከተዓማኒ እስላማዊ ምንጮች ለማየት ችለናል። ሚስዮናውያን ሴት ልጅን በቁሟ ግደላት ብሎ የሚያዝ ሀይማኖት ውስጥ ተቀምጠው ለሴት ልጅ የተጨነቁ ይመስል ይህን ገለባ ክስ እንደ ሙግት ማንሳታቸው እንደተለመደው ምን ያክል አላዋቂዎች መሆናቸውን ያሳየናል። አላህ ሒዳያ ይስጣችሁ ለእኛም የማሪያም ቢንት ዒምራን ሀይማኖት ላይ ጽናቱን ይስጠን።
1] Adolescent Sexuality: A Historical Handbook and Guide by Carolyn Cocca p. 15
በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦
የአባልነት ፎርሙን ለመሙላት ይህንን ይጫኑ
ማዕከላችንን የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጥታ ለመደገፍ፦
አካውንት – 1000499318212
የአካውንት ስም – Hidaya Islamic Center
በአጭር ቁጥር – 8212 መጠቀም ይችላሉ።


