የጀነት ሰዎች ከሚያገኙት መንፈሳዊ እርካታ መሀል አንድ የነቢያትን ጉርብትና ማግኘት ነው፡፡ አማኞች በጀነት ከነቢያት ጋር በመሆን፡ በአንድ ላይ የመሰብሰብን ዕድል ይጎናጸፋሉ፡፡ በተለይ ከነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ጋር መሆን፡፡ አላህ ይወፍቀን፡-
Category: ምላሾች
ጀነትና ጸጋዎቿ | ክፍል አንድ
ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ከካፊሮች በኩል የተነሳ አንድ ስሞታ አንብቤ ነው፡፡ እሱም፡- በሙስሊሞች ዘንድ ስለጀነት ሲወሳ ሁሌም የሚያስቡት በውስጧ ሚስቶች መኖራቸውንና የስጋ ፍላጎትም እንደሚከናወንባት ብቻ አድርገው ማሰባቸው ነው፡፡ በርግጥ እነዚህን ሰዎች እስኪ በናንተ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ገነት ጸጋዎች ምን የተዘረዘረ ነገር አልለ? ብለን ብንጠይቃቸው ምንም መመለስ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም መጽሐፉ ይህን ነገር ከመዘርዘር ተቆጥቧልና!!፡፡ እነሱም መመሪያ መጽሐፋቸውን ተከትለው ዝም ማለት ሲገባቸው፡ ጭራሽ በማያውቁት በሌላ ዕምነት ውስጥ ገብተው መዘባረቅ ከጀመሩ የኛ ዝምታ እስከመቼ ነው? ቢያንስ እንኳ ምላሹን ለሙስሊም ወንድሞችና እህቶች በተጠየቁበት ጊዜ እንዲረዳቸው፡ በዛውም አላህ ልቡን የከፈተለት የሌላ ዕምነት ተከታይ ካለም ጉዳዩን በልበ-ሰፊነት እንዲመለከተው ለማገዝ ተዘጋጅቷል፡፡
ማነው የሚያጠመው?
አንዳንዶች ባለማወቅ ለመረዳት፣ ሌሎች ደግሞ ግራ ተጋብቶ ሌላውንም ግራ ለማጋባት አላህ ለምን የፈለገውን ያጠማል? የሚል ጥያቄ ያለሳሉ፡፡ ጭራሽ የአላህን ፍትሐዊነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ለማስገባት ይሞክራሉ፡፡ ይህን ሀሳብ በአግባቡ ለመረዳት ሙስሊሞች ዘንድ መጥተው ጠይቆ መማር ሲገባ፡ ጭራሽ በመለኮታዊ አሰራሩ ጣልቃ ገብተው፡ እነሱ ከሱ በላይ ለፍጡሩ ተጨንቀው፡ አላህን ተከሳሽ እራስን ከሳሽ ማድረጉ ምን የሚሉት ዕብደት ነው? ዕብድም ደፍሮ እንደዚህ መናገሩን እንጃ!! ለማንኛውም ቅዱስ ቃሉ ‹በመልክተኛው ላይ ያለበት መልክቱን ማድረስ ብቻ ነው› ስለሚል፡ እኛም እውነታውን በመግለጽ፡ በነሱ ላይ ማስረጃውን በማቆም ከሐቅ የጠፋም ከማስረጃ በኋላ እንዲጠፋ፣ በሐቁ ሰበብም ወደ እውነት የሚመጣ እንዲመጣ የበኩላችንን እንወጣለን፡፡ ‹‹ወማ ተውፊቂ ኢልላ ቢላህ›› (ለማንኛውም መልካም ነገር ገጠመኛችን ከአላህ እንጂ ከማንም አይደለም››!! እንዲል ቃሉ፡፡ ጉዳዩ ግልጽ እንዲሆንም በአራት ነጥቦች በመከፋፈል በጥያቄ መልክ አቀርበዋለሁ፡-
ኢስላም ውሸትን ፈቅዷልን?
ክቡራን ወንድሞቼና እህቶቼ! ዛሬም እንደተለመደው የማስቃኛችሁ ነገር ቢኖር፡ ኢስላም ለሃይማኖትህ ስትል መዋሸትን ይፈቅዳል! የሚለውን የካፊሮችን ከንቱ ክስ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ምንም የራሳቸው ዕውቀትና ተሞኩሮ የሌላቸው፡ እንደ ገደል-ማሚቱ የተነገራቸውን ብቻ የሚያስተጋቡ፡ የጉዳዩን እውነተኝነት ከማጣራት ይልቅ በጥላቻ ስሜት ወሬውን ማሰራጨት የሚወዱ ናቸው፡፡ እስኪ ኢስላም ለሃይማኖትህ ስትል ዋሽ! ብሎ የፈቀደበትን ማስረጃ አሳዩን ስንላቸው ከሼህ ጎግል ያገኙትን ይህን ሐዲሥ አቅርበዋል፡-
በጀነት ውስጥ “ጠጅ” እንዴት ይኖራል?
አንድ ክርስቲያን ወገኔ በዚህ የቅዱስ ቁርኣን ክፍል ውስጥ ‹‹ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ›› የሚለው ቅዱስ ቃል ላይ በመመርኮዝ ሁለት ጥያቄዎችን ጠይቆኛል፡፡ እነሱም፡-
1ኛ. አላህ በናንተ ላይ እርም ያደረገው አልኮሆል መጠጦችን መጠጣት ነው ወይስ መስከር?
