ይህ ነጥብ ምን ያህል እንደተወዛገባችሁ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናያለን፣ “ሃሩን” هَارُونَ ማለት በአማርኛችን “አሮን” ተብሎ በቁርኣን የተጠቀሱ ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች አሉ፣ እነርሱም አንዱ የሙሴ ወንድም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም፣ ይህን ነጥብ በነጥብ እንመልከተው፦
Category: ምላሾች
ሁሉም ሙስሊም ጀሀነም ይገባል?
19፥71 *ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው*፡፡ ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ وَإِن مِّنكُمْ إِلَّا وَارِدُهَا ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتْمًا مَّقْضِيًّا ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا
ሁሉም ሙስሊም ጀሀነም ይገባል?
ወገኖቻችን የዚህን አንቀጽ ትክክለኛ መልእክት መረዳት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ትልቅ ስህተት ላይ ወደቁ፡፡ ጭራሹኑ እንዲህ ሲሉም ተደመጡ፡- በዚህ አንቀጽ መሰረት ሙስሊሞች ሁሉ ጀሀነም እንደምትገቡ ይህ አንቀጽ ይናገራል!! ያሳዝናል፡፡
አደምን በአምሳያው ፈጥሮታል?
ይህንን ሀዲስ አስመልክቶ አንዳንድ ክርስቲያኖች የዘፍጥረቱን አንቀፅ በማሰብ “አደም በአላህ አምሳያ” ተፈጠረ ማለቱ እኛ የአምላክ ምስልንና ቅርፅን ይዘን መገኘታችንን ያሳያል ሲሉ ሊያቀርቡ ይሞክራሉ፡፡
ለምን “ቀጥተኛውን መንገድ” ምራን?
ከአንድ ወንድሜ በፌስቡክ ፔጅ በinbox የመጣልኝ ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄውም ይህ ወንድሜ እንደጻፈልኝ፡- ክርስቲያኖች እንዲህ ይላሉ ‹‹እናንተ ለምንድነው ሁሌ ሶላት ስትሰግዱ፡ ቀጥተኛውን መንገድ ምራን የምትሉት? መንገዱን አላገኛችሁትም ማለት ነው? በሃይማኖታችሁ ላይ ጥርጣሬ እንዳደረባችሁ አያሳይምን? ወደኛ ሃይማኖት እንዲመራችሁ እኮ ነው የምትጸልዩት›› በማለት ሰዉን ስለሚያደናግሩ የተወሰነ ምላሽ ብትሰጥበት ብሎኝ ነው፡፡
ኢስላም ውሸትን ፈቅዷልን? – ሀዲስ ላይ
ክቡራን ወንድሞቼና እህቶቼ! ዛሬም እንደተለመደው የማስቃኛችሁ ነገር ቢኖር፡ ኢስላም ለሃይማኖትህ ስትል መዋሸትን ይፈቅዳል! የሚለውን የካፊሮችን ከንቱ ክስ ነው፡፡ ባለፈው በቅዱስ ቁርኣን ላይ ስለቀረበው ገለባ ክስ ምላሹን አይተናል፡፡ ዛሬ ደግሞ ሌላ ቅጥፈትን አብረን እንመለከታለን፡፡ እነዚህ ሰዎች ምንም የራሳቸው ዕውቀትና ተሞኩሮ የሌላቸው፡ እንደ ገደል-ማሚቱ የተነገራቸውን ብቻ የሚያስተጋቡ፡ የጉዳዩን እውነተኝነት ከማጣራት ይልቅ በጥላቻ ስሜት ወሬውን ማሰራጨት የሚወዱ ናቸው፡፡ እስኪ ኢስላም ለሃይማኖትህ ስትል ዋሽ! ብሎ የፈቀደበትን ማስረጃ አሳዩን ስንላቸው ከሼህ ጎግል ያገኙትን ይህን ሐዲሥ አቅርበዋል፡፡ የሚገርመው ቡኻሪና ሙስሊም እያሉ ቁጥር መለጠፍ እንጂ ሐዲሡን አስቀምጡት ሲባሉ ማምጣት አይችሉም፡፡ ቁጥሩንስ ቢሆን የተነገራቸው እንጂ መች ያገኙት ሆነና፡፡ ለማንኛውም ሐዲሡን ላስቀምጥላችሁና ለሃይማኖትህ ስትል ዋሽ! የሚለውን ከንቱ የጠላት ክስን በአላህ ፈቃድ መና እናስቀረው ኢንሻአላህ-
ሁለቱ መለኮታዊ እጆች!
