በዚህ አንቀጽ ላይ ከካፊሮች በኩል የቀረበ አንድ ጥያቄ አልለ፡፡ እሱም፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለጹ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ›› የሚለውን ቆንጥሮ በማውጣት፡- ኢስላም ከተከታዮቹ ጥያቄን ማስተናገድ አይፈልግም፡፡ አማኞቹ ያለ-ምንም ጥያቄ ዝም ብለው እንዲከተሉ ስለሚፈልግ ‹‹አትጠይቁ!›› በማለት ከልክሏል! ይሉናል፡፡ የጳውሎስን እከክ በጀማል ላይ ልክክ! ይሏችኋል እንዲህ ነው፡፡ እኛም ለዚህ ጥያቄ መሳይ ተቃውሞ የሚኖረን ምላሽ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ ወማ ተውፊቂ ኢልላ ቢልላህ፡-
Category: ምላሾች
ግብረ-ሰዶም በኢስላም ያለው እይታ
ከነዚህ ቀደምት ነቢያትና ሩሱሎች ውስጥ አንዱ ሉጥ (ዐለይሂ-ሰላም) ነው (አስ-ሷፍፋት 37፡133)፡፡ ሉጥ (ዐለይሂ-ሰላም) የነቢዩላህ ኢብራሂም (ዐለይሂ-ሰላም) የወንድሙ ልጅ ነው፡፡ መልክተኛ ሆኖ የተላከውም፡ ሰዱም (ሰዶም) ተብላ ወደምትጠራው መንደር እና በአካባቢዋ ለሚገኙት ነው፡፡ የዚህ መንደር ነዋሪዎች ሶዶማውያን በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከክህደታቸው በተጨማሪ (ካፊር ከመሆናቸውም ሌላ) ሌላ የሚታወቁበት አስቀያሚ የኃጢአት ተግባር አልለ፡፡ እሱም፡- የተመሳሳይ ፆታ ግብረ-ስጋ ግኑኝነት (HOMOSEXUAL) ነው፡፡
በሃይማኖት ማስገደድ የለም!!
ዛሬ የምንመለከተው፡ ኢስላም፡- ሰዎች እስልምናን ካልተቀበሉ፡ ሸሀደተይንን (የአላህን አምላክነት እና የነቢዩ ሙሐመድን መልክተኝነት) ካልመሰከሩ ግደሏቸው ብሎ ያዛል የሚለውን ከንቱ የባዶ ሜዳ ጩኸት ነው፡፡
መላእክት እንዴት ለአደም ሰገዱ?
ይህ ስግደት ለአባታችን አደም (ዐለይሂ-ሰላም) ታላቅ ክብር ነው፡፡ በመላእክትና በጂንኒዎች (የኢብሊስ ዝርያዎች) ላይም ብልጫን የተጎናጸፈበት ነው፡፡ አንዳንድ ካፊር ወገኖች እዚህ ላይ የተቃውሞ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ እሱም፡- እንዴት አላህ ለአደም እንዲሰገድ ትእዛዝ ያስተላልፋል? ስግደት የሚገባው ለሱ ብቻ አይደለምን? ለሰው እንዲሰገድ ማዘዙ ክብሩን አሳልፎ መስጠት አይሆንምን? ኢብሊስስ እኔ ለፍጡር መስገድ የለብኝም! በማለቱ እንዴት ከጀነት ይባረራል? የሚል፡፡ እኛም ለዚህ ጥያቄ የሚኖረን ምላሽ፡-
የወር አበባ ሙስሊም ሴትን አያረክሳትም!!
በዚህ አንቀፅ ውስጥ “ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ ራቋቸው፡፡ ንጹሕ እስከሚኾኑም ድረስ አትቅረቡዋቸው” የሚለውን ቃል በመምዘዝ: ሴቶችን ራቁ የተባለው እርኩስ ስለሆኑ ነው ይሉናል። የኛ ምላሽም:–
ጥንታዊው ቤተ መቅደስ
መካ በእስልምና ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው እና ቅዱስ ከሆኑ የአምልኮ ስፍራዎች ግንባር ቀደሟ ሀገር (ከተማ) ናት። ጌታ አምላካችን በክብር አልቆ የማለበት ሀገር (ሱራ 90:1) ከመሆኗም ባሻገር የነቢያቶች አባት የሆኑት አብረሃም ጸጥተኛ (የሰላም) ሀገር ትሆን ዘንድ በጸሎታቸው ያሰቧት ቅድስት ስፍራ ናት (ቁርኣን 2፥126)። በዚህች ጸጥተኛ ከተማ (መካ) ውስጥ ነቢዩ አብረሃም ከልጁ ኢስማኤል ጋር ለሰዎች የአምልኮ ቦታ ይሆን ዘንድ የቤተመቅደስን መሰረት ከፍ አድርገው እንዳቆሙ (እንደገነቡ) ቁርኣን እንዲህ በማለት ይናገራል:-
እውን ከአይሁድ ታልሙዶች የተቀዳ ነውን ?
