በብዛት የሚደጋገም ጥያቄ ነው፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከሌሎች ቀደምት ነቢያቶች ለመለየትና እሱን ከፍ ለማድረግ ከሚጠቀሙበት አስረጂዎች አንዱ ይህ ነው፡፡ እሱም፡- እንደ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ከድንግል ብቻ የተወለደ ሌላ ነቢይ ማነው? ይህ ብቻ ከሁሉ ነቢያት የተለየ አያደርገውምን? የሚል ጥያቄ!፡፡ የኛ ምላሽም በአላህ ፈቃድ እንደሚከተለው ይቀርባል ኢንሻአላህ፡፡
Category: ምላሾች
ማነው ወፍን የፈጠረው?
ሀሰት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንዲሉ ሆነና፡ ከሰብአዊ ፍጡርነትና ከነቢይነት ውጪ ምንም ድርሻ የሌለውን የመርየምን ልጅ ዒሳን (የአላህ ሰላም በሁለቱም ላይ ይሁን) አምላክና ፈጣሪ ለማድረግ የቅጥፈት ዘመቻዎች በየአቅጣጫው እየተደጋገሙ ነው፡፡ ከነዛም ውስጥ አንዱ፡- ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ወፍን ፈጥሯል የሚለው ተረት ተረት ነው፡፡ እንኳን ወፍን ሊፈጥር ይቅርና ፍጥረተ ዓለሙ እራሱ ቢተባበረውና ቢያግዘው: ዝንብን እንኳ መፍጠር አይችልም!!፡፡ ይህ የጌታችን ቃል ነው፡፡ እንዲህ ይላል፡-
ጨረቃ በኢስላም | ክፍል -2
በክፍል አንድ ትምሕርታችን ላይ ጨረቃ በኢስላም ያለውን ምልከታ በመጠኑ ቃኝተናል፡፡ በውስጡም ጨረቃ የአላህ ፍጥረት መሆኑን፣ በፈቃዱ ስር የተገራ እንደሆነና አምልኮም እንደማይገባው፡ እንዲሁም ለሰዎች የጊዜ ማወቂያ ምልክት እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ በመስጂድም ላይ የሙስሊሞችን የአምልኮ ስፍራ ከጣኦታውያን የአምልኮ ስፍራ ለመለየት ምልክት መደረጉን እንጂ፡ ከአምልኮ ጋር ምንም ትስስር እንደሌለው ተመልክተናል፡፡ አልሐምዱ ሊላህ፡፡
ጨረቃ በኢስላም | ክፍል -1
ይህንን ለመጻፍ ያነሳሳኝ ከካፊሮች በኩል የተነሳን ጥያቄ አንብቤ ነው፡፡ ሙስሊሞች የምታመልኩት የጨረቃ አምላክን ነው፡፡ በመስጂዳችሁም የሰቀላችሁት ለዚህ ነው፡፡ የጨረቃ አምላክ የሚባለው ደግሞ ከፀሀይ አምላክ ጋር በመጋባት ሴት ከዋክብቶችን ወልዷል የሚል እንቶ ፈንቶ በማየቴ ነው፡፡
እኔ እና እሱ “በቀደር ዙርያ የተደረገ ውይይት”
በኡስታዝ አቡ ሀይደር በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው እሱ፡- ቁርኣን የማን ቃል ነው? እኔ፡- ቁርኣን የአላህ ቃል ነው፡፡ እሱ፡- ምን ማስረጃ ይኖርሀል? እኔ፡- ቁርኣን ራሱ የአላህ ቃል መሆኑን ይናገራል!፡፡ እሱ፡- የቱ ጋር? እኔ በሱረቱ ተውባህ ምእ 9 ቁ 6 ላይ ‹‹ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው…
ወሕይ (መለኮታዊ ግልጸት)
ፈጣሪ አምላካችን አላህ ሰውንና ጂንኒን እሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩት ፈጥሯቸዋል (አዝ-ዛሪያት 56)፡፡ ትክክለኛ አምልኮ ምን እንደሆነ ያብራሩላቸው ዘንድ ከሰዎች መካከል የተወሰኑትን በፈቃዱ መርጦ፡ የመረጣቸውንም ነቢያትና መልክተኛ አድርጎ ወደ ህዝቦቻቸው ልኮአቸዋል፡፡ በነዚህ መልክተኞች በኩል ቃሉንም አውርዷል፡፡ ይህ ወደ ነቢያት የወረደው መለኮታዊ ቃል በጥቅሉ በዐረብኛው ‹ወሕይ› ይሰኛል፡፡
ጅሀድ በትክክል ምንድን ነው?
“ጂሃድ” የሚለዉ ቃል ሲወሳ ብዙ ሰዎች በተለይም ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች አስፈሪ ምስል ይደቀንባቸዋል። ከተለያዩ የሚዲያ ምንጮች የሚያገኟቸው የተለያዩ መረጃዎች በዚህ አረዳዳቸው ላይ የራሳቸው ተፅእኖ አላቸው። እነዚህ ሰዎች ስለ ጂሃድ ሲያስቡ ምናልባትም ፊልም ላይ እንደሚያዩት ጺሙ የተንዥረገገ፣ፊቱ የተኮሳተረ፣ በቀኝ እጁ ቁርአን በግራ እጁ ሰይፍ የያዘ ሰዉ በአይነ ህሊናቸዉ ሊመጣባቸዉ ይችላል፡፡ ይህም ሰዉ ከፊት ለፊቱ ያገኘዉን ሁሉ “ትሰልማለህ ወይስ አትሰልምም” በማለት ይጠይቃል “ሰልሜያለዉ” ያለዉን ይተዋል “አልሰልምም” ያለዉን ግን “አሏሁ አክበር” በማለት አንገቱን በሰይፍ ይቀላል ወይም ደግሞ ቦንብ አንግቦ ሰላማዊ ህዝብ የተሰበሰበባቸዉን ቦታዎች በማጋየት ንፀሃንን ሲጨርስ ይታያቸዋል፡፡








