“ክርስቶስ ሞትን ድል ነስቷል” የሚለውን ቃል እየደጋገመ እንደሚፎክር ሰባኪ የሚያሳዝነኝ ሰው የለም። ግለሰቡ የዚህ እምነቱ “ድንቅነት” ያስገረመበት ምክንያት ኢየሱስን አስመልክቶ ያለው ምልከታ በጥርጣሬ ወጀብ የተመታ ስለሆነ ነው። ከመነሻው ፈጣሪ ሞት የሚባለውንና እራሱ የፈጠረውን ነገር ማሸነፉ ምኑ ነው እንደ ትልቅ ጀብድ የእድሜ ልክ የሰበካ ርዕስ የሚሆነው? ምናልባት በሰባኪው ልቦና ውስጥ የኢየሱስ ቦታ የተደናገረ ደረጃ ካለው (ፍጡር ወይንስ ፈጣሪ የሚለው) ክስተቱን ቢያገዝፈው አይደንቅም። አንድ ፍጡር ሞትን ድል አድርጎ ቢነሳ የምርም ይገርማል፤ በዚህ መሀል በጥርጣሬ ለሚዋልል ሰው የኢየሱስን ከሞት መነሳትን ማመን እንደ ትልቅ ነገር ቢመለከተው አይገርምም። በዚህ ሰው እምነት ውስጥ ግን ኢየሱስ በትክክልም ከቃል በዘለለ ልቦናው ላይ አምላክነቱ ታምኖ እንዳልተቀመጠለት በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።
Author: Admin
እግዚአብሔርና ኢየሱስ
(የሕያ ኢብኑ ኑህ) መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ከሆነ ፈጣሪ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት እንዲሰግዱለት ያስፈልጋል። “እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።” ዮሐንስ 4፥24 በሌላ አነጋገር አምላክ ማንነቱ “መንፈስ” እንደሆነ በቀጥታ እየተነገረን ነው። ከዚህ ገለፃ ተነስተን ኢየሱስ ታዲያ እግዚአብሔር ነውን? ብለን ከጠየቅን መልሱ አይደለም የሚል ይሆናል። የዚህን መልስ እራሱ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ይሰጠናል፦…
የወንጌሉ ኢየሱስና ስህተቶቹ
የወንጌሉ ኢየሱስ የገበሬ ስራዎችን አስመልክቶ አስተያየት ሲሰጥም ሆነ ተግባራትን ሲያከናውን በተደጋጋሚ ስህተት ውስጥ ይወድቃል። የበለስ ወር መሆኑን ባለማወቁ ምክንያት ወደ በለሷ ሒዶ እንዳሰበው ሳይሆን በለስ ባለማግኘቱ ምክንያት ያችን ሚስኪን በለስ ረግሟታል።
የእግዚአብሔር አምሳያ ማነው?
እንደመጽሀፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሠረት የሰው ልጅ የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ነው። እኛ ሰዎች የእግዚአብሔር አምሳያ ነን ከተባለ ታዲያ የትኛው ፆታ ነው ይህንን መመሳሰሎሽ የገጠመው የሚለው ተያይዞ የሚነሳ ጥያቄ ነው። እንደሚታወቀው ሰው የሚባለውና መጽሀፍ ቅዱስም አያይዞ የጠቀሰው ፆታ ወንድና ሴት ነውና እግዚአብሔር ሰው ሲል የትኛው እሱን እንደሚመስል እንድንጠይቅ ያስገድደናል። አንቀጹ እንደሚከተለው ይነበባል፦
እግዚአብሔርና እውቀቱ
እግዚአብሔር ግብፃውያንን ሊያጠፋ አሰበ። እንግዲህ እግዚአብሔር ሲያጠፋ ሴት ወንድ አይልም፤ አዋቂ እንስሳም አይመርጥም፤ ሲገል ሁሉንም ነው የሚገለው። በዛ ወቅትም እንደተለመደው እግዚአብሔር ግብፃውያንን ሊገድልና አማልክታቸውንም ሊያጠፋ ወሰነ።
◾️የተረሳው መንፈስ ቅዱስ
እንደ ክርስቲያኖች እምነት መሠረት ከሥላሴ አካላት ውስጥ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ እንደ አብና ወልድ እኩል መለኮታዊ ስልጣን ያለው አምላክ ነው ብለው ያምናሉ። እንዳለመታደል ሀኖ ግን መንፈስ ቅዱስ የሚገባውን ያክል ቦታ አልተሰጠውም። አንዳንዴም እንዴውም ሌሎች አካላት ሁሉ ተጠቅሰው እሱ ሲረሳ እንታዘባለን። እንዴው መንፈስ ቅዱስ አምላክ የተባለው ሁሉ “አምላክ ሁለት ነው” እንዳይባል ተብሎ ብቻ የኃለኛው ጉባኤ የጨመረው ይመስላል። ይህንን ጥርጣሬ እስኪያረጋግጥልን ድረስ መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ልብም ሆነ በመጽሀፍ ቅዱስ ከአብና ወልድ ጋር እንኳን እኩል የማይታወስ ባይተዋር ተደርጓል። ማቴዎስ በወንጌሉ እንዲህ ማለቱ ተፅፏል፦
አላህ ﷻ አደምን ያስቀመጠበት ጀነት
አላህ (ሱ.ወ) አደምን አስቀምጦበት የነበረውንና ከእሷም እንዲወጣ ያደረገባቸውን ጀነት በተመለከተ ዑለሞች (ሙስሊም ምሁራን) የተለያየ አቋም አላቸው፡፡ በሰማያት ኣለም ነች ወይንስ በዚህች ምድር ላይ?
ግብጽና ሚሽነሪው – ጨረፍታ
በግብፅ ከ1925-1935 ባሉ ጊዜያት ውስጥ የነበረትን የሚሽነሪ እንቅስቃሴዎች መሠረት በማድረግ በዑመር ሪያድ የተሰራው ጥናታዊ ወረቀት እንደሚገልፀው በግብፅ ምድር ብቻ በ1930 ዓ.ል 450 የሚሆኑ የውጭ ሀገር ዜጋ ሚሽነሪዎች የነበሩ ሲሆን 1500 የሚሆኑ ደግሞ ግብፃዊ ሰራተኞች ነበሩ። አመታዊ በጀታቸውም $700,000 ዶላር ነበር። ከምንም በላይ የሚያስደንቀው ግን ለአላማቸው የነበራቸው ድፍረት ነበር። አዝሀር ኢስላማዊ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ሳይቀር ገብተው ለተማሪዎች ፓምፍሌትና ብሮሹር እስከመበተን የደረሱ ነበሩ።
ጋብቻና ክርስትና
እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን ሲናገር “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉዋት” ይላል። ይህ ትዕዛዝ የሰው ልጅን ከማብዛት አላማ ጋር የተሳሰረ ነው። በቃሉ ውስጥ የጋብቻን አስፈላጊነት እናስተውላለን። ሰው ምድርን የሚሞላት በአምላክ ቡራኬ ውስጥ ባለ ስርአት ውስጥ ነውና ጋብቻ መልካም ነገር ነው። ጻውሎስ በመልዕክቱ ደግሞ እንዲህ ይላል፦
የተፈጠርነው ለፈተና ነው!!
አንዳንድ አላዋቂዎች ከእምነታቸው ጉድለት: ከግንዛቤያቸውም እጥረት “ሰው የተፈጠረው ለፈተና ነው!” የሚለውን የሙስሊሞችን እምነት ይቃወማሉ። እንዲህ ሲሉም ተቃውሞ ያቀርባሉ፡- አላህ ሰውን የፈጠረው ለፈተና ከሆነ፡ እሱ መልካም አምላክ ሳይሆን ክፉ ነው ማለት ነው! ደግሞስ መፈተኑ ቀድሞ አያውቅም ነበር ማለት ነውን? የሚል ነው፡፡