ብሪታንያዊው የታሪክ ጸሐፊና ሚሺነሪው ዊልያም ክሌር በ1905 በጻፈው “The Original Sources Of The Qur’an” በተሰኘው መጽሐፉ ላይ ነቢዩ ሙሐመድ ከቀደሙት መጽሐፍት ማለትም ከአይሁዳውያን ጹሑፍ፣ ከባይብል፣ ከዞርስትያንስ፣ ከሳቢያኖች እና ከጣዖታዊያን ኮርጀዋል በማለት የተለመደውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ከፍተው ከደሰኮሩ ክርስቲያኖች መካከል አንዱ ሲሆን እርሱም እንደ ቀደሙት ተቺዎች ሞተው ከበሰበሱት ውስጥ ነው። ለነቢያችን የመጣው መገለጥ ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ እንደሆነ ቁርዓን ይነግረናል [1] ከሃዲዎች ከነቢያችን ዘመን ጀምረው ቁርዓንን ላለመቀበል ከሚያቀርቧቸው ማስተባበያዎች ውስጥ አንዱ ቁርዓን ከሌላ መጽሐፍ ዘንድ ኮርጇል የሚለውን ጸለምተኛ ክስ ነው:: [2] ወደ ርዕሳችን ስንመለስ ይህ ብሪታንያዊው ተቺ ከላይ በተመለከትነው መጽሐፉ ላይ “ቁርዓን የአዳምን ሁለት ልጆች (ሀቢል እና ቃቢልን) ታሪክና ንግግር ከአይሁዳውያን ጹሑፍ ማብራሪያ ማለትም ከ “ታርጉም ዮናታን” እና ከ “ታርጉም የሩሰሌም” (Pirqey Rabbi Eli’zer” እና “Mishnah Sanhedrin) የተኮረጀ ነው በማለት እንዲህ ብሎ ይጽፋል ‟conversation, or rather argument, between Cain and Abel is mentioned in Jewish legend both in the Targum of Jonathan 14 and in the Targum of Jerusalem” [3]
የዙልቀርነይን ታሪክ ከሲርያኩ ጹሑፍ የተቀዳ ነውን ?
ሚስዮናዊያን ቁርኣን ላይ ከሚከፍቷቸው ክሶች መካከል ‟ቁርኣን ከፊቱ ያለውን ታሪክ ከሌላ ጹሑፍ ገልብጧል (ኮርጇል)” የሚል ነው፣ ይህ ክስ ጥንትም በቁረይሾች ተነስቶ እንደነበር ይታወቃል፣ ዛሬም በምዕራቡ ዓለም ሰባኪዎች እና በአንዳንድ የሃገራችን ወገኖች በተደጋጋሚ ይነሳል። ተኮርጇል ተብሎ የሚቀርበውን ታሪክና የተኮረጀበት ቀዳሚው ምንጭ ይህ ነው ብለው ሲያቀርቡ ሁሌም ግርም ይለኛል። ለማንኛውም ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስንመጣ ገብርኤል ሳይድ ሪይኖልድስ የተባለው ጸሐፊ “The Qur’an in Its Historical Context” በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 175-80 ላይ ቁርኣን የዙልቀርነይንን ታሪክ ከሲሪያኩ ጹሑፍ ‟ኒሻነህ ዲሌህ አሌክሳንድሮስ” ወይም “የአሌክሳንደር ግሩም ስራዎች” በመባል ከሚታወቀው ጹሑፍ ነው የተቀዳው በማለት ይጽፋል።
በዘመነ ጃሒልያ ለሚኩሯራ…
የነቢዩን ሐያዕ እና ውብ ሥነ-ምግባር ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት እና ለማደብዘዝ ሌት-ከቀን የሚሰሩ አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት በርካታ የሕይወት ታሪካቸውንና ንግግራቸውን ከማጥመምም አልፈው ሐዲስ እስከ መፈብረክ እንደ ደረሱ ይታወቃል። ሐሰተኛ ነው የሚሉትን ነቢይ በእውነት ሚዛን ሐሰተኛ ማድረግ ስላልቻሉ መሰረት አልባ ክሶችን ማዘውተር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከእነርሱ መካከል ከታች የሚገኘውን ሐዲስ በማጥመም ነቢያችሁ የብልግና ቃል ተናግረዋል ይላሉ:-
ጎልማሶችን ማጥባት ሲባል እንዴት?
‟ሪዷዓቱል ከቢር”رَضَاعَةُ الْكَبِيرِ ማለት “ጎልማሶችን ማጥባት” ማለት ሲሆን ግኑኝነት ሐራም የሚደረግበት መንገድ ነው። በእስልምና አንድ ወንድ እናቱንም ሆነ ያጠባችውን ሴት ማግባት እንደማይችል ጌታ አምላካችን በቁርኣኑ ተናግሯል (Qur’an 4:23)። መጋባት የሚፈቀድላቸው ሰዎች እንኳ እርሷ ወተቷን ካስጠባችው ያ ሰው በእርሷ ላይ እርም ስለሚሆን እንደ እናት እና ልጅ ይሆናሉ። አንድ ሰሊም የተባለው ሶሃቢይ ሰህላን ለመጎብኘት ወደ አቡ ሑዘይፋ ቤት መግባቱ ለባሏ ምቾት እንዳልሰጣው የተረደችው ሚስት ወደ ነቢዩ በመምጣት ስለ ጉዳዩ ነገረችያቸው።