2ኛ. ደግሞስ በዚህ ዓለም የተከለከላችሁትን መጠጥ እንዴት በጀነት ተፈቀደላችሁ? በማለት ጥያቄውን አስከተለ፡፡
ለእነዚህ ጥያቄዎች እኔ ያለኝ ምላሽ እንዲህ ይቀርባል፡-
ለምን ሴቶች በጀሀነም በዙ?
ይህንን ነቢያዊ ሐዲሥ መሰረት በማድረግ አንዳንድ ክርስቲያን ወገኖች፡ በእስልምና አብዛኞቹ መስሊም ሴቶች ጀሀነም እንደሚገቡ ይታመናል በማለት የተሳሳተ ምልክታ ይዘው ሌላውንም ለማሳሳት ይሞክራሉ፡፡ ጭራሹኑ የሴቶችን የመዳን ተስፋ ያደበዝዘዋልም ሲሉ ይከሳሉ፡፡ ከኛ ሙስሊሞች ደግሞ የሚጠበቀው አገነዛዘቡ የተበደለውን ሐዲሥ የተቃና ማድረግ ስለሆነ፡ እውነትን ለሚፈልግ ሰው ይኸው ትክክለኛውን ማብራሪያ እንካችሁ ብለናል፡-
አላህ ከፈጠራቸው ፍጥረታት የተጠላው ጥቁር ሰው ነው?
የኢስላም ጠላቶች ኢስላምን በመረጃ መርታት ቢያቅታቸው፡ የሚኖራቸው አማራጭ የሀሰት ወሬዎችን በኢስላም ላይ መንዛት ነው፡፡ የነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ታሪክ ላነበበ ሰው የካፊሮችን ሴራ ለመረዳት ብዙም አይከብደውም፡፡ ከሀሰት ቅጥፈቶቻቸው አንዱ፡- አላህና መልክተኛው ያላሉትን ብለዋል ብሎ መዋሸት፡ አልያም የተነገረውን ነገር ሀሳቡንና መልእክቱን እንዲስት፡ ከፊትም ሆነ ከኋላ ወይም ከመሀል ቃላትን በመቁረጥ ማቅረብ ነው፡፡ ያ አልሳካም ያለ ጊዜ ደግሞ ትርጉሙን ቀይሮ የዋሁን ህዝብ ማምታታት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
ፊዳከ አቢ ወኡምሚ ያረሱለላህ!!
ጽሁፉ ያተኮረው በነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ ነው፡፡ ጭብጡም፡- ‹‹ለምን ለሳቸው ‹ፊዳከ አቢ ወኡሚ› ይባላሉ? ለምን በየቀኑ ‹ባለውለታዬ ሐቢብ ተምሳሌቴ፣ ስላንቱ ይሰዉ እናቴና አባቴ› በማለት ያስነብቡናል? ደግሞም ጉዳዩ መረጃ የሌለው የስሜት መገንፈልና የመድረክ ሞቅታ የወለደው ነው፡፡ ፊዳ ማለት መስዋእት ነውና፡ መስዋእት የሚገባው ደግሞ ለሕያው አምላክ ነው፡፡ ለእሳቸው መስዋእት ማቅረብ ደግሞ፡ እሳቸውን በአምላክ ቦታ ማስቀመጥ ነው፡፡ ለዚህ ነው ነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አምላክ አድርጋችሁ ይዛችኋል የምንለው፡፡››
የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) | ክፍል -1
በኡስታዝ አቡ ሀይደር በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡ (አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡ 1/ ከርሱ በሆነው ቃል፡- ” إِذْ قَالَتِ الْمَلآئِكَةُ يَا مَرْيَمُ…
እውን አንተ የጀነት ነህ?
ከተወሰኑ አመታት በፊት እዛው በሀገሬ ሳለሁ አንድ የክርስትና (ፕሮቴስታንት) እምነት ተከታይ ከሆነ ሰው ጋር ስወያይ፡ እኔንም የጠየቀኝ ጥያቄ ነበር፡፡ የጥያቄው ይዘትም፡- አንተ ጀነት ትገባለህ ወይስ አትገባም? የሚል ነበር፡፡ እኔም በወቅቱ አጠር አድርጌ፡- እኔንጃ! አልኩት፡፡ እሱም ቀጠለና፡- ታዲያ ጀነት ግባ አትግባ እርግጠኛ ያልሆንክበትን እምነት እንዴት ትከተላለህ? አለኝ፡፡ እኔም የምፈልገው ይህ ጥያቄ እንዲነሳ ስለነበር፡ ከዚያ በኋላ አብራራሁለት፡፡ ምን ብለህ? ትሉኛላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ኢንሻአላህ በአላህ ፈቃድ ያብራራሁለትን እነግራችኋለሁ፡፡ ዛሬም በፌስቡክ ላይ ጥያቄው ተደጋግሞ ሲነሳ ስላየሁ፡ ለሁላችን ይሆን ዘንድ ሰፋ ባለ ማብራሪያ ለናንተ ላቀርበው ወደድኩ፡፡ አላህ እውነቱን ተረድተን በሐቅ ላይ የምንጸና ያድርገን፡፡ ምላሹም ይህን ይመስላል፡-











