ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ቁርኣንን ለመተቸት ከሚያነሷቸው ሙግቶች መካከል ቁርኣን ስለ ሥነ-ፈለክ “astronomy” የሚናገረው ነገር በዘመናዊው ሳይንስ መነፅር ውድቅ ስለሆነ የአምላክ ቃል ሊሆን አይችልም የሚል ነው። ለዚህም የሚከተለውን አንቀጽ ያለ አግባብ በመጥቀስ ቁርኣን ምድርን ጠፍጣፋ አድርጎ እንደገለጻት ይናገራሉ:-
Author: Admin
አል-መሲሕ
አምላካችን አላህ ታላቁን መልዕክተኛ ነቢዩ ኢየሱስን “መሲሕ” በሚለው የማዕረግ ስሙ ወደ 9 ጊዜ በተደጋጋሚ ይጠቅሰዋል። በሱረቱል አሊ-ዒምራን አንቀጽ 45 ላይ መላእክት የብስራትን ዜና ለማሪያም ይዘው ሲመጡ የሚወለደው ልጅ ስሙ “መሲሕ” ተብሎ እንደሚጠራ አስቀድመው ተናግረዋል። እስኪ ይህ የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ማዕረግ በኢስላም የስሙ ትርጓሜ ምንድነው ? አላህ ለዒሣ ለምን ይህንን ለቀብ “title” ሰጠው? የሚለውን ነጥብ እንመልከት:-
መንፈስ ፈጠረኝ ?
ሥላሴያውያን በ4ኛው ክፍለዘመን የቁስጥንጥንያ ጉባኤ ላይ በአብላጫው ድምፅ ከአምላክ ጋር እኩል ይሆን ዘንድ የተወሰነውን መንፈስ ቅዱስ ባይብላዊ መሠረት ለማስያዝ በርካታ ጥቅሶችን አዛብተው ሲያቀርቡ ይስተዋላሉ። መንፈስ ቅዱስ በትኛውም የብሉይም ሆነ የሐዲስ ኪዳን መፅሐፍ ላይ እራሱን የቻለ ኑባሬያዊ መለኮት መሆኑን አይናገርም። ይህን ስንል አብዛኛውን ጊዜ ሚሽነሪዎች የሚከተለውን ጥቅስ ለመንፈስ ቅዱስ ፈጣሪነት ለመጠቀም ይሞክራሉ። እስኪ እንፈትሸው:-
እውን አል-ሐጃጅ የተወሰኑ የቁርኣን ቃላትን ለውጧልን ?
ሚሺነሪዎቹ ኪታብ አል-መሳሒፍ ላይ የተዘገበው ታሪክ በመጥቀስ ‟ሐጃጅ የተባለው ጥንታዊው ገዥ ከኡስማን ሙስሐፍ 11 የቁርኣን ቃላት ላይ ለውጥ አድርጓል ስለዚህ ቁርኣን ቃል በቃል ተጠብቋል የምትሉት ነገር ከእውነት የራቀ ንግግር ነው” ብለው ይናገራሉ። በዚህ ጹሑፍ ሰባኪዎቹ ያነሱት ታሪክ ምን ያክል ይደግፋቸዋል ? ምን ያክልስ ተዓማኒ ነው የሚሉትን ነጥቦች እንመለከታለን። እስኪ መጀመሪያ አል-ሐጃጅ ቀየራቸው የተባሉትን ቃላት ከጠቀሱት መጽሐፍ እንመልከት:-
የህጻናትን ምላስ መጥባት?
ሚሽነሪዎች እንደለመዱት ሐዲሳትን ከፊት እና ከኋላው እየቆራረጡ መልዕክቱን በማዛባት እንደው ከተሳካልን በማለት ስለ ዲናቸው መረዳት ያሌላቸውን ሙስሊሞች ለማሳሳት እንዲሁም ወደ እስልምና እየጎረፈ ያለውን የህዝበ ክርስቲያኑን ቁጥር ለመቀነስ ደፋ-ቀና ማለታቸውን ቀጥለዋል። “ነቢዩ ሙሐመድ ሀሰንና ሁሴን የተባሉትን ህጸናት (የልጅ ልጃቸውን) ምላሳቸውን (የነቢዩን ምላስ) እንዲጠቡ አስደርገዋል፣ ይህ ደግሞ የግብረሰዶማውያን ተግባር ነው” በማለት ይናገራሉ (ወነአዑዙቢላህ)። ጥላቻቸው እዚህ ደረጃ ደርሷል። በተመሳሳይ ፆታ አላስፈላጊ ንክኪ ላይ በጣም የከረራ አቋም ያላቸው አካል ላይ እንዲህ አይነት ተራ ትችት መክፈቱ በእውነቱ በጣም ያሳፍራል። አይደለም ታላቅ ነቢይን ይቅርና አንድ ተራ ሙስሊምን ራሱ በዚህ መወንጀል እንደ እውነቱ ከሆነ ይከብዳል። ለማንኛውም ወደ ምላሹ እንግባ:-
የብሉይ ኪዳን መበረዝ
ዛሬ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ተብሎ በሰፊው የክርስቲያን ማህበረሰብ ዘንድ እንደ አምላክ ቃል የሚታመንበት ባይብል ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግልጽ ብርዘትን እያስተናገደ የመጣ መፅሐፍ ነው። ባይብል ክፉኛ መበረዙን ለማወቅ የTextual criticism (ምንባበዊ ኅያሴ) ሊቅ መሆን አይጠበቅባችሁም። ለአፍታ ብቻ ሁለት ወይ ሦስት የአማርኛ ባይብል ቅጂዎችን አንድ ቦታ አድርጋችሁ ብታስተያዩት በመካከላቸው ያለው ግጭት እና ቅያሬ በቀላሉ የኃለ ታሪክ ችግሮቹን ያስገነዝባችኃል። እስኪ መለስ ብለን ይህን እውነታ ከራሳቸው ሊቃውንት እንስማ:-
በእኔ ምን እንደሚሰራ አላውቅም?