በዚህ አምላካዊ ቃል ላይ ከክርስቲኖች በኩል ሁለት ጥያቄ ተነስቷል፡፡ የመጀመሪያው፡- አንቀጹ አላህ እጆች እንዳሉት የሚናገር ነውና፡ እርሱ አካል እንዳለው በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለዚህ እናንተ አላህ ማንንም አይመስልም የምትሉት ለምንድነው? የሚል ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ፡- በዚሁ አንቀጽ ላይ ጌታ አላህ ኢብሊስን ‹‹ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ) ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?›› ሲለው፡ አላህ ኢብሊስን እንዲህ ሲጠይቀው ፡ ኢብሊስ ኮርቶ ይሁን ወይም ከትእቢተኞች ኾኖ ሁን አላወቀም ነበር ወይ? የሚል ነው፡፡ ጽሑፍን ላለማርዘም እና አንባቢንም ላለማሰልቸት ሲባል፡ የመጀመሪያውን ዛሬ እንመለከተውና፡ ሌላኛውን ደግሞ በአላህ ፈቃድ በሌላ ቀን እንመለስበታለን ኢንሻአላህ፡፡ ምላሹም እንደሚከተለው ይኾናል፡-
የውሻው ተረት ተረት
ከአንድ እህቴ በኩል የቀረበልኝ ሀሳብ ስለሆነ እንጂ መልስ ለመስጠት ብዙም አስቤበት አላውቅም ነበር፡፡ ይሄን ያህልም ሰዎች ለጉዳዩ ቦታ ይሰጡታል ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ነው፡- ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በወቅቱ የነበሩ ሰዎችን እሳቸው ነቢይ እንደሆኑ ለማሳመን፡ ከአፈር ውስጥ ወተት ፈለቀልኝ የሚልን ሀሳብ በልባቸው ይዘው ወተትን በአፈር ውስጥ ይቀብሩታል፡፡ ከዛም ወደ ህዝባቸው ዘንድ በመሄድ ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ትክክለኛ ነቢይ ለመሆኔ ማስረጃ ከፈለጋችሁ፡ ይኸው ከአፈር ውስጥ በተአምር ወተት ሳፈልቅ ኑ ተመልከቱ! በማለት ሰዎቹን ወደ ስፍራው ይዘው ይጓዛሉ፡፡ ውሻ ደግሞ ከሩቅ የማሽተት ተሰጥኦ አለውና በስፍራው ሲደርሱ ውሻው አፈሩን በእግሮቹ ጣት በመታገዝ እየቆፈረው ወተቱን ቀድሞ በማሳየት አጋለጣቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ውሻ በኢስላም የተጠላው የሚል ነው፡፡
ሴቶችን ግረፏቸው?
ለዛሬ የማስቃኛችሁ፡- ቅዱስ ቁርኣን ሚስቶቻችሁን ምቱ! በማለት ያዛል፡ ስለሆነም ሴቶች ተበድለዋል የሚለውን ቅጥፈት ነው፡፡ ለዚህ ክሳቸውም ተከታዩን የቁርኣን ክፍል ዋቢ አድርገው አቅርበዋል፡-
ሥላሴ እና የተውሒድ ክፍሎች
አንድ ሙስሊም ‹‹አላህ አንድ ነው!›› ብሎ አመነ ማለት፡ እሱ አላህ ሁለት ወይም ሶስት ወይም ከዛ በላይ አይደለም ብሎ ተቀበለ ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ የአላህን ሁለትነት፣ ሶስትነትና ብዜትን አምነው የሚቀበሉ ሰዎችን ተቃወመ፡ በእምነታቸውም ካደ ማለት ነው፡፡
ታዲያ ከዚህ ሙስሊም የሚፈለገው እምነት ‹‹አላህ አንድ ነው!›› የሚለው እምነት ብቻ ነውን? የአላህ ነቢያትና ሩሱሎችስ የተላኩት፡ አላህ ‹‹አንድ አምላክ›› ነው የሚለውን ትምህርት ብቻ ለማስተማር ነውን? በፍጹም አይደለም!፡፡ ይህ አይነት ንግግር ከአላዋቂዎች አንደበት እንጂ ከማንም አይጠበቅም፡፡ ጉዳዩን በማስረጃ ዘርዝረን እንመልከተው፡-











