ዛሬ የምናስተናግደው ጥያቄ ደግሞ ይህ ነው፡፡ እሱም፡- የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ሳይሞትና ሳይገደል አላህ ወደራሱ ካነሳው (ከወሰደው)፣ እስካሁንም በሕይወት ካለ፡ በርግጥም እሱ ምድራዊ ቆይታቸውን ፈጽመው፡ ወደ መቃብር ዓለም ገብተው ስጋቸውና አጥንታቸው በስብሶ ከቀረው ነቢያት ይበልጣል ማለት ነው! የሚለውን ነው፡፡ ይህ አመለካከት ግን ፍጹም ስህተት መኾኑን ቀጥሎ ባሉት ምክንያቶች ይብራራል፡-
Category: ቁርዓን
ቁርኣንም ሥላሴን አያውቅም?
“የራሷ አርሮባት የሰው ታማስላለች” እንዲሉ ሆነና ነገሩ፡ ቅዱስ ቁርኣን የአላህን ፍፁማዊ አንድነት (በህላዌው፣ በስራው፣ በባሕሪያቱና በአምልኮ) በሰፊው በማስተማር ከአንድ አላህ ውጪ እንደ አምላክ የተያዙና የሚመለኩ አካላትን (በተለይ ሥላሴን) ሲቃወም፡ ይህ ያልተዋጠላቸው የአክፍሮት ኃይላት ቅዱስ ቁርኣንን እንዲህ በለው ይተቻሉ፡- ቁርኣን ሥላሴዎች ብሎ የሚጠቅሳቸው ‹እግዚአብሄርን፣ ኢየሱስን እና ማርያምን› ነው፡፡ ይህ ደግሞ ስህተት ነው፡፡ እኛ ሥላሴዎች ብለን የምንጠራቸው ‹አብ (እግዚአብሄርን)፣ ወልድ (ኢየሱስን)፣ መንፈስ ቅዱስ (አጽናኙን)› ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ቦታ ማሪያም መግባቷ ስህተት ነው ይላሉ፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ የሚጠቅሱት ቀጣዩን የቅዱስ ቁርኣን አንቀጽ ነው፡-
አሏህ ﷻ ለምን “እኛ” ይላል?
በዚህ ምድር ላይ የፈጣሪ አምላካችንን የአላህን ፍጹማዊ አንድነት የሚሰብክ ብቸኛ ሃይማኖት ቢኖር፡ ኢስላም ብቻ ነው ማለት ማጋነን አይሆንም፡፡ የሙስሊሞች እምነትም ብዙ ጊዜ ጎልቶ የሚታየው ‹‹አላህ አንድ ነው!›› በሚል መሪ ቃል ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ተመራማሪዎች በዙና፡ ቅዱስ ቁርኣንን ሲመረምሩ፡ በውስጡም እንደ ሥላሴ አምላኪዎች የአላህን ሶስትነት የሚመሠክር ጥቅሶች በብዛት እንዳገኙበት ገለጹ!፡፡ ምንድነው የተገኘው ስንላቸው፡- አላህ እራሱን ‹‹እኛ›› ብሎ ነው የሚገልጸው፡፡ እሱ ‹‹አንድ›› ብቻ ከሆነ ለምን ‹‹እኛ›› በማለት በብዙ ቁጥር ይጠቀማል? አሉን፡፡
ጅሀድ በትክክል ምንድን ነው?
“ጂሃድ” የሚለዉ ቃል ሲወሳ ብዙ ሰዎች በተለይም ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች አስፈሪ ምስል ይደቀንባቸዋል። ከተለያዩ የሚዲያ ምንጮች የሚያገኟቸው የተለያዩ መረጃዎች በዚህ አረዳዳቸው ላይ የራሳቸው ተፅእኖ አላቸው። እነዚህ ሰዎች ስለ ጂሃድ ሲያስቡ ምናልባትም ፊልም ላይ እንደሚያዩት ጺሙ የተንዥረገገ፣ፊቱ የተኮሳተረ፣ በቀኝ እጁ ቁርአን በግራ እጁ ሰይፍ የያዘ ሰዉ በአይነ ህሊናቸዉ ሊመጣባቸዉ ይችላል፡፡ ይህም ሰዉ ከፊት ለፊቱ ያገኘዉን ሁሉ “ትሰልማለህ ወይስ አትሰልምም” በማለት ይጠይቃል “ሰልሜያለዉ” ያለዉን ይተዋል “አልሰልምም” ያለዉን ግን “አሏሁ አክበር” በማለት አንገቱን በሰይፍ ይቀላል ወይም ደግሞ ቦንብ አንግቦ ሰላማዊ ህዝብ የተሰበሰበባቸዉን ቦታዎች በማጋየት ንፀሃንን ሲጨርስ ይታያቸዋል፡፡
“የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ…”
ዛሬ ዛሬ ክርስቲያን ወገኖች እነዚህን ጥቅሶች በመያዝ “እነሆ ቁርዓን በወንጌል ፍረዱ ማለቱ ወንጌል አለመበረዙን ያስረግጣል፤ ከተበረዘ ለምንድነው በርሱ ፍርዱ የተባለው፤ በወንጌል ፍረዱ ሲል ወንጌል ትክክለኛና እስከአሁንም ድረስ ሊ’ሰራበት የሚገባ የፈጣሪ ቃል መሆኑን ያስረግጣል…” የሚሉ ወዘተረፈ ሙግቶችን አመክንዮአዊ ሆነው ሲሰነዝሩ ይታያል፡፡ አንዳንዶቹ እንድያውም አበክረው “ ወንጌል ተበርዟል የምትሉን ከሆነ፣ እንግድያውስ ቁርዓን በተሳሳተ መጽሃፍ ነው ፍረዱ የሚለን፤ ስለሆነም ቁርዓን መለኮታዊ አይደለም፡፡ ቁርዓን መለኮታዊ ከሆነ ደግሞ እንድንፈርድበት የተጠቆምነው ወንጌልም ትክክልና መለኮታዊም ነው” በማለት ሙግታቸውን ያጸናሉ፡፡
ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ..?!
ይህ ጥቅስ መኪያ ከሚባሉ ከስደት በፊት ከተወረዱት ጥቅሶች መካከል ይመደባል፡፡ አላህ ተግዳሮቱን አስቀድሞም ከስደት በፊት (ቀብለል ሂጅራ) በነዚህ ጥቅሶች አስቀምጧል- ቀሰስ/49፣ኢስራእ/88፣ ሁድ/13፤ዩኑስ/37፡፡ በአልበቀራህ ያለውን ለየት የሚያደርገው አንዲትን ምዕራፍ እንዲያመጡ መገዳደሩና…ማምጣትም እንደማይችሉ ማወጁ ነው፡፡ በጃሂሊያ የነበሩ አንደበተ-ርቱዕ ገጣሚዎች በቋንቋው ድካ ከመድረሳቸው አኳያ በቁም በርካታ ስንኞችን ማንፎልፎል የሚችሉና በቋንቋ ችሎታቸውም ዘመን ተሻጋሪ መቼም የማይደረስበት የመጨረሻ ስልጣኔ ላይ የደረሱ ነበሩ፡፡ ግን ታዲያ የቁርኣን ብጤ አንድንም ምዕራፍ ማምጣት ለምን አልተቻላቸውም?