ብዙ ጊዜ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ከላይ ያለውን የቁርኣን አንቀጽ በመጥቀስ “ነቢዩ ሙሐመድ የራሱንም ሆነ የእናንተን የወደፊት እጣፋንታ አያውቁም ነበር፣ ገሀነም ይሁን ገነት የት እንደሚገባ እርግጠኛ አይደለም፣ ስለዚህ ለገዛ ሕይወቱ እንኳ ዋስትና ያሌላውን ሰው አንከተልም” ብለው ሲናገሩ ይደመጣሉ። ጥያቄው እስልምናን በማያውቁ ክርስቲያን ወገኖች የተነሳ ቢሆንም አሁን ላይ አንቀጹን በማጣመም ብዙዎች ህዝበ ሙስሊሙን ለማወናበድ ይጠቀሙበታል። እስኪ ቀጥታ ወደ ምላሹ እንግባ:- ወደ ትክክለኛው የቁርኣኑ ትርጉም ከመሄዳችን በፊት ነቢዩ ሙሐመድ አስቀድመው ጀነት መግባታቸውን እንደሚያውቁ እና ተከታዮቻቸውም ጭምር ጀነት መግባታቸውን እንደተናገሩ፣ ከወዲሁ የጀነት መሆናቸውን የመሰከሩላቸው ሰዎች መኖራቸውን በማሳየት ሙግቱን ከስር መሰረቱ እናፍርሰው።
እውን ሱረቱል ተውባ 9/31 ኢየሱስ ይመለካል ይላልን?
ከታላላቅ የአሏህ [ﷻ] ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው ኢየሱስ ሰው፣ ባሪያ፣ ነቢይ እና መልዕክተኛ ብቻ መሆኑ በማያሻማ መልኩ በቁርኣን ውስጥ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ከዚህ የዘለለ ቅንጣት ያኽል ስልጣን እንዳሌለው እና ለእርሱም እንደማይገባው በራሱ አንደበት መናገሩን ጌታ አምላካችን ገልጿል፣ (ሱራ 5፥116)። በእስልምና አምልኮ የሚገባው ለአንዱ አምላክ ለአሏህ ብቻ ሲሆን ከእርሱ ውጪ ሌላን አካል መገዛትም ሆነ ለእርሱ አጋር ማድረግ ሺርክ መሆኑ የመጀመሪያው አንቀጸ-ዕምነት ነው። ኢየሱስ አምልኮ የማይገባው ባሪያ መሆኑንና ይህን ባርነቱንም ፈጽሞ እንደማይጠየፍ በግልጽ ተቀምጧል፣ (ሱራ 7፥172)። ይህን እወነታ መቀበል የከበዳቸው አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት የቁርኣኑን አንቀጽ ከዐውድ በማጋጨት፣ የቋንቋውን ሰዋሰው በሚንድ መልኩ ከታች የሚገኘውን አንቀጽ ለኢየሱስ አምላክነት ለመጥቀስ ይሞክራሉ:-
ሁሉን ዐዋቂ አይደለም!!
ከወገኖቻችን ዘንድ ይህን የቅዱስ ቁርኣን አንቀጽ መሰረት በማድረግ የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ሁሉን እንደሚያውቅ መረዳት ይቻላል የሚል ድምጽ ይሰማል፡፡ ይህ ግን ፍፁም የተሳሳተ ግንዛቤ ነው፡፡ እንዴት ካሉም፡-
አደምና ሙሳ ተከራከሩ!!
እኛ የአላህ ባሮች የሆንን ሰዎች፡ አላህ ሲፈጥረን ኃጢአተኛ አድርጎ አልፈጠረንም፡፡ ኃጢአት የሌለበት ፍጹምና ንጹህ ኾነን ነው የተፈጠርነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን አደምና ሐዋእም (ዐለይሂማ-ሰላም) ሲፈጠሩ ንጹሀን ነበሩ፡፡ ስህተት የተጀመረው በቀንደኛው ጠላታችን ኢብሊስ አሳሳችነትና ጎትጓችነት በጀነት ውስጥ አትቅረቡ! የተባሉትን ዛፍ በመቅረባቸውና ከዛፉም ወስደው በመብላታቸው ነው፡፡ ይህ አለፍጽምና አደምና ሐዋእ በምርጫቸው ያመጡት እንጂ፡ በውርስ ወይንም በተፈጥሮ የተቀበሉት ባሕሪ አይደለም፡፡











