በስተመጨረሻም በጥራት የተሰራው ኦፍላይን አፕልኬሽን ተጠናቆ ይኸው ወደናንተ ደርሷል። አፕልኬሽኑ ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎችም ለአይፎን ተጠቃሚዎችም የተሰራ ነው። በንጽጽር ዙሪያ የተጻፉ ጹሁፎችን በዚህ ድረ ገጽ በፈለጉት ሰአት ያለ ኢንተርኔት ገብተው ማንበብ ይችላሉ። አዳዲስ ጹሁፎችም በአሏህ ﷻ ፍቃድ በተከታታይ ይጨመሩበታል። አፑን ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ፣ ለሰውም ሼር ያድርጉት፦
![]()
በስተመጨረሻም በጥራት የተሰራው ኦፍላይን አፕልኬሽን ተጠናቆ ይኸው ወደናንተ ደርሷል። አፕልኬሽኑ ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎችም ለአይፎን ተጠቃሚዎችም የተሰራ ነው። በንጽጽር ዙሪያ የተጻፉ ጹሁፎችን በዚህ ድረ ገጽ በፈለጉት ሰአት ያለ ኢንተርኔት ገብተው ማንበብ ይችላሉ። አዳዲስ ጹሁፎችም በአሏህ ﷻ ፍቃድ በተከታታይ ይጨመሩበታል። አፑን ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ፣ ለሰውም ሼር ያድርጉት፦
![]()
እንኳን ደህና መጡ! በዚህ ድረ-ገጽ ውስጥ የሚያገኟቸው አበይት አርቲክሎች በዚህ ሊንክ ውስጥ ተዘርዝረው ያገኟቸዋል። መልካም ንባብ ጊዜ!
![]()
በአንድ ወቅት ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዚል-መጃዝ በተሰኘው የገበያ ማዕከል እለፉ፡- ‹እናንተ ሰዎች ሆይ! ላ ኢላሀ ኢለሏህ በሉ! ትድናላችሁና በማለት ተናገሩ፡፡ የከሀዲያን ቁንጮ የነበረው አቡ ጀህልም በሳቸው ላይ አፈርን እየበተነባቸው፡- እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህ ሰው ከሃይማኖታችሁ እንዳያስታችሁ፡፡ እሱ የሚፈልገው አማልክቶቻችሁን እንድትተዉ ነው፡፡ ላትናና ዑዝዛን ከማምለክ እንድትቆጠቡ ነውና የሚፈልገው አትስሙት አላቸው፡፡ የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደሱ ፊታቸውን ሳያዞሩ ዳዕዋቸውን ቀጠሉ፡፡ (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ 16119)፡፡
በነዚህ ሁለት ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾች መሠረት ‹‹ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ!›› የሚል ቃል አልለ፡፡ ይህ ጠላትነት በማን እና በማን መሐል ያልለ ነው? የሚል ጥያቄ ከአንድ ወንድሜ በኩል ስለቀረበልኝ፡ መጠነኛ ማብራሪያ ለመስጠት ነው ኢንሻአላህ፡፡
ዛሬ የምንመለከተው ደግሞ፡- ይህ የአላህ ቃል የኾነው ቁርኣን እንዴት ተሰብስቦ አንድ መጽሐፍ እንደኾነ፡ እሱም በማን ጊዜ እንደተሰበሰበ እና ለዚህም ምክንያቱ ምን እንደነበር እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡፡ መልካም ንባብ፡-
ቅዱስ ቁርኣን የአላህ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ሆነ መልእክቱ የአላህ ብቻ ነው፡፡ በቁርኣን ውስጥ የመላእክት፣ የነቢያት፣ የጸሐፊዎች፣ የአጋንንት ቃልና ሀሳብ አልሰፈረም አይሰፍርምም፡፡ በቁርኣን ውስጥ ተናጋሪው ጌታ አላህ ብቻ ነው፡፡ ስለ ነቢያት የሚተርክልን፣ ስለ መላእክት የሚያወሳልን፣ ይህን አድርጉ ያንን ደግሞ አትቅረቡ! በማለት የሚያናግረን እሱ ጌታ አላህ ብቻ ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ቁርኣንን ከፍቶ አነበበ ማለት፡ ጌታ አላህን አናገረው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በውስጡ የሰፈረው ቃል በጠቅላላ ተናጋሪው አላህ በመኾኑ ማለት ነው፡፡
በዚህ አንቀጽ ውስጥ ቅጣት የሚለው ቃል በቅንፍ ታጥሯል፡፡ በቅንፍ መታጠሩን የተመለከቱ አንዳንድ ወገኖች፡ ይህ በዐረብኛው ቁርኣን ላይ የሌለ፡ በአማርኛው ቁርኣን ላይ የገባ አዲስ ተጨማሪ ሀሳብ ነው የሚል አስቂኝ እና አሳዛኝ ተቃውሞ ያሰማሉ፡፡ የቅንፉን አስፈላጊነት፡ የቃሉንም መልእክት በተወሰነ መልኩ ማብራራት ግን የኛ ግዴታ ነው፡፡
የዚህን አንቀጽ መልእክት በአግባቡ ለመረዳት ወገኖቻችን አልታደሉም፡፡ በተሳሳተ መንገድ ተረድተው መልክቱን ለነሱ ሊያደርጓትም ቋመጡ፡፡ በድፍረትም እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፡- በዚህ አንቀጽ መሠረት ቅዱስ ቁርኣን ለሙስሊሞች፡ በእምነታቸው ጥርጥር ከገባባቸው መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢዎች ዘንድ ሄደው በመጠየቅ እውነቱን መረዳት እንደሚችሉ መጠቆሙን እንረዳለን!!፡፡
በየትኛው ስነ-አመክንዮ ነው ይህ ሀሳብ እውነት መሆን የሚችለው? እውነት ኃጢአትን ከኃጢአተኛው ለይቶ መግለጽ ይቻላልን? ኃጢአተኛው ጻድቅ ቢሆን ኖሮ ኃጢአት ትርጉም እና ምንነት ይኖረው ነበርን? አምላክስ ኃጢአተኛውን ከወደደው፡ ጀሀነም እሳትን ያዘጋጀው ለጻድቃን ነው ማለት ነውን? ወይስ ኃጢአት እራሱ አካል ለብሶ ወደ ጀሀነም እሳት ይወረወራል? መቼም አምላክ የሚወደውን ኃጢአተኛ ባሪያውን በጀሀነም እሳት ያሰቃየዋል የሚል አስተምህሮ አይኖርም፡፡ ካለም ስህተት እንጂ እውነት መሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ጀሀነም እሳት የአምላክ ቁጣ መገለጫ የሆነ የቅጣት ስፍራ እንጂ፡ የፍቅሩ መገለጫ የሆነ የወዳጆቹ የክብር ስፍራ አይደለም፡፡ ታዲያ ገሀነም የተዘጋጀው ለኃጢአተኞች ከሆነ፡ አምላክ ኃጢአተኛን ቢወደው ነው ቢጠላው ጀሀነምን የደገሰለት? አእምሮ የተሰጠን ምን ልናደርግበት ነው? ገና ህፃን ሳለ ጭንቅላት የተፈጠረው ለምንድነው? ብዬ ስጠይቀው፡ ኮፍያ ለማስቀመጥ በማለት የመለሰልኝ ልጄ ሐይደር ለካ እውነቱን ነበር!!